1. መግቢያ

  ዋነኛው የልማት አጀንዳ ድህነትን በማስወገድ ሀገሪቷን ወደ መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ ሀገሮች ጋር ማሰለፍ ሲሆን እንደቀደሙት የመጀመሪያው እድገትና ትራንስፎርሜሽን የእቅድ ትግበራ ዓመታት በ2012 በጀት ዓመት በተደረጉ ሁለንተናዊ ጥረቶች አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡እነዚህ እየተመዘገቡ ያሉ ሁለንተናዊ የልማት ውጤቶች በመንግስትና በህዝብ የተቀናጀ ጥረት በመሆኑ ይህንን ጥረት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በየበጀት አመቱ ያሉ መልካም ውጤቶችን ይበልጥ ለማስፋፋትና መሰረት ለማስያዝ እንዲሁም እጥረቶችን በመቅረፍና ወደ ታለመለት ግብ በመድረስ የተያዘውን የድህነት ቅነሳ ስራ  ለማረጋገጥ ሰፋፊ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው፡፡

  እንደሌሎች ጊዚያት ሁሉ በ2012 በጀት ዓመትም የክልሉን ልማት ለማስቀጠል እንዲቻልና በወረዳችን የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገትን የሚፈታተኑ አዝማሚያዎችን ለማስወገድ በማስፈፀም አቅም፣በዲሞክራሲና በመልካም አስተዳደር ስርዓት ግንባታ፣በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል፡፡ከምንጊዜዉም በላይ የክልላችን ብሎም የወረዳችንን ሰላም ስጋት በመቅረፍ የህዝቡ ወጦ የመግባት ስጋት ማስወገድና ሙሉ ሀቅሙን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ላይ እንዲያዉል በጠነከረ የህዝብ ተሳትፎ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ይገባል፡፡

 ስለሆነም የተገኙ መልካም ተሞክረዎች ላይ በመመስረት የክልሉን ብሎም የሀገሪቷን ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የልማት እድገት ለማረጋገጥ መላ ህዝቡን በማሣተፍ ሊተገበር የሚችለውን የሀገራዊውን ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሰረት አድርጐ በተዘጋጀው እቅድ ማዕቀፍ ውስጥ ያልተከናወኑ ተግባራትን ለቅሞ በመያዝ ያደሩ ተግባራትንም ጭምር በመፈፀም ከአቅዶ መቅረት ጎታች ልማድ መላቀቅ እንደሚያስፈልግ በመግባባት መስራት ተገቢ ይሆናል፡፡ከዚህ በተጨማሪም የወረዳውን ሰብዓዊና ቁሣዊ ሀብት በስፋት በማነቃነቅ የወረዳውን ህዝብ ከድህነት ለማውጣት እንዲቻል ከዚህ በፊት ይታዩ የነበሩትን አደናቃፊ አመለካከቶችና አስተሳሰቦች በማስወገድ አበረታች ጥረቶችን እና እሴቶችን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል፡፡

እቅዱ በዋናነት በውጤታማነት ተፈፃሚ እንዲሆን ሁሉም በየደረጃው የሚገኝ  የሲቪል ሰርቪስ አመራር አካላት ፣ሰራተኞች፣ህዝቡና ሌሎች አጋር አካላት በሙሉ የእቅዱን አላማዎችና ግቦች  በውል በመረዳት ለተፈፃሚነታቸው በተናጠልና በጋራ በከፍተኛ ተነሳሽነት በውጤት የሚገለጽ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፤ተግባራዊ ተሳትፎና ውጤታማ አፈፃፀም ሊመጣ የሚችለው ከላይ የተገለጹት አካላት በአመለካከት ደረጃ እቅዱን ለመፈፀም የሚያስችላቸውን ጠንካራ እምነት ሲይዙ እንደሆነም ግምት ውስጥ ሊገባ ይገባል፡፡

  ስለሆነም የተጀመረውን ድህነት ቅነሳ ለማስቀጠል አስተዋጽዖ የሚኖረው እና የሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አካል የሆነው ይህ የ2013 በጀት ዓመት የወረዳዉ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ ሰነድ ፣የ2012 በጀት ዓመት የልማትና መልካም አስተዳደር እቅድ አፈፃፀም፣የ2013 በጀት ዓመት እቅድ መነሻዎች የትኩረት መስኮች፣ዓላማዎች መሰረታዊ አቅጣጫዎችና ግቦች የበጀት ዓመቱ የክፍላተ ኢኮኖሚያት ዓላማዎች፣ግቦችና ዋና ዋና ተግባራት የልማት ፋይናንስ፣የወጭ አስተዳደርና የኦዲት ተግባራት፡የሁለተኛዉ የዕድገትና ትራንስፎሜሽን የ2013 ዕቅድና ያደሩ ተግባራት እንዲሁም ከወቅታዊ የለዉጥ ጉዞ ጋር የተከሰቱ መፈናቀል፤ስደት እና የስርዓት ዓልበኝነት ችግሮችን በሚቀርፍ መልኩ  እና የክትትልና ግምገማ ስርዓት የሚሉትን በውስጡ እንዲያካትት ተደርጐ ተዘጋጅቷል፡፡

 

 

 

 

 

ክፍል አንድ

2.የ2012 በጀት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ

  በመጀመሪያው እድገትና ትራንስፎርሜሽን የእቅድ አመታት የተገኘውን  አማካይ አጠቃላይ የወረዳ  የምርት እድገት የማስቀጠል በተለይም የግብርና ምርታማነትን የማሳደግ፣ቁጠባን የማጐልበት  የተጀመሩትን የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የማጠናቀቅና አዲሶችን የመገንባት ፣በሁሉም የልማት ዘርፎች የስራ እድል በመፍጠር በወረዳው የሚታየውን የስራ አጥነት ችግር የመቅረፍ፣ በሰው ኃይል ልማትና በኑሮ ደህንነት በዘላቂ የልማት ግቦች የተቀመጡትን መስፈርቶች የማሳካት የትምህርት፣የጤና እንዲሁም የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን የማጐልበት፣በሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች ምርታማነትን የማሳደግ ተግባራትን በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን በተጠናከረ መልኩ ለማከናወን ታቅዶ ወደ ተግባር በመግባት ውጤታማ ተግባሮችን ማከናወን ተችሏል፡፡በዚህም መሠረት በዋና ዋና ዘርፎች ያለው አፈፃፀም ማጠቃለያ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

   

 

 

 

 

 

 

 

2.1.ኢኮኖሚ ዘርፍ አፈጻጸም

2.1.1.የግብርና ዘርፍ አፈፃፀም

 ዋነኛ የኢኮኖሚ መሠረት ለሆነው የግብርናው ዘርፍ ትኩረት በመስጠት የግብርና ልማቱን በመስኖ ልማት፣በአፈርና ውኃ ጥበቃና አጠቃቀም ሥራዎች በመደገፍ በርካታ ተግባራት በመከናወናቸው ግብርናው ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል ጥረት ተደርጓል፡፡ ለ21657 አ/አደር የፓኬጅ ጥንቅሮችን (ሙሉ ፓኬጅ) በመስጠት የኤክስቴንሽን ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ ተይዞ ለ46612 ሄ/ር መሬት በዘር የተሸፈነ ሲሆን በመስመር የተዘራ 32851ሄ/ር(69%) ሲሆን 16350ሄ/ር መሬት በስንዴ፤9120ሄ/ር መሬት በበቆሎ ዘር ለመሸፈን ተቻለ ሲሆን ሁለቱም ሰብሎች በመስመር የመዝራት ዘዴ የተከተሉ ናቸዉ፡፡ በተጨማሪም 8810 ሄ/ር መሬት በጤፍ ዘር የተሸፈነ ሲሆን በመስመር የተዘራዉ 2210(25%) በመስመር ተዘርቷል፡፡የአ/አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ በ2011/12 የምርት ዘመን በኮሞዲቲ ክላስተር በስንዴ በ14 ቀበሌዎች 16343 ሄ/ር መሬት ለመሸፈን ታቅዶ 16350 ሄ/ር መሬት ለመሸፈን ተችሏል፡፡በተመሳሳይ በምርት ዘመኑ በኮሞዲቲ ክላስተር በበቆሎ በ22 ቀበሌዎች 10229 ሄ/ር መሬት ለማልማት ታቅዶ 9120(89%) ለመፈፀም ተችሏል፡፡የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት በተመለከተ በ2011/12 የምርት ዘመን 97856 ኩ/ል ለማቅረብ ታቅዶ 96452 ኩ/ል በማቅረብና በማሰራጨት 98.5% በፈፀም ተችሏል፡፡ይህም በ2010/2011 ከነበረዉ የ91560ኩ/ል አጠቃቀም በ11575 ኩ/ል ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ልዩነቱ ከዚህ ዓመት በፊት ያልተደረሱ አ/አደሮች እንዲጠቀሙ በማድረግ የመጣ ነዉ፡፡በኮሞዲቲ ክላስተር አሰራር ተከትሎ የመጣዉ የምርት ጭማሪ እና የምረት ጥራት ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባዉ ተግባር ነዉ፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ የስንዴ አብቃይ ቀበሌዎች በአፈር አሲዳማነት የአፈር ለምነት በመቀነሱ ምክንያት ምርታማነታቸዉ እየቀነሰ መጥቷል፡፤ይህን ችግር ለመቀነስ በበጀት ዓመቱ 3162ሄ/ር መሬት በኖራ ለማከም ዕቅድ ተይዞ 66.5ሄ/ር ብቻ(23%) ለማከም ጥረት ተደርጓል፡፡በኖራ የማከሙ ስራ ከዕቅድ አኳያ አፈፃፀሙ ዝቅተኛ ነዉ፡፡ስለሆን የችግሩን አሳሳቢነት የሚመጥን እርምጃ አልተወሰደም፡፡በተጨማሪምበ2011/12 ማዳበሪያ በምክረ ሀሳቡ መሰረት ያለመጨመር፤ምርጥ ዘር ያለመጠቀም፤የአፍር ለምነት ማስጠበቂያ ስራዎችን አቀናጅቶ ያለመጠቀም፤የሰብል ወቅት(ክሮፕ ካላንደር) ጠብቆ የእርሻ ስራን አለመከወን፤በተለይ ወደ መካናይዝድ እርሻ ያለመቀየር ችግር እና አሰራርን የአለመቀየር የሚፈለገዉን ያህል ምርታማነት እንዳያድግ አድርገዋል፡፡

በመሆኑም በ2010/11 የምርት ዘመን በተከናወኑ የምርት ተግባራት በዘርፉ ለዉጥ ማስመዝገብ ቢቻልም በዓመቱ ያለዉ የምርት ጭማሪ ሲታይ አዝጋሚና የሚጠበቀዉን ያህል አይደለም፡፡ ለማሳያ ያህል በ2009 ዓመት ከነበረዉ የ1.9 ሚሊዮን ኩንታል የዋና ዋና ሰብል ዕድገት በ2010 ዓ.ም ማሳደግ ሲገባ ወደ ታች 1.57 ሚሊዮን መዉረዱ ከወዲሁ ርብርብ በማድረግ ማስተካከል ይገባል በሚል ቁርጠኝነት ተይዞ በመሰራቱ በ2010/11 በመኸር ብቻ ወደ 1.9 ሚሊዮን ማድረስ ተችሏል፡፡ይህም ምርታማነቱን በአማካኝ 51 ኩ/ል በሄ/ር ማድረስ ተችሏል፡፡ በሌላ መልኩ በበጀት ዓመቱ በመስኖ ልማት በነባር 7116.25 በአዲስ 360.5 በድምሩ 7476.75 ሄ/ር በማልማት 1.0 ሚሊዮን ኩ/ል ምርት ማግኘት ተችሏል፡፡በዚህ ኸውም በመኽር ምርቱ በተገኘው የ1.9 ሚሊየን ኩንታል እና በመስኖ ከተገኘዉ 108259 ኩ/ል የሰብል ምርት ብቻ ወስዶ ሲታይ በነፍስ ወከፍ ለአንድ የወረዳ ነዋሪ ከ 11.91 ኩንታል እህል የማቅረብ ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡  ከባለፈዉ ከነበረዉ የ2.61 ኩንታል በዜጋ ጭማሪ  አሳይቷል፡፡

ለተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራዎች ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ከፍተኛ ርብርብ ተደርጓል፡፡በተፈትሮ ሀብት ስራ ወሳኝ ሀይል የሆነዉን ቀያሽ አ/አደር የማሰልጠን ስራ 2682 ቀያሽ አርሶ አደሮች ለማሰልጠን ታቅዶ 2560(95.5%)ለማሰልጠን ተችሏል፡፡የመረጃ ታማኒነት ወይም ጥራት በእጅጉ የአደገ እንደሆነ ታሳቢ ተደርጎ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዉ የሚሳተፉ 44923 የሰዉ ሀይል ልየታ በማከናወን ከተሳትፎ አኳያ 44.77% ብቻ መሆኑ የተሰራዉ የንቅናቄ ሰራ ከአ/አደሩ ጋር ከልብ ሳይግባቡ ወደ ተግባሩ አለመገባቱን ወይም ክፍተት ያለ መሆኑን ያሳያል፡፡

የተፈጥሮ ሀብት ልማትና የጥበቃ ስራን ለማጠናከር 136 የተፋሰስ ስራን ማካሄድ፣672.3 ሄ/ር የማሳ ላይ እርከን ስራ ተከናዉኗል፡፡3359 ሄ/ር የእንስሳት መኖ ለመጨመር የሚሻሻሉ የግጦሽ መሬቶች መስፋት ተችሏል፡፡

 የመስኖ አትክልትና ፍራፍሬ ስራዎች በተመለከተ በ1ኛ ዙር 1347.75 ሄ/ር በነባር መስኖ በአዲስ 93.6 ሄ/ር በድምሩ 1441.35ሄ/ር መሬት በሰብል ለመሸፈን ጥረት ተደርጓል፡፡በዚህም 86% ከዕቅድ ንፅፅር ምርት ማግኘት ተችሏል፡፡በ2ኛዉ ዙር ከዕቅዱ 70% በማልማት 81.7% ከዕቅድ ንፅፅር ምርት ማግኘት ተችሏል፡፡በበጀት አመቱ 169ሄ/ር በፓኬጁ መሰረት ቅመማቅመም አትክልትና ለማልማት ታቅዶ 130.9 ሄ/ር(77.5%) በመሸፈን 6424 ኩ/ል ምርት ለማምረት ተችሏል፡፡በ2011/12 በመኸር 136310 የቡና ችግኝ ለመትከል ታቅዶ 129580 በማዘጋጀት 106750 ችግኝ በመትከል 44ሄ/ር ለመትከል ተችሏል በዚህም 1564 አ/አደሮችን ማሳተፍ ተችሏል፡፡ በጥንካሬ የሚነሱት እንቅስቃሴዎች የበለጠ አጉልቶ መቀጠል ያስፈልጋል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ የገፀ ምድር እና የከርሰ ምድር ዉሃን ለመጠቀም ወንዝ ጠለፋ፤በምንጭ ጠለፋ፤በባህላዊ ካናል ጠረጋ፤የእጅ ዉሃ ጉድጓድ፤ጅኦ ሜምብሬን የመሳሰሉ የዉሃ መያዠ ስልቶችና አሰራሮች ተክኒሎጆች ላይ የነበረዉ ጥረት ከነበረን ፖቴንሻል አንፃር አነስተኛ ነበር፡፡ በቀጠይ ልዩ ትኩርት ተሰጥቶ ሊሰራበትም ይገባል፡፡

  በእቅድ ዘመኑ የአብዛኛው ተግባራት አፈፃፀም  መጠነኛ እድገት የተመዘገበ ቢሆንም በሴክተሩ ውስጥ ትራንስፎርሜሽን በሚያመጣ መልኩ የተከናወነ አይደለም፡፡ግብርና በአጠቃላይ ኢኮኖሚው ውስጥ የመሪነት ሚናውን እንዲጫወት ከተፈለገ ከተለመደው የምግብ ሰብል ምርት ወደ ከፍተኛ ምርታማነት እድገትና ጥራት በተጨማሪ ወደ ላቀ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ወዳላቸው የጥራጥሬ የቅባት፣አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የኢንዱስትሪና የኤክስፖርት ስታንዳርድ የሚያሟሉ ተዋጽዎ ምርቶች መሸጋገር አለበት፡፡

 የግብርና ልማታችን በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ከተያዘው ግብ አንፃር በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኝና በሴክተሩ ውስጥ ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀዉን መዋቅራዊ ለውጥ ለማሳካት በሚያስችል ደረጃ  አለመሆኑን ያሳያል፡፡በሌላ መልኩ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ የግብርና ልማቱን ከዝናብ ጥገኝነት የሚያላቅቅ ቀጣይም የመስኖ ግብርና ዋናውን የምርት ድርሻ እንዲይዝ በሚያስችል አግባብ ታቅዶ ወደ ተግባር እንቅስቃሴ ለመግባት ቢታቀድም አፈፃፀሙ ዝቅተኛ ሆኖ ይታያል፡፡

  ይህም ከአካባቢ አካባቢ፣ከተፋሰስ ተፋሰስ በተሰራው ሥራ ልዩነቶች እንዳሉ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡በ2011 ዓ.ም በጀት ዓመት የተሰሩ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራዎች ከውሃ ጋር እንዲቀናጁና ውሃ በመሰነቅ ረገድ በተወሰኑ ቀበሌዎች ጥሩ ጅምር ያለ ቢሆንም የተግባሩ አፈፃፀም ዝቅተኛና ሁሉንም አካባቢ ያዳረሰ ያለመሆን ችግር ነበረበት፡፡ከዚህም በመነሳት ከመጀመሪያው የዕትዕ ዘመን እና በሁለተኛዉ ዕትዕ የተገኙ ልምዶችን በመቀመር የ2011/12 በጀት ዓመት አፈፃፀምን እንደግብዓት በመጠቀም በ2012/13 በጀት ዓመት አፈፃፀሙን ሆነ የሚገኘውን ለውጥ ለማሻሻል ብዙ ጥረት ተደርጓል፡፡ቀጣዩ የትግበራ ዓመት ልምዶችም በተሻለ ሁኔታ ግምት ውስጥ የሚገቡበት፣ታሳቢዎች ከውጤትና ዘላቂነት ጋር በማስተሳሰር ለመተግበር የተቀናጀ ጥረት የሚደረግበት ዓመት የሚሆን ስራ ይሰራል፡፡

2.1.2 እንስሳት ሀብት አፈፃፀም

  በእንስሣት ሀብት ልማት ሥራ የተሠሩ ሥራዎች ሲታዩ ዘርፉን የአርሶ አደሩን ህይወት ሊቀየር በሚችል መልኩ አልተጠቀምንበትም እንዲሁም በእንስሳት ሃበት ልማት ስራችን የአካባቢ ፓቴንሻልን መሠረት ያደረገ ንቅናቄ መፍጠር ባለመቻሉ በዘርፉ በምርትና ምርታማነት የመጣው ዕድገት ዝቅተኛ ነው፡፡

በሰብል ልማት ረገድ ዝቅተኛ ፓቴንሻል ያላቸውን አካባቢዎች በእንስሳት ሀብት ልማት እንዲረባረቡ በማድረግ ውጤታማ ስራዎች በበቂ ሁኔታ አልተከናወኑም፡፡

የተሰሩ ሰውራዎች  ለማሳየት ያህል  በእንስሳት ሀብት ማድለብ በስጋ ምርት ደልበዉ ለገብያ የሚዉሉ እንስሳት 55095 ዳ/ከብት፣ 6023 በግና ፍየል 1881.046 ቶን ስጋ ለማምረት በእቅድ ተይዞ የተመረተ ምርት ከ 35095 ዳ/ከብት 871.3 ቶን ስጋ/62.3%/ ከ19124 በግና ፍየል 188.4 ቶን ስጋ/50%/ ምርት ማምረት ተችሏል፡፡የተመረተ ጠቅላላ ወተት ምርት 9022 ቶን ለማምረት በእቅድ ተይዞ 6850.1 ቶን/76%/ ከላም ለማምረት ተችሏል፡፡የእንስሳት መኖ ልማት ከተለያዩ መኖ ምንጮች የሚመረት ድርቅ መኖ 0.279853 ሚ/ቶን ለማልማት በእቅድ ተይዞ 0.8979 አፈጻጸም 43% ሲሆን የበልግና የመስኖ ዉሃን ተጠቅሞ በመስኖ መኖ ማልማት 99.37 ሄ/ር በእቅድ ተይዞ 56.34 አፈጻጸም 44.61% የወል ግጦሽ መሬቶችንና የግል ግጦሽ መሬቶችን የያዘ ነዉ፡፡

  የሁለተኛውን የእድገትና ትራስፎርሜሽን ዕቅድ መሠረት በማድረግ በግብርናው ዘርፍ ለአርሶአደሩ እርሻ ትኩረት በመስጠት የግብርናውን ምርትና ምርታማነት ለማሣደግ ጥረት ተደርጓል ፡፡ በዚህም መሻሻሎች የታዩ ቢሆንም አርሶ አደሩን ሙሉ በሙሉ የዘመናዊ የግብርና ልማት ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ በማድረግ የግብርና ምርታማነትን በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ አልተቻለም ፡፡ በተወሰኑ አርሶ አደሮች ተሞክሮ ውጤታማ የሆነውን ቴክኖሎጅና የግብርና ዘዴ ወደ ሁሉም አርሶ አደሮች ለማድረስ አለመቻልና በዚህም በአርሶ አደሮች መካከል ሰፊ የምርታማነት ልዩነት መኖር ፣ የመስኖና የከርሰ ምድር ውሃ አጠቃቀም በማጎልበት የግብርና ልማቱን በማፋጠን የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ዓላማን ማሳካት አለመቻል ፣ የአነስተኛ የእርሻ መሣሪያዎች በጥራትና በብዛት በተፈለገው ጊዜና ቦታ ማቅረብ አለመቻል ኬሜካል ማዳበሪያ ባሻገር የተፈጥሮ ማዳበሪያ አጠቃቅም ማስፋፋት አለመቻሉ ፣ የእንስሳት ሃብት ልማት ስራን በማስፋት ረገድ በመኖ አቅርቦት ፣ በዝርያ ማሻሻልና እየተተገበረ ያለው ስራ ውጤታማ አለመሆን በእንስሳት ህክምና አገልግሎት አሠጣጥ ጥሩ መሸሻል እየታየበት ቢሆንም  በድምር በዘርፉ እየታዩ ያሉ እጥረቶች ከፍተኛ ናቸው ፡፡ በመሆኑም እነዚህና ሌሎች ድክመቶችና ፈታኝ ሁኔታዎችን በቀጣይ የእድገትና ትራስፎርሜሽን የዕቅድ ዓመታት በማስወገድ ሁኔታዎችን በመቀየር አርሶ አደሩ ከእጅ ወደ አፍ ከሆነ የአመራረት ሂደት ተላቆ የግብረና ምርትና ምርታመነትን በማሳደግ ለኢንዱስትሪው ጥሬ ዕቃነት የሚያገለግሉ፣የህብረተሰቡን የምግብ ፍጆታ የሚያሟሉና የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኙ ምርቶችን በጥራትና በብዛት ለማምረት እንዲችል ለዘርፉ የተሠጠው ትኩረት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡

 

 

 

 

2.1.3. ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ስራዎች አፈፃፀም

  በከተማና በገጠር ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር እና የስራ አጥ ምጣኔን ለመቀነስ እንዲሁም የህብረተሰቡን ገቢ በማሣደግ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍልን ለማረጋገጥ በወረዳዉ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ የግድ ይላል ፡፡

   ለ2065 ስራ ፈላጊዎች በከተማና ለ5387 ስራ ፈላጊዎች በገጠር ለመመዝገብ በእቅድ ተይዞ 473 በከተማ አፈጻጸም 22.91%ና 7583 በገጠር አፈጻጸም 140% ፣የዩንቨርስቲ ምሩቃን ዕቅድ 484 ክንዉን 223 አፈጻጸም 46.07 % መመዝገብ ተችሏል፡፡ በአጠቃላይ በወረዳ 343 ኢ/ዝ ለማደራጀት በእቅድ ተይዞ 588 ኢ/ዝ የተደራጀ ሲሆን አፈጻጸም 171% ከዚህም ዉስጥ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተደራጀ 53 ኢ/ዝ በእቅድ ተይዞ 42 አፈጻጸም 79.24% ተደራጅቷል፡፡

  በጥቃቅንና አነስተኛ ኢ/ዞች የፋይናንስ ችግር ለመቅረፍ የብድር አቅርቦት መደበኛ ብድር አቅርቦት ብር 11465489 በእቅድ ተይዞ 16390400 አፈጻጸም 142%፣ተዘዋዋሪ ብድር የተሰራጨ በብር 20904627 በዕቅድ ተይዞ የተመለሰ ብር 5837943.5 በገጠርና በከተማ መመለስ 27%፡፡

  በእድገት ተኮር ተርፎች ክፍተትን መሰረት ያደረገ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ለ100 ነባር ኢ/ዝ በከተማና በገጠር ክንዉን 66 አፈጻጸም 66%፣ለ20 አዲስ ኢ/ዝ በከተማና ገጠር በዕቅድ ተይዞ 3 የተፈጸመ ሲሆን አፈጻጸም 15% የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት መስጠት ተችሏል፡፡

 

 

 

 

 

2.1.4.ንግድና ኢንዱስትሪና ገበያ ልማት

ንግድ ምዝገባና ፍቃድ፡-ንግድ ፍቃድ እድሳት እቅድ 2622 ክንዉን 2056/78.41%/፣አዲስ የተሰጠ የንግድ ምዝገባ ዕቅድ 520 ክንዉን 602 አፈጻጸም 100% አዲስ የተሰጠ የንግድ ፍቃድ ዕቅድ 1000 ክንዉ 1726 አፈጻጸም 100% ፣የተሰጠ የንግድ ምዝገባ ማሻሻያ መስጠት የአመት ዕቅድ 40 ክንዉን 19 አፈጻጸም 47.5%፣ምትክ የንግድ ስራ ፍቃድ መስጠት ዕቅድ 10 ክንዉን 13 አፈጻጸም 100%

ንግድ ዉድድርና ሸማቶች ፡፡-4000 ኩ/ል ስኳር ለማሰራጨት በእቅድ ተይዞ  400 ኩ/ል 100%፣ፓልም ዘይት የአመት ዕቅድ 360000 ሊትር ክንዉን 175743 አፈጻጸም 49%፣የዳቦ ዱቄት 624 ኩ/ል ክንዉን 313 ኩ/ል አፈጻጸም 50.1%ወቅታዊ የዋጋ ዝርዝር የለጠፉ ድርጅቶች ብዛት የአመቱ እቅድ 349 ክንውን 360 አፈፃፀም 100%

  ከኢንስፔክሽንና ሪጉሌሽ አንጻር ለ3529 የንግድ ምዝገባና ፍቃድ እድሳት አሰጣጥ የውስጥ ኢንስፔክሽን ማካሄድ በዕቅድ ተይዞ 3302 /93.5%/፣ የውጭ ኢንስፔክሽን የድርጅት በር ከበር ማካሄድ 11150 ታቅዶ 10723/96.1%)፣ የመለኪያ መሳሪያ ቬሪፊኬሽን እቅድ 4708 ክንውን 2986/63.36%/፣የመለኪያ መሳሪያ ኢንስክት ማድረግ እቅድ 13699 ክንዉን 14962/109%/ ማከናወን ተችሏል፡፡የዉጭና የዉስጥ ኢንፔክት በማድረግ የመጣ ለዉጥ/የተወሰደ እርምጃ ለ124 የቃል ማስጠንቀቂያ፣ለ88 እሽ የተደረገ፣ለ1 በፍ/ቤት ክስ የተመሰረተባቸዉ በአጠቃለይ ለ213 ነጋዴዎች እርምጃ ተወሰወዷል፡፡

  ከገብያና መሰረተ ልማት፡- ሁለገብ የገብያ ማእከላት ማሻሻል እቅድ 4 ክንዉን 4 /100%/፡- የሰሊጥ ገብያ ማሻሻል እቅድ 4 ክንዉን 3/75%/፣የገጠር መደበኛ ገብያ እቅድ 4 ክንዉን 2/50%፣የከተማ መደበኛ ገብያ ማሻሻል እቅድ 1 ክንዉን 1/100%/፣መጀመሪያ ደረጃ የቁም እንስሳት ገብያ ማሻሻል እቅድ 3 ክንዉን3 /100%/ ሲሆን አዲስ የገብያ ማእከላት ማቋቋም  በጥራጥሬ ገብያ እቅድ 2 ክንዉን 2/100%/ እንዲሁም የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን የገብያ ዋጋ መረጃዎችን መቀበል፣ማደራጀት እና8 መተንተን እስከዚህ ሩብ አመት እቅድ 52 ክንዉን 26/50%/መፈጸም ተችሏል በሰብል ምርት 35629.31 ኩ/ል የተገዛ ሲሆን 34271 ኩ/ል ሰሊጥ ደግሞ ወደ ምርት ገብያ ተልኳል፡፡

ከቁም እንስሳት ተዋጽኦ ግብይት ኳያ በጉዞ የተሸኘ የቁም እንስሳት ብዛት ዳልጋ ከብት በግና ፍየል እቅድ 7166 ክንዉን 1531/21.36%/ ለሀገር ውሥጥ የቀረበ ቆዳናሌጦ ብዛትየበግ/የፍየል ሌጦ ዕቅድ 45409 ክንውን 5336/100%/ ለሀገር ውሥጥ የቀረበ የእንስሳት ተዋፅኦ ለገበያ የቀረበ ዶሮ 8247፤እንቁላል 40000፤ወተት በሊትር 1842፤የቅቤ ትስስር በቶን 100 እና የአይብ ትስስር በቶን 20 ፤የማር ምርት ትስስር 500 ቶን ፣እንስሳት መኖ 3273 ዕቅድ ተይዞ  እስከዚህ ሩብ ዓመት ክንዉን ዶሮ 4620/56.02/፤ እንቁላል 38900/97.25/ ፤ወተት በሊትር 648/27.1/፤የቅቤ ትስስር 52.2/52.2/ በቶን ፤የአይብ ትስስር 8.51/56.88%/ ቶን ፤የማር ትስስር 422/84.4/ ቶን ፤እንስሳት መኖ 1257 /38.4%/ ማከናወን ተችሏል፡፡

2.1.5. ከገቢ ዘርፍ አንፃር

 የታክስ ከፋዩን ማህበረሰብ ስለግብር ትምህርት በመስጠት ለልማቱ ሊሆን የሚችል ኢኮኖሚዉ ያመጣዉን የግብር ገቢ ለመሰብሰብና ግብር ከፋዩ የግብር የመክፈል ሃላፊነቱን እንዲወጣ ለማስቻል የግብር ትምህርትና ኮምኒኬሽን ስራዎች በታቀደዉ መሰረት 32 መድረክ በማዘጋጀት ለወንድ 4475 ሴት 1543 ድምር 6018 ግንዛቤ ለመፍጠር በእቅድ ተይዞ 22 መድረክ በመፍጠር ለ1066 ወንድ 374 ሴት ድምር 1469 ቤት ለቤት ትምህርት ስልጠና ለ2000 ወንድ ለ800 ሴት ድምር 2800 ለሚሆኑ ግብር ከፋዩች ግንዛቤ ለመፍጠር በእቅድ ተይዞ ለ1600 ወንድ ለ1200 ሴት በድምሩ 2800/100%/ ግንዛቤ ተሰጥቷል፡፡

የደንበኛ አገልግሎት አሰጣጥ ፡-ቅሬታናይግባኝ አሰጣጥ በተመለከተ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የቀረበ 2 አቤቱታዎች ቀርበዉ 2 ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ከግብር ጋር በተያያዘ 204 አቤቱታዎች ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ የቀረበ ሲሆን ለ175/85.7%/ አቤቱታ ቅሬታ በማጽናት 24/11.76%/  አቤቱታ በመቀነስ 5/2.4%/ አቤቱታ ቅሬታዎችን በመጨመር የተወሰነላቸዉ ግብር ከፋይች ናቸዉ፡፡ በወረዳ ካሉት 1569 ግብር ከፋዩች ዉስጥ 204 ግብር ከፋዩች ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆኑ የብር መጠን 2251198.08 ከዚህ ዉስጥ 5 ግብር ከፋይ  በመጨመር ብር 4790፣175 ግብር ከፋይ በማጽናት የተወሰነላቸዉ ሲሆን የብር መጠን 2195053.54፣

በመቀነስ የተወሰነላቸዉ 24 ብር መጠን 31434.5 ግብር ከፋይ ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ ግብር ታክስ በዛብኝ በማለት ለግብር ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ  የቀረቡ አቤቱታዎች በቁጥር 36 ሲሆኑ የብር መጠናቸዉ 361134.21  ዉሳኔ የተሰጣቸዉ ግብር ከፋዩች የተቀነሰ/የጸና/ የብር መጠን በመጨመር 1 የብር መጠን 1100 በማጽናት 30 የብር መጠን 295548.21 በመቀነስ 5 የብር መጠን 37558.15 ድምር 334106.36 ብር፡፡

 ከገቢ አሰባሰብአኳያ፡- በአዲሱ በጀት ዓመት በአዲስ ወደ ግብረ መረቡ የገቡትን ነጋዴዎችና አከራይ ተብለው የተለዩትን በወቅቱ በመወሰን አሰራጭቶ ግብሩን ለመሰብሰብ የተቻለ ሲሆን በወረዳዉ ኢኮኖሚ በሚያመነጨዉ በብቃት ለመሰብሰብ ብር 35761599 ለመሰብሰብ በዕቅድ ተይዞ እስከዚህ ወር የተሰበሰበ 33379343.36 አፈጻጸም 93.33% ከተሰበሰበዉ ዉስጥ  ተጨማሪ እሴት ታክስ 235200 በእቅድ ተይዞ 167692/71.29%/፣ቲኦቲ ታክስ አሰባሰብ 5087911 በእቅድ ተይዞ 4294385.49/84.4/፣ የኪራይ ገቢ 46664 በእቅድ ተይዞ 68042.16/145/፣ሮያሊቲ ገቢ አሰባሰብ 40000 በእቅድ ተይዞ 621115.83/155/፣የካፒታል ዋጋ እድገት ገቢ 353100 በእቅድ ተይዞ 204601.16/57.94/፣የንግድ ትርፍ ገቢ አሰባሰብ 3487648 በእቅድ ተይዞ 3446203.73/98.81/፣ሌሎች ገቢዎች 4154122 በእቅድ ተይዞ 17285728.11/116.23/፣ወጭ መጋራት 183650 በእቅድ ተይዞ 179292.7/97.62/ ቅድመ ግብር/ዊዝ ሆልድ ታክስ/ 26000 በእቅድ ተይዞ 27329.8/105.11/ የጡረታ መዋጮ መረጃ  ከ22 የግል ድርጅት ብር 290952.36 መሰብሰብ ተችሏል፡፡

  አሰባሰብ በዘርፍ ሲታይ በእርሻ ዘርፍ 3904452 በእቅድ ተይዞ 2320943.1/59.44/፣በንግድ 10886560 በእቅድ ተይዞ 8886312.81/81.62/፣ሌሎች 20970587 በእቅድ ተይዞ 22172087.45/105.72/ በድምሩ 35761599 በእቅድ ተይዞ 33379343.36/93.33/ የተሰበሰበ ሲሆን በዋና ዋና የታክስ መደቦች  በቀጥታ ታክስ 25159870 በእቅድ ተይዞ 24886599.34/98.91/፣ቀጥታ ያልሆኑ ገቢዎች 5486281 በእቅድ ተይዞ 4922063.77/89.71/፣ታክስ ያልሆኑ ገቢዎች 5115448 በእቅድ ተይዞ 357063.77/69.8//በድምሩ 35761599 በእቅድ ተይዞ 33379343.36/93.33/ መሰብሰብ ተችሏል፡፡

2.2.መሠረተ ልማት የማስፋፋት አፈፃፅም

2.2.1.መንገድ

   በመንገድ ልማት ዘርፍ የወረዳዉን የገጠር መንገድ አዉታር ይዞታ በማሻሻልና ጥራቱን የጠበቀ የመንገድ አዉታር፣ የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽ በማድረግ የአጠቃላይ ልማትን ለማፋጠን በተቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት ፡-   የመንገድ ተደራሽነት ለማሳደግ በበጀት ዓመቱ እስከዚህ ሩብ አመት የተሰሩ ስራዎች  በወረዳ መስመሮች በተዘረጉ መንገዶች የመንገድ ቦይ ጠረጋ ስራ በኪ.ሜ 6.360 ወንድ 227 ሴት 61 ድምር 288 ህዝብ በማሳተፍ በወቅቱ የጉልበት ዋጋ በገንዘብ ሲቀየር ብር 10800 ያወጣ መሆኑ ይገመታል፡፡ከአብስራ-ደን የመንገድ ጥገና ስራ የነጠላ ዋጋ ሂሳብ በማዉጣት ጫራታ በማዉጣት 5 ኪ.ሜ ስራ መሰራት ተችሏል፤፣እና ከከየጁቤ-የላምገጅ ፊልጥኒ  የጥገና ስራ በሁሉም አቀፍ የገጠር መንገድ ተደራሽነት ፕሮግራም ባወጣዉ ነጠላ ዋጋ መሰረት ጫራታ ወጥቶ የጠረጋ ስራና የአፈር ድልዳሎ ስራ አልቆ ዳፕ እየተደረገ ነዉ፡፡ የፍልጢኝ ድልድይ በክልል ዋጋ ትመና መስራት ጫራታ ወጥቶ እየተሰራ ይገኛል፡፡የለመለም-4ቱ አምባ መንገድ ስትራክቸር ቦታ ልኬታናትመና ሰርቶ መስጠት እንዲሁም በክረምቱ ሳቢያ የተበላሹ ቦታዎች በኪ.ሜና በቦታ ለይቶ ማሳወቅ ተችሏል፡፡የተደፈኑና የተደረመሱ ቱቦዎች በኪ.ሜ በቦታ ለይቶ መስጠት ተችሏል እንዲሁም ያደሩነስራዎችን ማለትም የስትራክቸር ስራ ለመስራት ዉል ተይዞ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡የተደፈኑ 2 የተደረመሱ 1 ቱቦዎችን 1 በኪ.ሜ በቦታ ተለይተዉ እየተጠገኑ ይገኛሉ፡፡በሰዉ ሀይል የተጠገነዉ 41.688 ኪ.ሜ በማህበረሰቡ ተሳትፎ የተጠገነ የተሳትፎ የሰዉ ሀይል ብዛት ወንድ 179 ሴት..ድምር 179 ፤ከየጁቤት-የላምገጅ ፍጥኒ ድረስ ያለን መንገድ 14.898 ኪ.ሜ በማሽን ተጠግኖ ተጠናቋል፡፡ ከኮርክ-ቤተንጉስ ድረስ ያለዉ 8.635 ከ.ሜ ጫራታ አሸንፎ ስራዉ ተሰርቶ ተጠናቋል ፡፡አዲስ መንገድ ግንባታ በተመለከተ አዲስ መንገድ ከፈታ ስራ በሰዉ ሀይል 1.5 ከ.ሜ በማሽን 3.180 ኪ.ሜ በድምሩ 4.680 ከ..ሜ ተሰርቷል፡፡

ከመንገድ ደህንነት ዘርፍ በግንዛቤ ፈጠራ የተሰጣቸዉ እቅድ 68000 ክንዉን 83717/100%/ የህብረተሰቡ የግራ መስመር ተከትሎ መጓዝ ፤እና ለአሽከርካሪዎች ግንዛቤና ቁጥጥር ማድረግ በመስራት በዚህም መሰረት ቁጥጥር የተደረገባቸዉ አሽከርካሪዎች ብዛት 2216 ከነዚህም ዉስጥ ህግ ተላልፈዉ የተቀጡ 2216 ከቅጣቱ የተሰበሰበ ገንዘብ 630438.50 ብር ገቢ ማስደረግ ተችሏል፡፡

2.2.2 ዉሃ ሀብት ልማት አፈፃፀም

  የወረዳዉ ህዝብ ቁጥር 173750 ሲሆን የወረዳዉ ዉሃ ተጠቃሚ ህዝብ ብዛት 1654456 ነዉ፡፡የወረዳዉ የዉሃ ሽፋን አሁን ካለበት በ2013 በአማካኝ ወደ 95.2% ሲሆን የገጠር 96.8% የከተማ 100% ለማድረስ ይሰራል፡፡             

  የመጀመሪያ ደረጃ የመጠጥ ዉሃ መገኛ ጥናትና መጠንን ለማሻሻል 60 ለማድረግ ታቅዷል፡፡በዉሃ ተቋማትን ቁጥር  60 ለማዉጣት ታቅዷል፡፡ ዘርዘር አድርጎ ለማየት ማለትም 5 ገመድ ፓምፕ፣30 እጅ ጉድጓድ ፣15 መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓድ፣4 ምንጭ፤ማንዋል ድሪሊንግ 10 በገጠር ለይቶ ለማስቀመጥ 10 ዕቅድ ተይዟል፡፡

በተለያዩ የኢነርጂ ምንጮች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገት መፋጠን ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣የተሻሻሉ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ተጠቃሚዎች 3000 በእቅድ ተይዟል፡፡ 600 ምርጥ ፣2400፤የኤሌክትሪክ ምድጃዎች ምርትና ስርጭት 300፤የኤሌክትሪክ ምጣድ 114፤የኤሌክትሪክ ምድጃ 186፤የሚሰራጭ ሶላር 2500፤ ላቀች ምድጃ፣18 በቤተሰብና በተቋማት የሚገነቡ የባዩ ጋዝ ማመንጫ የተሻሻሉ የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ስርጭት ለማሰራጨት ታቅዷል፡፡በኢነርጅ ዘረፍ የሚፈጠር የስራ ዕድል በተመለከተ በማገዶ ቆጣቢ 6፤በባዮ ጋዝ ግንባታ 6 በድምሩ 12 የስራ ዕድል ይፈጠራል፡፡

   በገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን በኩል የሚታየውን የመብራት ችግር ለሚመለከተው በትኩረት እንዲሠራ መነጋገር ተገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም በከተሞች የሚታየውን የመብራት ማስፋፋት ችግርና የሚታየውን የማስፈፀም አቅምና የመልካም አስተዳደር ሁኔታ በማሻሻል ውጤታማና ቀልጣፋ የመሬት አስተዳደር እንዲዘረጋ የማድረግ ፣ የከተሞችን የሽግግር አደረጃጀት የማሻሻል ፣ ከተሞች በፕላን እንዲመሩና ግንባታዎች ደረጃቸውን ጠብቀው በጥራት እንዲገነቡ የማድረግ ቀልጣፋና ፍትሃዊ የሆኑ መሠረተ ልማቶች የመዘርጋት እንዲሁም ወጪ ቆጣቢ የቤት ልማት ስራን የማከናወን ፣ በከተሞች ሁለንተናዊ የሆነ ፈጣን ፣ ፍትሃዊና ህብረተሰቡን  ያሳተፈ ዘላቂ ልማት በማረጋገጥ የከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት ለማከናወን ጥረት ተደርጓል ፡፡ ሆኖም ግን የከተማ ነዋሪው ለሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ወቅታዊ ምላሽ በመስጠትና የአገልግሎት አሰጣጡ ተጠያቂነት ያለበት ፣ ሠራተኛው የአገልጋይነት ስሜት የተላበሰና ከኪራይ ሰብሣቢነት የፀዳ በማድረግ በኩል ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ በከተሞች ያለውን ችግር ውስብስብ እና ፈታኝ አድርጎታል ፡፡

2.2.3 ከመሪ ማዘጋጃ አፈፃፀም

በወረዳችን ያሉ ከተሞች 100% በፕላን እንዲመሩ ለማድረግ በእቅድ ተይዞ በወረዳዉ ካሉት 3 ከተሞች ዉስጥ 3ቱም በፕላን የሚመሩ ከተሞች ናቸዉ፡፡ ይህም አፈጻጸሙ 100% ሲሆን የከተማነት እዉቅና ከተሰጣቸዉ ከተሞች መካከል 3ቱ በግልጽ የከተማ ወሰን ለማዘጋጀት ተይዞ 1 የከተማ ወሰን ማዘጋጀት ተችሏል፡፡

ከመሬት ልማት አስተዳደር አኳያ ክፍት ቦታዎችን በአገልግሎት አይነት በመቁጠር፤ለመሪ ማዘጋጃቤቱ ተጠሪ የሆኑት ታዳጊ ከተማ አስተዳደሮች የራሳቸዉ የታወቀ ወሰን እንዲኖራቸዉ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤100% ማከናወን ተችሏል፡፡

ለምደባ የቀረቡ የቤት ስራ ማህበራት 9.7ሄ/ር፤ለኢንዱስትሪ የቀረቡ 1ሄ/ር ሁሉም ከዕቅድ አንፃር >100% ማከናወን ተችሏል፡፡የሰነድ አልባ ይዞታን ማጣራትና 65፤የሊዝ ይዞታን በመለየት ለገቢ ሰብሳቢ መረጃ መስጠት 1 በሰነድ በማከናወን የአመቱን እቅድ 100% መፈፀም ተችሏል፡፡የማይንቀሳቀስ ንብረት ም/ወረቀት ዕቅድ 280 ሲሆን 481 በመፈፀም>100% ማከናወን ተችሏል፡፤ከአረንጓዴ ልማት ስራዎች አንፃር የ4 ነባር ፓርኮች የመንከባከብ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፤

ከመሰረተ ልማት ስራዎች አንፃር የኮብል ወይም ጌጠኛ መንገድ ግንባታ ዕቅድ 0.2 ኪ.ሜ ክንዉን 0.523፤የጠጠር መንገድ ግንባታ ዕቅድ 12.95ኪ/ሜ ክንዉን 13.442፤የመንገድ ከፈታ ስራዎች ዕቅድ 1.445ኪ/ሜ ክንዉን 3.609 በሁሉም >100% በላይ በማከናዎን በአይነቱ ልዩ የሆነ አፈፃፀም ማስመዝገብ ተችሏል፡፤በሂደቱ በርካታ ችግሮች የገጠሙ ቢሆንም ከተማን ከአለባት ችግር ለማላቀቅ በነበረ ቁርጠኝነት ለስኬት ተደርሷል፡፤ የእነዚህ አፈፃፀም በቀጠይ ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባዉና ከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ ተጨምሮበት በወረዳ አስተዳደሩ ድጋፍ የበለጠ ሊሆን የገባዋል፡፡

ከገቢ አሰባሰብ አኳያ 11233306 ለመሰብሰብ ታቅዶ 8610173 በመሰብሰብ የዕቅዱን 76.6% ማከናዎን ተችሏል፡፡

በጥንካሬ የተከናወኑት ተግባራት እንደተጠበቁ በበጀት አመቱ በዉስንነት የታዩ ተግባራት የከተማ መሬት ዝግጅት ለጫረታ ለንግድ እና ለመኖሪያ ያለዉ ዝግጅት 50% ይህም አፈፃፀሙ ዝቅተኛ መሆኑ፡፡የከተማዉ ፅዳት አጠባበቅ ላይ በሽንት ቤት ማስመጠጥ ዉስንነት እና በከተማዉ የትም ተጥለዉ የሚገኙ ደረቅ ቆሻሻ ክምችት በህብረተሰብ ተሳትፎ መስመር መያዝ ካልቻለ ለጤና ችግር መሆኑ አየቀርም፡፡በአረንጓዴ ልማት የህብረተሰብ ተሳትፎ 3.5% መሆኑ ለቀጣይ ስልት ተቀይሶ ሊሻሻል ገበዋል፡፡ከገቢ አሰባሰብ እስካሁን ባለተሰራባቸዉ የገቢ አርሰቶች ላይና ጥሩ ገቢ ሊያስገኙ የሚችሉ ዘርፎች ላይ አተኩሮ ባለመስራት የአፈፃፀም ጉድለት ታይቷል፡፡

2.3.የማህበራዊ ልማት ዘርፍ አፈጻጸም

2.3.1 ትምህርት ዘርፍ

  ትምህርት የሰው ሀይል ልማትን በማፋጠን በተማረ የሰው ሃይል ላይ የተመሠረተ ኢኮኖሚ እንዲገነባ ቁልፍ ሚና አለው ፡፡ በተማረ የሰው ሃይል መር ኢኮኖሚ ዋነኛ መገለጫ ደግሞ በእውቀት የሚመጣ ልማት ፍጥነትና ቀጣይነት አስተማማኝ መሆኑ ነው፡፡በሌላ አገላለጽ በማንኛውም መልኩ ቀጣይነት ያለው ልማት ሊረጋገጥ የሚችለው ደግሞ ኢኮኖሚው የሰው ሀይል ልማት ላይ ትኩረት ሲያደርግ ብቻ ነው ፡፡ ብቃት ያለው የተቀናጀ ሁለገብ የሰው ሃይል በብዛትና በጥራት በማፍራት ከውስን ካፒታል ጋር በማጣመር በቴክኖሎጂ ፈጠራና ሽግግር ፣ በመልካም ተሞክሮና አዳዲስ የፈጠራ ግኝት በማላመድ ረገድ ትምህርት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ፡፡ በመሆኑም ወረዳችን የክልሉ መንግስት አቅጣጫና ከራሱ ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት ለትምህርት መስፋፋት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል ፡፡

ይሁን እንጅ ለትምህርት ጥራት መጓደል ረዘም ያለ ግምገማ ሰዓት ወስዷል፡፡ ለዚህም ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም ዘርፉን ከእድገት አቅጣጫ ወደ ኃላ ከጎተቱትና ጥራቱንና ብቃቱን ከተፈታተኑት መካከል ጥራት ያለው የትምህርት መረጃ መሣሪያዎች እጥረት ፣ የክትትል፣ ቁጥጥርና የግምምገማ ስርዓት በበቂ ሁኔታ አለመዘርጋት ፣ ት/ቤቶች ለመማር ማስተማር ምቹ አለመሆን የሚያስችል ደረጃ ባለመያዛቸው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የራሱን አሉታዊ ጫና ማሣረፍ እንዳለ ሆኖ በዋናነት  ህብረተሰቡን ለትምህርት ያለውን አናሳ ግንዛቤ ለመቅረፍ የተሰራዉ ስራ ዝቅተኛ መሆን ይገኝበታል፡፡

በትምህርት ተሳትፎ ረገድ የትምህርት ሽፋን ተደራሽ በማድረግ ለትምህርት የደረሱ ህጻናትን የቅ/መደበኛናየመሰረታዊ ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ ከተያዘዉ መሰረታዊ አቅጣጫ በ2012 ዓ.ም የቅድመ መደነኛ ትምህርት የትምህርት ተሳትፎ 8709 ለማደረግ ታቅዶ 3639 መፈጸም ተችሏል፡፡በዚህም የሴቶች ተሳትፎ 41.8% ማድረስ ተችሏል፡፡ይህም ከአለፈዉ አመት አፈፃፀም 10% ያንሳል፡፡

   የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ዕቅድ 3023 ተይዞ 3023 በመመዝገብ የዓመቱን ዕቅድ 100% ማሳካሰት የተቻለ ቢሆንም 9.1% የማቋረጥ መጠን በማስተናገድ ችግር ዉስጥ መግባት ችሏል፡፡የከፍተኛ መሰናዶ 2ኛ ደረጃ የበጀት ዓመቱ ዕቅድ 1703 ክንዉን 1703 በመመዝገብ 100% መመዝገብ የተቻለ ቢሆንም 5.2% የማቋረጥ መጠን ተከስቷል፡፡የችግሩ ትክክለኛ ሚንጭ ሊመረመርና መፍትሄ ሊሰጠዉ ይገባል፡፡

በትምህርት ዘመኑ የትምህረትን ጥራት ለማሰጠበቅ በአመቱ መጀመሪያ በሁሉም ክፍል ደረጃ 100% የነፍስ ወከፍ በጀት በመመደብ ማሰራጨት ተችሏል፡፡በጀቱን በመጠቀም ረገድ 2152211 ተመድቦ 993258.32 (46.1%) መሆኑ ያሳያል፡፡

በትምህርት ዘመኑ ክፍተት የታየባቸዉ ከስራ ዘርፎች ዉስጥ ትምህርቱን ተጨባጭ ለማድረግ በቤተ-ሙከራ አስድግፎ የሳይንስ ትምህረትን በተግባር በመስተት የተማሪዎችን ዉጤት ለማሻሻል የተደረገዉ ጥረት አናሳ ነበር፡፡የተግባር ተኮር ጎልማሶች ትምህረትን ከወረዳ አመራር እስከ ቀበሌና ት/ቤት ድረስ የሚመለከታቸዉን ትኩረት ሰጥቶ አለመስራት ታትይቷል፡፤የፕላዝማ ትምህርት አሠጣጥ በግብአት እጥረት እና በፕሮግራም ችግር ወደ ስራ አለመግባት(በሁለቱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የመብራት ችግር) ታክሎበት ከፍተኛ ችግር አለ፡፡የኢንተርኔት ዝርጋታ ወይም መሰረተ ልማት በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች አለመኖር የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማጠናከር አለመቻሉ፤የትምህርት ዉስጣዊ ብቃት አኳያ የንጥር ቅበላ(7 ዓመት የሆናቸዉ የ1ኛ ክፍል ተማሪዎች)65% ላይ መቆሙ አሁንም በእድሜአቸዉ ወደ ት/ቤት መግባት ያለባቸዉ ተማሪዎች በሙሉ አለመግባታቸዉን ያሳያል፡፡ከዚህ በተጨማሪ የእንግሊዝኛ መምህራን እጥረት በከፍተኛ ደረጃ የተከሰተ ሲሆን የመርሱ ከኮሌጅ ጋር ተቀናጅቶ የሀዉ ሃይል ማምረት ወይም ማዘጋጀት ስራ ጉድለት እንደነበረበት ያሳያል፡፡ጥገና ሚያስፈልጋቸዉ ክፍሎች በክረምት ወቅት መጠናቀቅ ሲገባዉ ክፍል የማዘጋጀት ስራ ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን መሄዱ በትምህረቱ አሰጣጥ ላይ ችግር ፈጥሯል፡፡የተወሰኑ ተቋማት ተመደበ በጀትን ለትምህርት ጥራት ሊያመጡ በሚያስችሉ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ከማዋል ይልቅ በዘፈቀደ በመምራት ያላስፈላጊ ብክነት አሳይተዋል፡፡ተጨማሪ ሀብት ፈጥሮ የትምህርት ቁልፍ ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ወደ ላይ መንግስትን አንጋጦ በመጠበቅ የጠባቂነት ችግር በአብዛኛዉ ተጠናዉቶት ይገኛል፡፡ከዚህ በሻገር የተመደበ በጀትንም ቢሆን GEQIP ከብክነት በፀዳ መልኩ ተጠቅሞ ሰነድ ማቅረብ የተሳናቸዉ የት/ቤት አመሮችም ነበሩ፡፡ከሁሉም ችግር ደግሞ የከፋዉ የት/ቤት ገንዘብን የግለሰቦች መጠቀሚያ ማድረግ ምሳሌ፡-የላምገጅ 1ኛ ደረጃ፤የጁቤ መሰናዶ፤አንጅም፤የጁቤ 1ኛ ደረጃ(ሰነድ ባለማቅረብ ለብክነት ማመቻቸት)፤ስራ ታይቷል፡፤በቀጠይ ጥብቅ ቁጥጥር ስራ በመዘርጋት ት/ቤቶችን መታደግ ይገባል፡፡

 

 

 

 

 

 2.3.2.በጤናው ዘርፍ

   በሌላ በኩል በጤናው ዘርፍ የወረዳውን ሕዝብ የጤንነት ደረጃ ለማሻሻል መንግስት ጤና ለሁለንተናዊ የልማት እድገት ያለውን ፋይዳ በመገንዘብ መከላከልን መሠረት አድርጎ የተቀረፀውን የጤና ፓሊሲ ለተግባራዊነቱ በመረባረብ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል ፡፡ ሆኖም ግን  በወሊድና ከወሊድ ጋር በተያያዙ ችግሮች የእናቶችና የህጻናት ሞት በሚፈለገው ደረጃ ያልቀነሰበት ሁኔታ መኖሩን እንዲሁም የጤና ተቋማት ተደራሽነት  እያደገ የመጣ ቢሆንም የሚቀር ስራ ያለው መሆኑን ነባራዊ ሁኔታዎች ያሣያሉ ፡፡ በዚህም መሠረት በገጠሩ ህብረተሰብ ዘንድ የመሠረተ ጤና እንክብካቤ ማስፋፋት አስፈላጊነትን በመገንዘብ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ተዘርግቶ እየተተገበረ ቢገኝም ሁሉም ፓኬጆች በተሟላ መልኩ ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ችግሮች ይሠተዋላሉ ፡፡

 የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት የሚጠበቀዉ የአመት ዕቅድ 35330 ክንዉን 32950 አፈጻጸም 93% ቅድመ ወሊድ፤የወሊድና ድህረ ወሊድ ክትትል እንዲያደርጉ ታቅዶ 4342(74%)፤1923(33%)እና 2278(39%) ነፍሰጡር እናቶችን እነደ ቅደም ተከተል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

2.3.2. የባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች አፈፃፅም

  የሴቶችን በልማቱ የነቃ ተሣትፎ እንዲኖራቸው የማድረግና በኢኮኖሚና በማህበራዊ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል ፡፡ በተጨማሪም የህፃናትን መብትና ደህንናት በማረጋገጥ ዙሪያና ከልማቱ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች በማከናወን ረገድ ጥረቶች ተደርገዋል ፡፡ በተለይ በሴክተር ደረጃ ስርዓተ ፆታን በማካተት ረገድ ለሁሉም ዘርፎች ግንዛቤ በመፍጠር በእቅድ ተካቶ እንዲሠራ ማድረግ ተችሏል ፡፡ ሆኖም ግን የሴቶችንና ህፃናትን መብቶችን ከማረጋገጥ አኳያና በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፓለቲካዊ ሂደቶች የተሟላ ተሣትፎና ተጠቃሚነት ዙሪያ ብዙ የሚቀሩ ስራዎች እንዳሉ ከዘርፎች አፈፃፅም ውጤቶች መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም በሴቶችና ህፃናት እንዲሁም በስርዓተ ፆታ ዙሪያ የታዩ ችግሮችን በየደረጃው ያሉ አመራሮች በመፍታት፣ በመደገፍና በማብቃት ረገድ የሚሰጡት ትኩረት ውስንነት ያለበት መሆኑ፣ በሴክተሮች እቅድ አካቶ አለመተግበር ፣የሴቶች አደረጃጀቶች ጠንካራ አለመሆን፣ በህብረተሰቡ ዘንድ በሴቶችና ህፃናት ላይ ያለው የተዛባ አመለካክት አለመወገዱ በሴቶችና ህፃናት በልማት ተሣታፊነትና ተጠቃሚነት ዙሪያ ተጽፅኖ እያሳደሩ ያሉ መሠረታዊ ችግሮች ናቸው ፡፡ እነዚህን ችግሮች በመፍታት ሴቶችንና ህፃናትን በልማቱ ማሣተፍ በወረዳዉ ልማት ላይ አይነተኛ ለውጥ ማምጣት ያስችላል ፡፡ ይኸውም ሴቶች ከግማሽ በላይ የልማት ሃይል በመሆናቸው ችግሮቻቸውን መፍታት የግድ ይላል ፡፡

  በሌላ በኩል ወጣቶች ወረዳ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፓለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚኖራቸውን ሚና ለማሳደግ አደረጃጀቶቻቸውን በማጠናከርና በተለያዩ የልማት ዘርፎች የስራ ስምሪት ውስጥ በመግባት፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በክረምትና በበጋ በመሳተፍ ለወረዳዉ ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥረቶች ተደርገዋል ፡፡ በክልሉ ስነ ህዝብ መረጃ መሠረት በወጣት የእድሜ ክልል የሚገኘው ወጣት በአመዛኙ ከፍተኛውን ቁጥር የሚወስድ ስለሆነ ይህንን ሃይል በልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ማሳተፍ ካልተቻለ አሉታዊ ጎኑ ከፍተኛ ሊሆን ስለሚችል በልዩ ትኩረት ወጣቱን ወደ ስራ የማስገባትና ከልማቱ ተጠቃሚ የማድረግ ስራዎችን በተጠናከረ መልኩ መስራትን ይጠይቃል፡፡ምንም እንኳን ወጣቱ ከአልባሌ ቦታዎች እንዲርቅና ከአጓጉል ሱሶች ርቆ ጤናው የተጠበቀ ዜጋ እንዲሆን የስፓርት ማዘውተሪያ ስፋራዎችንና የወጣት ማዕከላትን በመገንባት ተጠቃሚ ለማድረግ ጥረቶች የተደረጉ ቢሆንም አሁንም ወረዳው ወጣቶች በልማት ተሣታፊነትና ከልማቱ ተጠቃሚነታቸውን በተሟላ መልኩ ማረጋገጥ አልተቻለም ፡፡ በመሆኑም የወጣቶችን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ችግሮችን በመፍታት አደረጃጃቶቻቸውን በማጠናከር ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ ሂደት በየደረጃው ባሉ አመራሮች፣ ፈፃሚ ባለሙያ እና ህብረተሰብ ዘንድ የሚስተዋሉ የአመለካክት ችግሮች እንዲፈቱ ማድረግ ይገባል፡፡

  የህዝብ ብዛት ፈተናዎችንም ሆነ እድሎችን ይዞ የሚመጣ ጉዳዩ ነው፡፡ በአንድ በኩል እያደገ ያለ ህዝብ በወጣቶች የተሞላና በበቂ ሁኔታ የሚገኝ ሰራተኛ ማህበረሰብ እንዲፈጠር የሚያደርግ ሲሆን በተጨማሪ በሀገር ውስጥ የተመረቱ ምረቶችን ሊገዛ የሚችል ሰፊ የሀገር ውስጥ የገበያ እድሎችን ይፈጥራል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ደካማ አቅም ላለው ሀገር እንደ ሆስፒታል፣ ትምህርት ቤት ትራንስፓርት ፣ መኖሪያ ቤት የመሳሰሉት በቂ መሰረተ ልማቶች በሌሉበት ሁኔታ በህዝብ አገልግሎት ተቋማት ላይ ጫናን ያሣድራል ፡፡ በመሆኑም ከስነ ህዝብና ልማት ጋር ተያይዘው የሚሰሩ ተግባራት መልካም ዕድሎችን አሟጦ በመጠቀም ፈተናዎችን የሚቀርፉ መሆን ይኖርባቸዋል ፡፡ ስለሆነም የሚመለከተው አካል ሁሉ በጉዳዩ ላይ አልሞ መስራት ይጠበቅበታል ፡፡

    2.4. ዴምክራሲንና መልካም አስተዳደርን የማስፈን አፈፃፀም

   የዴሞክራሲያዊ ስረዓትን በአገር ብሎም በክልል ደረጃ መገንባት ከክልሉ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ወሣኝ ጉዳይ ነው ፡፡ በመሆኑም ልማትን ለማረጋገጥ ቀዳሚው መስፈርት ተደርጎ ተወስዷል ፡፡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገትን ማስመዝገብ፣ መልካም አስተዳደርን ማስፈን እና ብልሹ አሠራሮችን ማስወገድ እንዲሁም የሚፈጠሩትን ወቅታዊ ችግሮች በሰለጠነ መንገድ መፍታት ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መሠረታዊ ጉዳዮች አድርጎ መውሰድ ይቻላል ፡፡ በመሆኑም የህዝብ ተመራጮችን አቅምና የህዝብ ቀጥተኛ ተሣትፎን የማጎልበትና የተደራጀ የህዝብ እንቅስቃሴ የማጠናከር እንዲሁም የዴሞክራሲ ባህልን ለማጎልበት የሚያስችሉ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል ፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን የወረዳዉ ነዋሪዎች ለማህበራዊ እድገት እንዲነሳሱ በማድረግ የማህበራዊ ተሣትፎአቸውን በማሳደግ መብትና ግዴታቸውን በማክበር ፣ የግልጽነትና የመቻቻል እሴቶችን በማጎልበት ለዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ መዳበር ሠፊ ስራዎችን ለማከናወን ጥረት ተደርጓል ፡፡ ይኸውም የወረዳዉን ህብረተሰብ ለስብዓዊ መብቶችና መሠረታዊ ነፃነቶች እንዲሁም ስለ ህግ እውቀት እንዲኖረው የማድረግና ጠንካራ የፍትህ ስርዓት መዘርጋት የሚያስችል የፍትህ አቅም ግንባታ ስራዎች በማከናወን በህብረተሰብ ጥራት ያለው ፍትህ እንዲያገኝ አገልግሎቱን ለማሻሻል የሚያስችሉ ስራዎች ተከናውነዋል ፡፡

   በሌላ በኩል ለመልካም አስተዳደር መጓደል መንስኤ የሆነውን ኪራይ ሰብሣቢነት በማዳከም የልማታዊ ፓለቲካል ኢኮኖሚ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚስችሉ ስራዎችን ለማከናወን ወደ ተግባር እንቅስቃሴ ተገብቶ ነበር፡፡ በበጀት ዓመቱ የኪራይ ሠብሳቢነት ችግር የሚታይባቸውን የግዢ፣ የመሬት አስተዳደር ፣ ግብር አሰባሰብ እንዲሁም የኮንትራት አስተዳደር ሌሎች የስራ መስኮች ላይ በተደራጀ የህዝብ ተሣትፎ ችግሮችን ለመለየትና ለመፍታት ጥረቶች ተደርገዋል፡፡የህግ የበላይነትን ለማስፈንና ተጠያቂነትንና ግልጸኝነትን ለማጎልበት በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡

2.5.የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ግንባታ አፈፃፅም

  ወረዳችን ፈጣን ልማትና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ቀጣይነትና ውጤታማነት ለማረጋገጥ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ግንባታ የማያቋርጥ ስራ በመሆኑ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በማስቀመጥ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተገብቷል ፡፡ የመፈፀም አቅም  ግንባታ ሲባል ለተልዕኮው ብቁ የሆነ የሰው ኃይል ፣ አደረጃጀት እና አሰራር መኖር ማለት ሲሆን የማስፈጸም አቅም ግንባታ የሚያጠነጥነው በሰው ሃይል ልማት ላይ ሆኖ ይህም በአመለካክት፣ ክህሎት፣ አሠራር ፣ አደረጃጀት እና ግብዓት በማሟላት ላይ የተመሠረተ ነው ፡፡ የዴሞክራሲያዊ ስርኣት ግንባታም ሆነ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ግለቱን ጠብቆ እንዲቀጥል ለማድረግ የሚቻለው ኪራይ ሰብሣቢነት ከምንጩ እያደረቀ ልማታዊነት የበላይነቱን እየጨበጠ መሄድ ሲችል ነው ፡፡ ይህን እውን ማድረግ የሚቻለው በመንግስት መዋቅር ውስጥ የተሟሟቀና የተደራጀ የልማታዊነትና የፀረ- ኪራይ ሠብሣቢነት ትግል በሕዝቡ የተደራጀ ተሣትፎ ማቀጣጠልና ማስቀጠል ሲቻል ብቻ ነው፡፡ በዚህም መሠረት በሲቪል ሰርቪሱ የሚታዩትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታትና ከወቅታዊ የፓለቲካ ሁኔታው ላይ ያሉበትን ብዥታዎች በማስወገድ በክልሉ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና ልማት እንቅስቃሴ ውስጥ የሚኖረውን ድርሻ ለማሳደግና ብልሹ አሠራሮችን እንዲታገልና የወረዳውን ሰላም የሚያናጉ እንቅስቃሴዎች በያለበት የስራ መስክ መታገል እንዲችል በተጀመረው የለዉጥ እንቅስቃሴ እንዲያልፍ በማድረግ የትግሉ አጋር አካል ለማድረግ ጥረት ተደርጓል፡፡

የለውጥ ስራው የፓለቲካ አመራሩን ቁርጠኝነትና የህዝብ ተሣትፎ ባለቤትነት ወሣኝ መሰረታዊ አቅጣጫን በመከተል የሚፈጸም መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በክልሉ የመንግስት ተቋማት የለውጥ ተግባራት ሁሉንም የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ወጥነት ባለው መልኩ መፈፀም የሚያስችል አሰራርና አደረጃጀት ሊኖር ይገባል፡፡

    በአጠቃላይ የወረዳው የልማት እቅዶች ውጤታማ ተፈፃሚነት የሚረጋገጠው በስኬታማ የማስፈጸም አቅም ግንባታ ስትራቴጂ ትግበራ ላይ በመሆኑ ከ2008 አስከ 2012 የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈፃፅም ዓመታት ያላሳካናቸውን የልማት ስራዎች በተለይ የግብርና ልማት ስራችን እንዲሁም የቀጣይ በጀት ዓመት የቀጣይ ስተራቴጅክ ዕቅድ የመጀመሪያ ዓመት  በመሆኑ የተያዘውን እቅድ በተሟላ መልኩ ለማሣካት  የመስፈፀም አቅም ግንባታ ስትራቴጂዎችን ልዩ ትኩረት በመስጠት መተግበር የግድ ይላል ፡፡