የባሶሊበን ወረዳ ገጽታ ባሶሊበን ወረዳ ማለት በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን ዉስጥ ከሚገኙት 18 ወረዳዎች አንዱ ሲሆን ጎነ  (triangular)ቅርፅ ያለዉ በምስራቅና በሰሜን አነደድ ወረዳ፣ በምዕራብ ጐዛምን ወረዳ፣ በደቡብ ምዕራብ ደግሞ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ያዋስኗታል፡፡የባሶሊበን ወረዳ ዋና ከተማ የጁቤ በመባል ይታወቃል፡፡ ወረዳዋ 2 የከተማና 22 የገጠር ቀበሌዎች ያሏት ሲሆን ጠቅላላ የቆዳ ስፋቷ  ,1,118.56 km2 (431.88 sq mi  ሄክታር ነው፡፡

የባሶ ሊበን ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት የኢቨ/ማ/ኢ/ዞ/ቡድን በወረዳው ያሉትን የኢንቨስትመንት አማራጮች የማጥናት ስራ በመስራትና የወረዳው እምቅ ሃብቶች ለባለሃብቶች የማስተዋወቅ ስራ በመስራት ወረዳውን ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ማድረግ የሂደቱ ዋነኛ ተግባር ነው፡፡

በመሆኑም የኢቨ/ማ/ኢ/ዞ/ቡድን ከላይ የተቀመጠውን የኢንቨስትመንት ግብ ከዳር ለማድረስ በወረዳው ያሉትን ጸጋዎች የመለየትና ምን ያህል እንደሚመረቱ፣ለምን የስራ መስክ አገልግሎት እንደሚውሉ ብሎም ለምን ያህል አመት ከገቢ ግብር ነጻ ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚያስችል የሚያሳይ የጸጋ ልየታ ስራ እንደሚከተለው ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

የባሶሊበን ወረዳ ገጽታ ባሶሊበን ወረዳ ማለት በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን ዉስጥ ከሚገኙት 18 ወረዳዎች አንዱ ሲሆን ጎነ  (triangular)ቅርፅ ያለዉ በምስራቅና በሰሜን አነደድ ወረዳ፣ በምዕራብ ጐዛምን ወረዳ፣ በደቡብ ምዕራብ ደግሞ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ያዋስኗታል፡፡የባሶሊበን ወረዳ ዋና ከተማ የጁቤ በመባል ይታወቃል፡፡ ወረዳዋ 2 የከተማና 22 የገጠር ቀበሌዎች ያሏት ሲሆን ጠቅላላ የቆዳ ስፋቷ  ,1,118.56 km2 (431.88 sq mi  ሄክታር ነው፡፡

የአየር ንብረቷ

  ወይና ደጋ ————— 46%

  ቆላ ——————— 54%

  የሙቀት መጠን ከ15-25 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ዓመታዊ የዝናቡ መጠን በአማካኝ ከ900-1200 ሚ.ሜ ይደርሳል፡፡