መጽሐት

       የባ/ሊ/ወ/ጽ/ቤት ፕላን ኮሚሽን መጽሔት

   በባሶ ሊበን ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት  ውስጥ አንዱ የሆነው የፕላን ኮምሽን የስራ ሂደት የስነ ህዝብ ጉዳይ ዘርፍን በውስጡ ያካተተ በመሆኑ የስነ ህዝብ ጉዳይ ተግባራትንም ያስተባብራል፡፡ ከዚህ አንፃር የተለያዩ ስነ ህዝባዊ በራሪ ጽሁፎችን፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ማኑዋሎችን፣ መጽሄቶችም እንዲሁም የስነ ህዝብና ልማት መረጃዎችን ወዘተ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት የስነ ህዝብ ጉዳይን በልማት እቅዶች ውስጥ ለማካተት እና የስነ ህዝብ ትምህርታዊ ቅስቀሳ ተግባራትን ለማከናወን ይረዳ ዘንድ ይህን የስነ ህዝብ መጽሄት አዘጋጅተናል፡፡

 

        2.የመጽሄቱ ዋና አላማ፡-

  1. በሁሉም ት/ቤቶች ስነ ህዝብ ክበብ አባላት በስነ ህዝብ ዙሪያ ተቀራራቢ የሆነ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ
  1. በስነ ህዝብ ዙሪያ በሁሉም ተቋማት የተደራጀ የስነ ህዝብ መረጃ፣ የእቅድ      አስተቃቀድ፣ እንዲሁም የሪፖርት ዝግጅት እንዲኖር ለማስቻልና በአጠቃላይ ግልጽና ወጥነት ያለው አሰራር ለማጐልበት
  1. የስነ-ህዝብ ፖሊሲዎችን፣ አዋጆችንና መመሪያዎችን የተከተለ አሠራር እንዲኖር ለማስቻል፡፡
  1. ለዚህም የፕላን ኮምሽን የስራ ሂደት ለሁሉም ተቋማት ከተልዕኮና ራዕይአቸው አንጻር የሚያከናውኗቸውን የስነ ህዝብ ጉዳይ ተግባራት በመለየት  በአሠራሩ ዙሪያ እጥረት ለታየባቸው መስሪያ ቤቶች ክፍተቱን  ለመሙላት ጥረት ያደርጋል፡፡

         3.ያዘጋጁ መልዕክት

 

   በአገራችን የወሊድና የሞት መጠንን በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ በማድረግ በህዝቡ የዕድሜ ስብጥር ላይ ለውጥ ማምጣትና ዲሞግራፊያዊ ሽግግርን እውን ማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት ሊተገበር የሚገባው ዋነኛ ጉዳይ ነው፡፡

  • የስነ ህዝብ ጉዳዮች በባህሪያቸው የተለያዩ መ/ቤቶችን የተቀናጀ ተሳትፎ የሚጠይቁ ናቸው፡፡ በስነ ህዝብ ፖሊሲ ሰነዱ ውስጥ በግልፅ እንደተቀመጠው የሚመለከታቸው ሴ/መ/ቤቶች የስነ ህዝብ ጉዳዮችን በልማት ዕቅዶቻቸው ውስጥ አካተው እንዲተገብሩ ይጠበቃል፡፡ ለዚሁ ተግባር የሚረዳና የስነ ህዝብ ፖሊሲውን አፈጻጸም ለማስተባበር የሚችል የስነ ህዝብ ምክር ቤት በሁሉም ደረጃ ማቋቋም በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ዪታመናል፡፡ አሁን በስነ ህዝብና ልማት ዙሪያ የተመዘገቡት አበረታች ውጤቶች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማስቻል ይህንን የማስተባበሪያ አካል በአዋጁ መሰረት እንዲቋቋም ማድረግ የተለየ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው፡፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ዛሬም እጅግ በርካታ እናቶች በህክምና ተቋማት የባለሙያ እርዳታ እያገኙ ሳይሆን በቤታቸው ልጆቻቸውን ይወልዳሉ፡፡ ይህም ከወሊድ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ የእናቶችና ህጻናት ሞት መጠንን በመቀነስ የምዕተ ዓመቱን ግብ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳርፋል፡፡ በመሆኑም እናቶች ተገቢውን የቅድመ ወሊድ ክትትል በህክምና ተቋማት እንዲያደርጉ፣ በባለሙያ እገዛ በጤና ተቋማት ውስጥ እንዲወልዱና አስፈላጊውን የድህረ ወሊድ ክትትል እንዲያገኙ አሁን ከሚደረገው በላይ ሁሉንም ተደራሽ ሊያደርግ የሚችል ሰፊ የስነ ህዝብ ስራ በየደረጃው መከናወን ይኖርበታል፡፡ በቅርቡ የተካሄደው የስነ ህዝብና ጤና ጥናት እንደሚያመለክተው የቤተሰብ ዕቅድ መጠቀም እየፈለጉ በተለያዩ ምክንያቶች መጠቀም ያልቻሉ ያገቡ ሴቶች 25 በመቶ ያህል ይደርሳል፡፡ ይህንን ያልተሟላ የቤተሰብ ዕቅድ ፍላጎት በማሟላት ወላጆች የሚፈልጓቸውን ያህል ልጆች በሚፈልጉት የጊዜ እርቀት መውለድ እንዲችሉ ማድረግ እንዲሁም በፍላጎት ላይ የተመሰረተ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ማክበር ጭምር ነው፡፡
  • በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ አሁን የሚታየውን ያልተሟላ የቤተሰብ ዕቅድ ፍላጎት ለማሟላት ተገቢውን ሁሉ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • የሥነ ህዝብ ጉዳዮች በአንድ አገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ሥነ ህዝባዊ ጉዳዮች ሳቢያ ሊከሰቱ በሚገመቱ የሕዝብ ችግሮች ስፋት ይወሰናሉ፡፡ እንደ ችግሮች መጠንም አግባብ ያላቸው የሥነህዝብ ጉዳዮች በልማት ዕቅዶች ውስጥ እንዲካተቱ ማድረግ ይገባል፡፡ በተቋማት መካከል በዕቅድ አስተቃቀድና አፈጻጸም ወቅት በጋራ የተሳሰረና የተቀናጀ የአሰራር አግባብ  ሲኖር የሚፈለገው ግብ ላይ እንዲደረስ ወሳኝ ይሆናል፡፡ የግንኙነት ሰንሰለቱም ከተቻለ ታች እስካለው ተጠቃሚ ማህበረሰብ (target Population) ድረስ የተዘረጋ ቢሆን ይመረጣል፡፡ በየወቅቱ የሚለዋወጡ የስነ ህዝብ ጉዳዮች አንፃርም አሠራሩና የዕቅድ አፈፃፀሙ ተጣጥሞ የሚካሄድበትን አግባባዊ አሠራር መፍጠር ይገባል፡፡
    በአጠቃላይ የስነ ህዝብ ጉዳይ የሁሉንም ሴክተሮች ትኩረትና እርብርብ የሚሻ በመሆኑ ኃላፊነታችንን እንወጣ ዘንድ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

 

 

 

የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትና የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች

 የቤተሰብ እቅድ ምጣኔ ማለት ጥንዶች ጋብቻ ከመፈጸማቸው በፊትም ሆነ በኋላ ሊኖሯቸው የሚገባቸውን ልጆች ከአላቸው ገቢ መጠን ወይም ልጆችን የማሳደግ አቅም ጋር በማመጣጠን የሚወስኑበት ዘዴ ነው፡፡ የህዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የህዝቡ የኑሮ ደረጃ ዝቅ እያለና ውስብስብ እየሆነ ነው፡፡ ስለሆነም ይህንን ውስብስብ የኑሮ ሁኔታ ለመፍታትና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት ቤተሰብን በመመጠን እና አቅምን ባገናዘበ መልኩ አራርቆ መውለድ ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የተለያዩ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎቶችንና ፕሮግራሞችን ማስፋፋትና የተጠቃሚዎችን ቁጥር ማሳደግ አስፈላጊ ነው፡፡ የቤተሰብ እቅድ ፕሮግራም በ1960ዎቹ የተጀመረ ሲሆን ዓላማውም የልጆቻቸውን ቁጥር መወሰን ለሚፈልጉ ጥንዶች ዘመናዊ የእርግዝና መቆጣጠሪያ ዘዴዎችን ማቅረብ እና እንዲጠቀሙ ማድረግ ነው፡፡ ፡፡

በባሶ ሊበን ወረዳም የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዳበረ እና የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ቁጥርም እየጨመረ የመጣ ሲሆን ነገር ግን  ካለው የህዝብ ቁጥር መጠንና ከኢኮኖሚ አቅም ጋር ሲነፃፀር  ብዙ የሚቀሩ የስነ ህዝብ ስራዎች የአሉ መሆኑ መገንዘብ ይቻላል፡፡ አሁንም አገልግሎቱን መጠቀምና መስጠት ላይ በዘርፉ ከፍተኛ ክፍተት የሚታይ መሆኑን እና ወጥነትና ቀጣይነት ያለው የስነ ተዋልዶ ጤና ስራና የስነ ህዝብ የመረጃ ስርዓት በተጠናከረ መልኩ እንድናካሂድ መንገድ የሚያሳይ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡የህዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የህዝቡ የኑሮ ደረጃ ዝቅ እያለና ውስብስብ እየሆነ ነው፡፡ ስለሆነም ይህንን ውስብስብ የኑሮ ሁኔታ ለመፍታትና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት ቤተሰብን በእቅድ በመምራት መመጠን እና አቅምን ባገናዘበ መልኩ አራርቆ መውለድ ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የተለያዩ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎቶችንና ፕሮግራሞችን ማስፋፋትና የተጠቃሚዎችን ቁጥር ማሳደግ ተገቢ ነው፡፡

 

 

 የእርግዝና መቆጣጠሪያ ዘዴዎች

              የእርግዝና  መከላከያ  ዘዴዎች  በሶስት  ይከፈላሉ

  • ተፈጥሯዊ (ልማዳዊ) የእርግዝና መከላከያ   ዘዴ
  • ዘመናዊ የእርግዝና መከላከያ   ዘዴ
  • ቋሚ (በቀዶ ህክምና  የማምከን) ዘዴ ናቸው፡፡
    • ተፈጥሯዊ ወይም ልማዳዊ ዘዴዎች፡-
  • በቀን መቁጠሪያ ዘዴ፡- በመውለጃ እድሜ ውስጥ የሚገኙ  ሴቶች መዳኒቶችን ሳይወስዱ  የወር አበባ  ኡደትን  በጥንቃቄ በመከታተል  እርግዝናን መከላከል ይቻላል፡፡ አብዛኛውን  ጊዜ  አንዲት ሴት  እንቁላል የምታኮርተው ከሚቀጥለው  የወር አበባ  መምጫ 14 ቀናት ቀደም ብሎ  በመሆኑ   ሴትዮዋ  የዘር ፍሬ  ለማመንጨት  ከምትችልበት ጊዜ 5 ቀናት በፊት እና በኋላ  የግብረ ስጋ  ግንኙነት  ከመፈፀም  በመታቀብ እርግዝናን መከላከል ይቻላል፡፡
  • የሰውነት ሙቀትን በመለካት /በመቆጣጠር፡-አንዲት ሴት የዘር  ፍሬ በምንታመነጭበት  ወቅት የሰውነት  ሙቀቷ ከወትሮው ከፍ ይላል፡፡  እዳትፀንስ  ስትፈልግ  በቴርሞ ሜትር  በመለካት  የዘር ፍሬ  ልታመነጭ  ወይም የሰውነት  ሙቀቷ  ከፍ ሊል  ከሚችልባቸው  5ቀናት  በፊትና 5 ቀናት  በኋላ  የግብረ ስጋ ግንኙነት  ከመፈፀም  መታቀብ አለባት፡፡ 
  • የማህፀን ፈሳሽን ልዩ ጠባይ በማጤን፡- ከማህፀን  የሚዎጣው  ፈሳሽ የዘር ፍሬ  ከምታመነጭባቸው  ጥቂት ቀናት  በፊት ጀምሮ  መልኩንና ይዘቱን  ይለውጣል፡፡  ሴትየዋ  እነዚህ  ለውጦች  በየወሩ  የሚከሰቱባቸውን  ቀናት አስቀድማ በማጤን   ለውጦቹ ከሚከሰቱባቸው 5 ቀናት በፊትና 5ቀናት በኋላ  የግብረ ስጋ ግንኙነት ከመፈፀም  መታቀብ ይኖርባታል፡፡ 
  • የእናትን ጡት በማጥባት እርግዝና  የሚከሰትበትን  ጊዜ ማራዘም
  • በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የወንዱ ነባዘር ወደ ማህጸን ከመግባቱ በፊት ብልትን በማውጣት የወንድ ዘርን ከሴቷ ብልት ውጭ የማፍሰስ ዘዴን ናቸው፡፡ እነዚህ ልማዳዊ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች አስተማማኝ ባለመሆናቸው ጥቅም ላይ እንዲውሉ አይመከርም፡፡
    • ዘመናዊ መከላከያ ዘዴዎች፡-

በዓማራጭነት የቀረቡ የተለያዩ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች ሲኖሩ እነዚህም ባለ ንጥረ ቅመም (ሆርሞናል) ዘዴዎች ውስጥ በመርፌ የሚሰጥ መከላከያ፣ የሚዋጥ እንክብል እና በክንድ የሚቀበር የእርግዝና መከላከያ እንዲሁም የሴትና የወንድ ቋሚ የእርግዝና መከላከያ፣ ሉፕና ሌሎች የመቆጣጠሪያ ዘዴዎችን ለምሳሌ የወንድና የሴት ኮንዶም፣ ዲያፍራም እንዲሁም በቅባት ወይም በአረፋ መልክ የተዘጋጁ ፀረ-ነባዘር ኬሚካሎችን ያጠቃልላል፡፡

የሚዋጥ  ክኒን (ፒልስ)፡- በአብዛኛው ሴቶች እንደ ዋነኛ  የእርግዝና መከላከያ  ዘዴ አድርገው  የሚጠቀሙበት ሲሆን  ማንኛውም ሴት  ይህንን ዘዴ   ከመጠቀማቸው በፊት  ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

የእርግዝና መከላከያ  ክኒኑ በአብዛኛው የሚዘጋጀው  በአንድ ፓኬት  ውስጥ 21 ነጭ ወይም ቢጫ  እንክብሎችና 7ቀለማቸው የተለየ ቡናማ መልክ ያላቸው  እንክብሎችን  የሚያካትት ሲሆን ዋናዎቹ  እርግዝና  የሚከላከሉት 21 ክኒኖች ካለቁ በኋላ  የወር  አበባ  እስከሚመጣበት  ጊዜ  መዘናጋት እንዳይኖር ሰባቱ  ክኒኖች  ይወሰዳሉ፡፡  የወሊድ  መከላከያ  ክኒኖች የወር አበባ ከመጣበት  ቀን ጀምሮ  ግብረ ስጋ  ግንኙነት  ኖረም  አልኖረም  ያለማቋረጥ  በየቀኑ መወሰድ አለባቸው፡፡

  • በመርፌ የሚሰጥ  የእርግዝና  መከላከያ ዘዴ፡- የተለያዩ  የአገልግሎት  አይነቶች አሉት፡፡ ለአንድ ወር፣ ለሁለት ወር ለሶስት ወር እና ለ6 ወር የሚያገለግል  ሆኖ  የተዘጋጀ ነው፡፡

ይህ ዘዴ እርግዝና እንዳይከሰት  የሚያደርገውም  እንቁላል ከከረጢቱ  አኩርቶ እንዳይወጣ  በማድረግ፣ ማህፀን በር ላይ  የሚገኘውን  ተፈጥሯዊ  ፈሳሽ በማለድለድና  በማወፈር  የወንድ  የዘር ፍሬ  ወደ ማህፀን   ዘልቆ  እንዳያልፍ  በማድረግና የማህፀን ግድግዳ  የተፈጥሮ ፈሳሽን  በመቀየር ነው፡፡

  • ኖርፕላንት፡- አስተማማኝና ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል  በሴቷ የግራ ክንድ ጡንቻ  ላይ በመቅበር  ጥቅም ላይ  የሚውል  መከላከያ ዘዴ ነው፡፡ ለስላሳ ከሆነ ጎማ ነክ ጥሬ  እቃ የተዘጋጀ  6 ቀጫጭንና የሚተጣጠፉ  የክብሪት  እንጨት  መጠን  ያላቸው  ጥቅሎች  ከሴቷ የላይኛው  ጡንቻ  በውስጥ በኩል  ይቀበራል፡፡ ከዚያም ያለማቋረጥ  ሆርሞን በሴትዮዋ  ሰውነት  ስለሚያስተላልፍ   በየወሩ  እንቁላል  አኩርታ  እንዳትወጣ  ያግዳል፡፡
  • ኖርፕላንት በክንድ ከተቀበረ ጀምሮ ለ3፣ ለ5 እንዲሁም ለ12 ዓመታት ያህል ሴትዮዋ እንዳትፀንስ  ያደርጋል፡፡
  • ሉፕ (IUCD) በማህፀን ውስጥ የሚቀመጥ  የወሊድ  መከላከያ  ዘዴ  ሲሆን ከማይዝግና ከማይበላሽ  ፕላስቲክና  መዳብ   ጥምዝ  የተሰራ እና ልዩ ልዩ  ቅርጾች ያሉት  እንዲሁም  ከመዳኒት  ጋር የተቀመመ መከላከያ ነው፡፡

ሉፕ በማህፀን  ውስጥ  ሲቀመጥ የወንድ  ዘር ወደ ማህፀን  ዘልቆ  ከሴቷ  የዘር ፍሬ  እንዳይገናኝ  በማድረግ  እርግዝናን  ይከላከላል፡፡ 

  • ኮንዶም፡- ስስ ከሆነ ፕላስቲክ የተሰራ  ሲሆን  የግብረ ስጋ ግንኙነት ከመደረጉ በፊት  በደንብ በቆመ  የወንድ ብልት ላይ በማጥለቅ  የወንድ  የዘር ፍሬ  ወደ ሴቷ  ብልት  እንዳይፈስ  ወይም እንዳይገባ በማድረግ  እርግዝናን ይከላከላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ  በአግባቡ  ከተጠቀሙበት ኮንዶም  ኤች.አይቪ ኤድስን ጨምሮ ሌሎች የአባላዘር በሽታዎችን  ይከላከላል፡፡ ኮንዶምን በቀዝቃዛ፣ ደረቅና ተስማሚ  በሆነ ስፍራ  ማስቀመጥ  ያስፈልጋል፡፡
  • ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ፡- የምንላቸው ምንም አይነት የእርግዝና መከላከያ ሳይጠቀሙ በድንገት ከሚፈጸም የግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ ወዲያውኑ እርግዝናንለመከላከል የምንጠቀምባቸው ዘዴዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ዘዴዎች ፅንስን ለማቋረጥ እንጂ በግብረ- ስጋ ግንኙነት ወቅት የሚመጡ በሽታዎችን ለመከላከል አይረዱም፡፡

ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ክኒኖች፡- እንደ እርግዝና መከላከያ ንጥረ ቅመም (ሆርሞን) ሲሆኑ ነገር ግን መጠናቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ በድንገት ያለ እርግዝና መከላከያ የግብረ ስጋ ግንኙነት ከተፈጸመ እስከ 72 ሠዓታት ባለ ጊዜ ውስጥ ከተወሰደ ብቻ ከ60% እስከ 90% ድረስ እርግዝናን ይከላከላሉ፡፡

   ከ3 ቀን ባለፈ ወይም ጽንስ ወደ ማህጸን ተጉዞ በማህጸን ውስጥ መኖር ከጀመረ    በኋላ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ መድሃኒቶች እርግዝናውን አያቋርጡትም፤ በመሆኑም እርግዝናው እድገቱን ይቀጥላል፡፡ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እንክብሎች ያልታሰበ ድንገተኛ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ብቻ ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው፡፡ ለምሳሌ የእርግዝና መከላከያ ካልተጠቀሙ ወይም እንደ ኮንዶም ያለ የእርግዝና መከላከያ በሚቀደድበት ጊዜ ወይም አስገድዶ መድፈር ሲፈጸም እንጂ እንደ ቋሚ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ አያገለግሉም፡፡

  • በቀዶ ህክምና  በማምከን  እርግዝናን የመከላከያ ዘዴ
  • የወንድ የዘር ፍሬ ማምከን ፡-በቀዶ ጥገና ወንዶችን ማምከን  ተጨማሪ  ልጆች  እንዳይኖራቸው ወይም  መውለድ  ለማይፈልጉ  ወንዶች  የሚጠቅም ዘላቂ  የሆነ  የመከላከያ  ዘዴ ነው፡፡ ይህ ቋሚ ዘዴ ቀላል በሆነ የቀዶ ጥገና በሙያው ልዩ ስልጠና  ባላቸው  ሃኪሞች  አማካኝነት  የሚሰራ ሲሆን የወንድ  የዘር ፍሬ  የመተላለፊያ  ቱቦ  በመቁረጥና በመቋጠር  የዘር ፍሬውን  ወደ ሴቷ  ብልት እንዳይተላለፍ  የሚያደርግ ዘዴ ነው፡፡
  • የሴቶችን የማህፀን ቱቦ ማስቋጠር፡- በቀዶ ጥገና ሴቶችን ማምከን ተጨማሪ ልጆች  እንዲኖራቸው ወይም መውለድ ለማይፈልጉ ሴቶች የሚጠቅም ዘላቂ የሆነ የመከላከያ ዘዴ ነው፡፡
  • በአጠቃላይ በወረዳችንም ልክ እንደ ሌሎቹ የክልላችን አካባቢዎች በመርፌ የሚሰጥ የመከላከያ ዘዴ በስፋት አገልግሎት ላይ በመዋል የታወቀ ነው፡፡ ከዚህም በመቀጠል በኪኒን ወይም በእንክብል መልክ በአፍ የሚዋጥ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ በሁለተኛ ደረጃ ይታወቃል፡፡ የትኛውም የእርግዝና መከላከያ መቶ በመቶ እርግዝናን አይከላከልም፡፡ በጣም አስተማማኝ የሚባሉት በተጠቃሚው ባህሪይ ላይ የማይወሰኑት ናቸው፡፡ ይሄውም የረጅም ጊዜ የእርግዝና መከላከያ እንደ ሉፕ፣ በክንድ ውስጥ የሚቀበር (ኢምፕላንት) እንዲሁም የወንድና የሴት ዘላቂ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች (ስትራላይዜሽን) የሚያጠቃልል ሲሆን በአስተማማኝነታቸው ደረጃ ዝቅ የሚሉት ደግሞ ከላይ የተጠቀሱትና በተጠቃሚው ባህሪና በሚያደርገው ጥንቃቄ ላይ የሚመሰረቱትን ያጠቃልላል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

  1. የህዝብ ቁጥር እድገትና የውልደት መጠን

በአለፉት ጊዜያት በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ አካላት የወሊድ መጠንን ለመቀነስ በተደረጉ ጥረቶች የወረዳችን ህዝብ ቁጥር እድገት ምጣኔው በተለይ በገጠር አካባቢዎች መቀነስ ቢያሳይም የህዝብ ቁጥር ብዛቱ ግን እየጨመረ ነው፡፡ በ1999 ዓ.ም በተደረገው የህዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት መሰረት የወረዳዋ ህዝብ ብዛት 138332 የነበረ ሲሆን በ2012 ዓ.ም ወደ 170387 ከፍ ማለቱን መገንዘብ ይቻላል፡፡

የስነ ህዝብና ልማትን በተለይ ደግሞ የአነስተኛ ቤተሰብ ቁጥር እሳቤን ለማስረፅ ባለፉት አመታት በርካታ ተግባራት በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ አካላት እንዲሁም በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች አማካይነት  ተከናውነዋል፡፡ ነገር ግን ገና የሚፈለገው ያህል የአስተሳሰብና የባህሪ ለውጥ አልመጣም፡፡ ስለ ቤተሰብ ዕቅድ ግንዛቤ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎቱን ከሚያገኙት ጋር ሲታይ ሰፊ ልዩነት የሚታይባቸው ናቸው፡፡በመሆኑም የአስተሳሰብና የባህሪ ለውጥ ለማምጣት  እንዲቻል በተለይ በሴቶች ትምህርት፣ በህብረተሰቡ ዘንድ ለዘመናት በኖሩት ልማዳዊ አስተሳሰቦች እንዲሁም የቤተሰብ ዕቅድ ከመጠቀም ጋር ተያይዞ በሚነገሩ የተሳሳቱ አባባሎች ዙሪያ ብዙ መስራት ይጠበቃል፡፡ የሴቶችን ሁለንተናዊ ብቃት ማሳደግ ደግሞ ሴቶች የተዋልዶ ጤና መብታቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙበት ለማድረግና የስነ ህዝብ ፖሊሲውን ግብ ለማሳካት ከፍተኛ ድርሻ አለው፡፡ በዚህ ረገድ ሴቶችን ማስተማር የሚኖረው ፋይዳ ትልቅ ነው፡፡ እንደሚታወቀው በአገራችን ለአለፉት በርካታ ዓመታት በነበሩት ጥቂት የትምህርት እድሎች ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ይበልጥ ተጠቃሚ ነበሩ፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለው የትምህርት ፖሊሲ ለሴቶች ትምህርት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠቱ የሴቶች የትምህርት ተሳትፎ በሁሉም የትምህርት እርከኖች ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳየ መጥቷል፡፡ ሴቶች በተለይም ልጃገረዶች በትምህርት ገበታ ላይ ረዝም ያለ ጊዜ በቆዩ መጠን ቶሎ ወደ ጋብቻ ህይወትና ወደ ልጅ መውለድ የሚያመሩበትን ሁኔታ በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተማሩ ሴቶች የአነስተኛ ቁጥር ቤተሰብን ጠቀሜታና የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን በተመለከተ በቂ መረጃና ግንዛቤ ስለሚኖራቸው የሚወልዷቸውን ልጆች መጠንና በምን ያህል የጊዜ ልዩነት ልጆቻቸውን መውለድ እንደሚኖርባቸው የመወሰን ብቃት ይኖራቸዋል፡፡ ይህም በአጠቃላይ የወሊድ መጠን ላይ እንዲሁም በእናቶችና በህፃናት ጤና መሻሻል ረገድ የላቀ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ በዚህ ረገድ ባለፉት ዓመታት በተደረጉ ጥረቶች በመጀመሪያ ደረጃ የወንዶችና የሴቶች ጥምርታ በእጅጉ የተቀራረበ ሲሆን በ2ኛ ደረጃና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደግሞ አበረታች ለውጦች ታይተዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

                         

  1. የሥርዓተ ፆታና ልዩነት

  ብዙ ሰዎች የስርዓተ ፆታና የፆታን ጽንሰ ሃሳብ አንዳዴም ፆታ ሌላ ጊዜ ደግሞ ስርዓተ ፆታ በማለት እየቀያየሩ ሲጠቀሙ ይስተዋላል፡፡ በእነዚህ ሀሳቦች መካከል ልዩነት መኖሩን ምሁራንና የዘርፉ ባለሙያዎች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም መሠረት

7.1. ፆታ:- በወንድና በሴት መካከል ያለን አካላዊና ስነ ተዋልዶአዊ የተፈጥሮ ልዩነት ያሳያል፡፡ ለምሳሌ ሴቶች ለጽንስ መፈጠር የሚረዳ እንቁላል ያኮርታሉ፣ ይወልዳሉ፣ ያጠባሉ የወር አበባ ኡደት ይታይባቸዋል ወዘተ ሲሆኑ ወንዶች በተፈጥሮዓቸው የወንዴ ዘር /ነባዘር/ ያመነጫሉ፣ ፂም አላቸው፡፡ ወዘተ… እነዚህና ሌሎች ተፈጥሮዓዊ ልዩነቶች ናቸው፡፡ በሴትና በወንድ መካከል ያሉ የተፈጥሮ ልዩነቶች ከህብረተሰቡ እድገት እና ለውጥ ጋር የሚቀየሩ አይደሉም፡፡

  7.2.ስርዓተ ፆታ፡- ቃሉ እንደሚያመለክተው ስርዓት ነው ይህ ስርዓት በሰዎች ኑሮ ሂደት ውስጥ በህብረተሰቡ አማካኝነት ተፈጥሮ ያደገ ብሎም የህብረተሰቡ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ሲቀየሩ አብሮ ሊቀየር የሚችል ስርዓት ነው፡፡

በሴቶችና ወንዶች መካከል ያልተመጣጠነ የኢኮኖሚ እድገት፣ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እንዳለ የሚያሳይ ስርአት ነው፡፡ ይህም ሊለወጥ የሚችል ስርዓት ሲሆን ስርዓተ ፆታ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና የፖሊቲካ ስርዓት ውስጥ ተንሰራርቶ ስለሚገኝ በተለያየ መንገድ ይገለፃል፡፡ ስርዓተ ፆታ ህብረተሰቡ የሰጠውን የወንዶችና ሴቶች የስራ ድርሻ ወይም የተሳትፎ ሚና የሚገልጽ ሲሆን የስራ ክፍፍሉ ከአገር አገር ከባህል ባህል ይለያያል፡፡ ለምሳሌ በኢትዮጵያ በተለምዶ የሴቶች ስራ ነው ተብሎ የሚታወቀው ምግብ ማብሰል፣ ልጅ መንከባከብ፣ ቤት ማጽዳት ወዘተ.. ሲሆኑ የወንዶች ስራ /ሚና/ ተብሎ የሚታወቁት  ደግሞ ውሳኔ መስጠት፣ ሹፌርነት፣ እርሻ፣ ወታደራዊ ስራ ወዘተ የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ስለዚህ የአገራችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ለውጥ ሲደረግ የስርዓተ ፆታ የስራ ድርሻ /ሚና/ አብሮ ይለወጣል፡፡

የስርዓተ ፆታ እኩልነት እንዲመጣ ትኩረት ተሰጥቶት ከተሠራ ያልተስተካከለው የስርአተ ጾታ ልዩነት እየጠበበ ይመጣል፡፡ ትኩረት ካልተሰጠው ግን የስራ ክፍፍሉ ቅርፁ ይለወጣል እንጅ ሴቶች ወይም ወንዶች ተሳታፊና ተጠቃሚ ሳይሆኑ ኢፍትሃዊነት ስርዓት ሊቀጥል ይችላል፡፡

በማንኛውም ህብረተሰብ ውስጥ ሴቶች  በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና በፖሊቲካዊ  ጉዳዮች ውስጥ  የሚኖራቸው  ተሳትፎ  በወሊድ  መጠን ላይ  ቀጥተኛ  የሆነ ተጽእኖ አለው፡፡ የሴቶች ሚና በቤት ውስጥ ስራዎችና በእናትነት  ተግባር ላይ ብቻ  የተወሰነ ሆኖ  በሚታይበት የአመለካከት ሁኔታ  ሴቶች ብዙ ልጆችን  በመውለድ ዘር  የማበርከት  ግዴታ እና የማሳደግ  ሃላፊነት  እንዳለባቸው  ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

  1. የሥነ-ህዝብ ክበባት እንቅስቃሴ በትምህርት ቤቶች

   ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የተማሯቸውን ትምህርቶች በተግባር ለመፈፀም የሚያስችሏቸው የት/ቤቶች የተጓዳኝ ትምህርቶች ወይም ክበባት በተማሪዎች ፍላጎትና ዝንባሌ ላይ ተመስርተው ይቋቋማሉ፡፡ የክበቡ አባላትና አስተባባሪ የመወያያ ቀን ወዘተ የመሳሰሉት ፕሮግራሞች በክበቡ አመታዊ እቅድ ተካተው ክበቡ ይመሰረታል፡፡

ትምህርት ቤቶች የእውቀት መገብያ ከመሆናቸው በተጨማሪ ተማሪዎች ለቀጣይ የህይዎት ጉዞአቸው ከህብረተሰቡ ጋር የሚያቆራኟቸውን እና በክፍል ውስጥ ያገኟቸውን ትምህርቶች ወደ ህብረተሰቡ በመዝለቅ በተግባር ከመፈፀም ባለፈ ነባራዊ እውነታውን  የሚረዱበት፣ ከአካባቢያቸው ጋር ይበልጥ የሚተዋወቁበት እና የሚለማመዱበት ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ በትምህርት ቤቶች መኖር ከሚገባቸው መሰረታዊ ክበባት መካከል አንዱና ዋነኛው የስነ ህዝብ ክበብ ሲሆን በዚህም ቀጣይነት የአለው የስነ ህዝብ ትምህርታዊ ቅስቀሳና የማህበረሰብ ውይይት ተግባራት ተጠናክረው የሚሄዱ ክንውኖች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

የስነ ህዝብ ክበብ አባላት በት/ቤታቸው ስለ ስነ ህዝብ ምንነት ከመረዳት በአለፈ ስነ ህዝብና ልማት ስለሚኖራቸው አሉታዊና አዎንታዊ ቁርኝት፣ ፈጣን የህዝብ ቁጥር እድገት ሊያመጣ ስለሚችለው ተፅዕኖ፣ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ያለዉን ፋይዳና ስነ ተዋልዶ ጤና እንክብካቤ ከት/ቤቱ ማህበረሰብ ጀምሮ ግንዛቤ በመያዝ ወደ ህብረተሰቡ ዘልቆ በመግባት በእድር፣ ሰንበቴ፣ ማህበርና ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች እየተገኙ ግንዛቤ በመፍጠር የአስተሳሰብ ለዉጥ እንዲመጣ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡

በአሳለፍነው የ2012 ዓመት በወረዳችን ውስጥ ከሚገኙት 66 ት/ቤቶች መካከል በ ት/ቤቶች 45 የስነ ህዝብ ክበብ የተቋቋመ ሲሆን በነዚህ የስነ ህዝብ ክበባት ውስጥም ከ1479 በላይ አባላት ተማሪዎችን በማፍራት ስነ ህዝባዊ ግንዛቤአቸውን ማሳደግ ተችሏል፡፡ ይህም ማለት የክበቡን የስራ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ሪፖርት በመላክ፣ የመወያያ ቀን በመወሰን አባላትን ማወያየት፣ እንዲሁም ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ የስነ ህዝብ ትምህርት በመስጠት እረገድ በተሻለ ተንቀሳቅሰዋል፡፡

 

  1. ቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ዙሪያ የወንዶች ሚና

ለረጅም ጊዜ በአገራችን ሰፍኖ ከኖረው ልማድ ባህል አኳያ የወንዶች በቤተሰብ ዕቅድ ዙሪያ ተሳታፊነት በእጅጉ አናሳ ነው፡፡ ወንዶች በተገቢው ሁኔታ በቤተሰብ ዕቅድ አጠቃቀም ዙሪያ ተሳታፊ ካልሆኑ ደግሞ የሚጠበቀውን ውጤት ለማምጣት አስቸጋሪ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ዛሬም የቤተሰብ ዕቅድን መጠቀም ለሴቷ ብቻ የተተወ ሀላፊነት ተደርጎ የሚወሰድበት ሁኔታ በሰፊው ሰፍኖ ይታያል፡፡ በዚህ ዙሪያ የአስተሳሰብና የባህሪ ለውጥ በማምጣት የወንዶችን ተሳትፎ ከፍ ማድረግ በስነ ህዝብና በተዋልዶ ጤና እንዲሁም በስርዓተ ፆታ ዘርፍ የተሰማሩ አካላትን የተቀናጀ ጥረት የሚጠይቅ ጉዳይ ይሆናል፡፡

  • በቤተሰብ እቅድና በተዋልዶ ጤና ዙሪያ የወንዶች ሚና፡-
  • ሴቶች በተዋልዶ ጤና ዙሪያ ያለባቸው ችግር ቤተሰባዊ ማህበራዊና ሀገራዊ መሆኑን ግንዛቤ መውሰድና በዚህ ዙሪያ የሌሎችን ግንዛቤ ማሳደግ
  • ፆታዊ ጥቃት በተቀናጀና ማህበራዊ መሠረት ባለው መንገድ እንዲዎገድ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ
  • ሴቶች በትምህርት በስራ መስክ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግና ከወንዶች እኩል ብቃት እንዳላቸው ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠር
  • በቤተሰብ ውስጥ ልጆችና ሌሎች የቤተሰብ አባላት በተዋልዶ ጤና ዙሪያ በነፃነት የሚወያዩበትን ሁኔታ መፍጠርና ግንዛቤያቸው የተሟላ እንዲሆን ማመቻቸት

በአገራችን ለወጣቶች ተስማሚ የሆኑ የተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ገና በሚፈለገው መጠን አልተስፋፉም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በመልካም ጅምርነት የሚታዩ በመንግስት የጤና ተቋማትና በአንዳንድ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስን እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም በተሟላ መልኩ ለወጣቶች ተስማሚ የሆኑ የተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች እየተሰጡ ነው ለማለት ግን አያስደፍርም፡፡ በተለይ በ2ኛ ደረጃ ትምርት ቤቶችና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አካባቢ ለወጣቶች ተስማሚ የሆኑ የተዋልዶ ጤና መረጃዎችና አገልግሎቶች መስፋፋት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ወጣቱን ከአልተፈለገ እርግዝና፣ ኤች አይ ቪ ኤድስን ጨምሮ ከአባላዘር በሽታዎችና  ጥንቃቄ ከጎደለው ውርጃ ወይም የጽንስ ማቋረጥ ተግባራት ሊታደግ የሚችል በመሆኑ ትኩረት  የሚሻ አብይ ጉዳይ ነው፡፡

 

 

  1. ሥነ-ህዝብና የምግብ አቅርቦት

የምግብ እህል በሚመረትባቸው አካባቢዎች ምንም እንኳ ምርታማነት  እየጨመረ ቢሆንም ከህዝቡ ጋር መመጣጠን አልቻለም፡፡

የህዝብና የመሬት ጥምርታ በመጨበሩ  የአርሶ አደሩ  የነፍስ ወከፍ  የእርሻ መሬት መጠን ቀንሷል፡፡ ይህ ደግሞ የምግብ እህል ምርት እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት  የህዝብ ቁጥር  በከፍተኛ ደረጃ መጨመር ነው፡፡

በአገሪቱ ለሰብል  ተስማሚ ነው ተብሎ ከሚገመተው  መሬት  ውስጥ በስራ ላይ የዋለው አነስተኛ  እንደሆነ የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

የምግብ  አቅርቦትና  የህዝብ ብዛት  አለመጣጣም  በምግብ  ራስን  ለመቻል  የሚደረገውን  ጥረት  ምን  ያህል  እንደሚፈታተነው  ማወቅ  ያስችላል፡፡

ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ጫና የእርሻ መሬት እጥረት እንዲከሰት፣ አፈር  ለምነቱን  እንዲያጣ እና ምርት  እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡

በ21ኛው ምእተ አመት የመጀመሪያዎቹ አስር አመታት ወቅት በምግብ  እራስን  መቻል በሚለው  ግብ  ለመድረስ  ወይም እቅዱን ለማሳካት አዳጋች ይሆናል፡፡

ነገር ግን  የወሊድ  መጠንን  በጉልህ  ለመቀነስ  ከተቻለና  የምግብ ምርት  መጠንን ለማሳደግ  ጥረት ከተደረገ  አገራችን የታለመው ግብ ላይ ለመድረስ  እንደምትችል ይጠበቃል፡፡

 

 

  • ፈጣን የህዝብ ቁጥር እድገት በተፈጥሮ  ሃብትና በምግብ  ዋስትና  ላይ  ያለው አንድምታ

በኢትዮጲያ  የምግብ ዋስትናን  ለማረጋገጥ መሰናክል  የሚሆኑ በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ እነዚህም ኋላ ቀር የሆነ የአመራርት ቴክኖሎጂ፣ ፈጣን  የህዝብ ቁጥር  እድገት፣ የአካባቢና  የተፈጥሮ ሃብት መመናመን በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ የምግብ ዋስትና  ሊረጋገጥ የሚችለው  የተፈጥሮ ሃብት  መሰረት የሆኑትን  መሬት፣ ውሃ፣ ደን እና ሌሎችንም በአግባቡ  መያዝና ጥቅም  ላይ ማዋል ሲቻል ነው፡፡ የሰዎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ  እንቅስቃሴና  ትክክለኛ ያልሆኑ የግብርና  ተግባራት የተፈጥሮ  ሃብት  አጠቃቅምና አያያዝ  ላይ እንዲሁም ስረዓተ ምህዳር  ላይ መዛባት ያስከትላል፡፡

መሬትን ከመጠን  በላይ ማረስ፣ የግጦሽ  ቦታዎችን ከአቅም  በላይ በእንስሳት ማስጋጥ፣ የደኖች መመናመን፣ የአፈር  መሸርሸር /ለምነት ማነስ/፣  እንዲሁም  የውሃ፣ የመኖና  የማገዶ  እጥረት  በገጠሩ  አካባቢዎች በስፋት ይስተዋላሉ፡፡ እነዚህ  ሁኔታዎች በአብዛኛው ጊዜ አንዱ በሌላው  ላይ ተፅእኖ በመፍጠር  የምግብ ዋስትና ማጣት፣  የተፈጥሮ ሃብት መመናመን እና የድህነት፣ ሁኔታዎች  እንዲጠናከሩና  እንዲባባሱ ያደርጋል፡፡ በዚህም የተነሳ ሰዎች በተደጋጋሚ በድርቅ ሊጠቁ እና ለርሀብ ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡

የህዝብ ቁጥር  እየጨመረ  በሚሄድበት  ጊዜ አብዛኛው  ደን ለእርሻ ቦታ ለማስፋፋት ሲባል ይመነጠራል ከመጠን በላይም  ይታረሳል ከ75 አመታት በፊት 40 በመቶ የነበረው የደን ሽፋን  አሁን 13.65 በመቶ ወይም ከዚህ በታች  ነው፡፡ እያደገ  የመጣው  የህዝብ ብዛት  ያስከተለው  ተጨማሪ  የማገዶና የግንባታ  እንጨት   እንዲሁም  ተጨማሪ የእርሻ  መሬት  ፍላጎት  የደን  ሀብቶች ይበልጥ  እንዲመናመኑ  አድርጓል፡፡ ይህም  የግብርና ምርታማነት  እንዲቀንስ፣ ማለትም የምግብ እህል ምርት በጥራትም ሆነ  በመጠን ዝቅ እንዲል በማድረግ በምግብ  ዋስትና  ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ  ያስከትላል፡፡

በቂ የእፅዋት ሽፋን ከሌለውና ውጤታማ ያልሆኑ የአፈር ጥበቃ ከማይካሄድበት አካባቢ በርካታ ለም አፈር በየጊዜው በጐርፍና በንፋስ ይሸረሸራል፡፡ የአፈር መሸርሸር በአብዛኛው የሚከሰተው በእርሻ መሬቶች ላይ ነው፡፡ በገጠር አካባቢ  የህዝብ ቁጥር መጨመር በእያንዳንዱ  ሄክታር ላይ  የሚኖረው የሰዎች ቁጥር እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ ይህም በህዝብ ብዛት መጨናነቅን እና  የነፍስ ወከፍ  የእርሻና  የግጦሽ መሬት  እጥረት እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ የእርሻ መሬት ጥበት በሚከሰትበት ጊዜ አርሶ አደሮች እያደገ  ያለውን  የምግብ እህል  ፍላጎት  ማርካት  የሚችሉት ተጨማሪ መሬትን  በማረስ ነው፡፡

በገጠር አካባቢ  ያለው  የህዝብ ቁጥር መጨመር ጫና መገለጫ የእርሻ ለም አፈር መከላት ነው፡፡ የለም አፈር ክለት ደግሞ ምርታማነትን  ይቀንሳል፡፡ የእርሻ መሬቶች ከመጠን በላይ ተደጋጋሚው መታረሳቸውና አርሶ አደሩ መሬት አጥ መሆን  የህዝብ ቁጥር መጨመር የሚያስከትለው ጉዳት ነው፡፡

በአጠቃላይ የእርሻ መሬት ከእያንዳንዱ ገበሬ እየቀነሰ መሄድ እንዲሁም በእርሻ መሬት መሸርሸር የተነሳ ለእርሻ  ተግባር መዋል የማይገባቸው አካባቢዎች ጭምር መታረስ፣ ቤተሰቦች ራሳቸውን የመመገብ አቅም  እንዲቀንስ  ከማድረጉ በተጨማሪ  በአገራችን የግብርና  ምርትን በማሳደግ  የምግብ ዋስትናን  ለማረጋገጥ  የሚደረገውን ጥረት ይፈታተነዋል፡፡

 

 

  1. ህዝብና ጤና

   የህዝብ ቁጥር እድገትና የጤና አገልግሎት አቅርቦት የጠበቀ ትስስር ያላቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡ የአንድ ሀገር ህዝብ ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም ጋር የተመጣጠነ ሲሆን የተሻለ የጤና ሽፋንና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል፡፡
አቅምን ያገናዘበ ቤተሰብ በመመስረት ልጆች በተሻለ ሁኔታ ጤናማ እንዲሆኑ ተመጣጣኝ ምግብ እንዲያገኙና የተሻለ አቅም እንዲኖራቸው ማድረግ ይቻላል፡፡  በሀገራችንም  የሚከሰቱ አብዛኛዎቹ በሽታዎች የሚመጡት በተላላፊ በሽታ ነው፡፡ በመሆኑም የአካባቢና የግል ንፅህናን በመጠበቅ ራስንም ሆነ ህዝቡን ከበሽታ መከላከል ይቻላል፡፡ የጤና እንክብካቤ ዋና ዋና ክፍሎች የጤና፣  ትምህርት፣ የግልና የአካባቢ ንፅህና ፣ የአመጋገብ ስርዓት፣ ክትባትና የቤተሰብ እቅድ ናቸው፡፡  ከህዝቡ ቁጥር ጋር ያልተመጣጠነ የኢኮኖሚ አቅም  መኖር አነዚህን የጤና ክፍሎች ለህዝቡ ለማቅረብና የጤና አገልግሎት ሽፋንና ጥራትን ለማሳደግ በሚደረገው  እንቅስቃሴ ላይ   አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡  የጤና አገልግሎትን ለማቅረብ ሆስፒታሎችንና ጤና ጣቢያዎችን መገንባት፣ ሀኪሞችን ማሰልጠንና መድሀኒቶችን ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡

የእናቶችን  ጤና ለማሻሻልና በወሊድ ምክንያት የሚሞቱ ህፃናትን ቁጥር ለመቀነስ ሁሉም ሴቶች መብቶቻቸው ተከብሮላቸው በመብቶቻቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግና የአካል፣ የአምሮ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴአቸው ላይ ያሉ ችግሮች መቅረፍ ወይም አጠቃላይ ደህንነታቸውን ማረጋገጥ ሲቻል ነው፡፡ በሰፈር ዉስጥ በሚገኙ የልምድ አዋላጆች የሚደረገውን የማዋለድ ተግባር እና የሚያስከትለውን  ጉዳት በማስገንዘብ እናቶች ወደ ጤና ተቋማት ሂደው እንዲወልዱ እና የጤና ክትትል እንዲያገኙ በማድረግ የእናቶችን ጤና መጠበቅ ይቻላል፡፡ እናቶች ጤናቸው ተጠብቆ ጤናማ ልጆችን በመውለድ በእንክብካቤ እንዲያሳድጉ ሴቶችን መደገፍና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት እንዲጠቀሙ ማበረታታትም ዋና ተግባር መሆን አለበት፡፡ እንደ አስገድዶ መድፈር፣ ጠለፋ፣ የሴት ልጅ ግርዛት፣ ያለ እድሜ ጋብቻ ወዘተ… የመሳሰሉ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከልና ለማስወገድ ህብረተሰቡን በማስተማርና የድርጊቱ ፈጻሚዎችን ለህግ በማቅረብ የእናቶችን ሁለንተናዊ ደህንነት /ጤና/ ማስፈን ይቻላል፡፡ እ.ኤ.አ በ2005 የስነ ህዝብና ጤና ጥናት፣ በወሊድ  እድሜ ክልል ከሚገኙ ሴቶች ውስጥ 28% ያህሉ የደም ማነስ ይታይባቸዋል፡፡ ይህ ክስተት አዘውትሮ የሚታየው ባልተማሩ እናቶች፣ እርጉዝ የሆኑ እና በደሀ ቤተሰብ ውስጥ መገኘት ነው፡፡ ይህን ችግር ከከተማ ይልቅ በገጠሩ ህብረተሰብ ጐልቶ ይታያል፡፡ እ.ኤ.አ በ2005 የስነ ህዝብና ጤና ጥናት መሰረት 27% አዝጋሚ የምግብ አለመመጣጠን ሲታይባቸው ከ15 እስከ 19 እና ከ45 እስከ 49 እድሜ ክልል ባሉ ሴቶች ከ10ሩ 3ቱ የምግብ እጥረት  ችግር እንደሚታይባቸው ያሳያል፡፡ ይህ ችግር በስፋት የታየው በገጠሪቱ ኢትዮጵያ መሆኑን መረጃዎች ይገልፃሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2005 የስነ ህዝብና ጤና ጥናት የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት በሀገር አቀፍ ደረጃ 3.5 % ሲሆን ከዚህ ውስጥ 4%ቱ በሴቶች ላይ ያለው ስርጭት ሲሆን 3% ደግሞ የወንዶች ነው፡፡ እነዚህንና ሌሎችን በእናቶች ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ ሴቶች የትምህርት እድል እንዲያገኙ ማመቻቸትና በልማት እንቅስቃሴ ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ በማድረግ የእናቶችን የኢኮኖሚ አቅም ማጎልበት ይገባል፡፡ ጤናማ እና ጠንካራ፣ በስነ ምግባር የታነጹ የወደፊት ሀገር ተረካቢ የሚሆኑ ህጻናትን ለማፍራት ሁሉም ሰው የእናቶችንና የህጻናትን መሰረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት ጥረት ማድረግ አለበት፡፡ ህጻናትን ከልዩ ልዩ በሽታዎች ለመከላከል በወቅቱ በማስከተብና ሲታመሙ ወደ ጤና ተቋማት በመውሰድ እንደ ኩፍኝ፣ መንጋጋ ቆልፍ፣ ፖሊዎ፣ ማጅራት ገትር ወዘተ ከመሳሰሉ ገዳይ በሽታዎች መከላከል ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ የሴቶችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻልና ጤናማ እናትነትን ለማረጋገጥ የሁሉም አካላት ድጋፍና እርብርብ ያሻል፡፡

ለእናቶችና ህፃናት የጤና ችግር ትኩረት ከሚሰጥባቸው ምክንያቶች መካከል የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡

ህፃናትና እናቶች በቁጥር አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል ስለሚይዙበእናቶችና ህፃናት ላይ የሚከሰቱ

 የጤና ችግሮች ተያያዥነት ስላላቸው

በአብዛኛው በእናቶች ላይ የሚደርስ የጤና ችግር በእርግዝና ወቅት የሚከሰት ሲሆን በእናቶች ላይ

 ህመምና ሞትን በማስከተል በተዘዋዋሪ የህፃናትንም ሞት ስለሚጨምር

እናቶች የቤተሰብ መሰረት  በመሆናቸውና ህፃናት የነገ አገር ተረካቢ በመሆናቸው፡፡

ለእናቶች ጤንነት የሚደረግ ርብርብ ለአገራዊ ብልጽግና መሰረት የሚጥል በመሆኑ እንዲሁም

የእናቶች ሞት ምክንያቶች መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና ህብረተሰቡም ተጠቃሚ

 በማድረግ በቀላሉ ሊቀረፉ የሚችሉ በመሆናቸው ነው የሚሉት ትኩረት የሚደረግባቸው ምክንያቶች

 ናቸው፡፡

በሀገራችን ከወሊድ ጋር በተያያዘ ችግር ምክንያት በየቀኑ 68 እናቶች፣ በየሠዓቱ ደግሞ 3 እናቶች ህይወታቸው

ይቀጠፋል፡፡ ስለዚህ የጤናማ እናትነት ዘመቻን በማጠናከር የእናቶችን ህይወት እንታደግ፡፡ በየቀበሌው የሚገኙ የጤና

 ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ለጤናማ እናትነት ከጤና ተቋማት ጋር የሚያገናኙ ድልድዮች ናቸውና የሚሰጡትን ምክርና

 ኣገልግሎት ተቀብለን በተግባር ላይ ልናውል ይገባል፡፡ ዛሬ እየተካሄደ ባለው የኤች አይ ቪ/ኤደስ ትግል መላው ሴቶች

 በሽታውን ከመግታትና ከመከላከል አኳያ ንቁ ተሳትፎ ሊያሳዩ ይገባቸዋል፡፡ አንድም እናት በወሊድ ምክንያት

የማትሞትበትንና አንድም ህጻን ከኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ ነጻ የሚሆንበትን ሁኔታ ለመፍጠር ሁላችንም

በጋራ መስራት ይኖርብናል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

         

  ሴቶች እናቶች ህጻናትን ወልደዉ በማሳደግ ከመልካም ትእትናና ርህራሄ ጋር

ከመቅረጻቸዉ በላይ እድሉ ደርሷቸዉ ዘመናዊ ትምህርት የመማር እድል የገጠማቸዉ

 ጥቂት ሴቶች፣እናቶች በህይወት መስተጋብራቸዉ ዉስጥ እንደሚኖሩበት የህብረተሰቡ

 ደስታ ችግር(የኑሮ ፈተና) ሁሉ በተለያዩ የስነ ቃል መገለጫዎች ደስታና ብሶታቸዉን

 ሲገልጽ መቆየታቸዉ ይታወቃል፡፡

ስለሆነም ጣሊያኖች በ1888 ዓ.ም በወርሃዊ የካቲት 23 ቀን ኢትዩጽያ ቅኝ ለመግዛት

በወሰዱት የወረራ ጦርነት ወቅት በደረሰባቸዉ ሸንፈት ለ40 አመት ቅድመ ዝግጅት ከአካሄዱ

 በኋላ በ1928 ዓ.ም በወርሃ ጥር ውስጥ ለ2ኛ ዙር በተካሄደዉ ወረራ ወቅት ጣሊያን

በኢትዩጽያ ላይ የደረሰዉን የሰዉ ዘር ጭፍጨፋ ሴት ደራሲያን ስለደረሰዉ ግፍ

 ከደረሱት ደራሲዎች መካከል ሙሉ እመቤት ገብሬ ተክሌ፣ብዙነሽ መኮነን፣ምሳሌ

ጥኡመልሳንና ማህሌት ብርሃን አካሉ ይገኙበታል፡፡

በመሆኑም የብሶት መግለጫ መካከል የደራሲ ምሳሌ ጥኡመልሳን ጹሁፍ(ግጥም)

 

12.1.ሥነ-ህዝብን የሚገልፅ ግጥም

ደጃዝማች በላይ ዘለቀና እጅጉ ዘለቀ ከ1928 ዓ/ም -1933 ዓ/ም ድረስ በነበረው የነጻነት ተጋድሎ ወቅት አርበኝነትን ለማበረታታት

በጐጃም ውስጥ ማህበረሰቡ ይገልጻቸው ከነበሩ ስንኞች መካከል

  • ያ ዘለቀ ላቀው የዘራው እንጣቆ ፣
  • ያጯጩሆው ጀመር በየጎራው ዘልቆ ፡፡

ከ1933 ዓ/ም ሚያዚያ ወር ጀምሮ ሀገራችን ኢትየጵያ ነጻ ከወጣች በኋላ በተደረገው የሥልጣን ድልድል

 ወቅት ደጃዝማች

 በላይ ዘለቀ የእነማይ ወረዳ አስተዳዳር ዋና አስተዳደሪ ብቻ ሆኖ በመሾሙ ቅር ሲሰኝ  በመሸፈቱ የተጋድሎ

  የአርበኝነት

 ጊዜ ጓደኛው  የቆላ ደጋዳሞቴው  አርበኛ ደጃዝማች መንገሻ ጀንበሬ በእርቅ ምክንያት አግባባቶ ከቢቸና

አውራጃ ወደ

 ደብረ-ማርቆስ ከተማ ከሠራዊታቸው  ጋር  በመጓዝ ላይ እያሉ የመንገሻ  ጀንበሬ አቅራሪታ

  • ያልተገራ ፈረስ ኮስተር እያላችሁ ፣
  • መንገሻ ጀንበሬ ወርዶ ገራላችሁ ፡፡

በል ብሎ ሲያቅራራ የኢትዮጵያ  ደመላሽ  አባኮስትር  በላይ

ከመንገሻ  ጀምበሬ ጋር  እጁን በሻሺ  ታስሮ  ስለነበር  ዘወርብሎ  ወደራሱ  አጃቢና       

አቅራሪታ  ለቀኛማች ደሴ

  • ቴዎድሮስ በጎ ሠራ   ሽጉጡን  ጎረሰው ፣
  • ተነጋግረን (ተመምለን ) ነበር ላንገዛ ለሰው ፡፡

በማለት በእርቅ ድርድር  በመሃላ  ከአስገባው  በኋላ  በውጊያ     እንዳሸነፈው በማድረግ 

የደጃዝማች መንገሻ ጀንበሬን አቅራሪታ በተመሣሣይ   ስንይ  ሸንቆጥ  አድርጎታል ፡፡

 

ከ1966 ዓ/ም በፊት  በነበረው አስተዳደር  አርሶ አደሩ የነበረበትን የጭሰኝነት እሮሮ

 ከዚህ በታች  በተመለከተው  ስንኝ መሠረት ይገልጽ  ነበር

  • የእናንተልጅ በልቶ የእኛ ልጅ ያለቅሳል ፣
  • የእናንተ ቤት ተከድኖ የእኛ ቤት ያፈሣል ፣
  • የእናንተ መሬት ታርሶ የእኛ ዳዋ ለብሷል ፣
  • ወይ ከእናንተ ወይከእኛ ያንዳችን ቀን ደርሷል ፣
  • ጊዜ መሃንዲስ ነው ይሰራል ያፈርሳል ፡፡

 

 

 

  1. የባሶ ሊበን ወረዳ ጠቅላላ ህዝብ ብዛት 1999-2013.

 

             ከተማ

                 ገጠር

                     ከተማ+ገጠር

ዓ.ም

ወንድ

ሴት

ድምር

ወንድ

ሴት

ድምር

ወንድ

ሴት

ድምር

1999

3094

3345

6439

67940

66953

131893

68034

70298

138332

2000

3227

3488

6715

65921

67965

133886

69148

71453

140601

2001

3365

3638

7003

66918

68992

135910

70283

72630

142913

2002

3509

3794

7304

67929

70035

137964

71439

73829

145267

2003

3660

3957

7617

68956

71093

140049

72616

75050

147666

2004

3817

4127

7944

69998

72168

142166

73815

76294

150109

2005

3981

4304

8284

71056

73258

144314

75036

77562

152598

2006

4410

5376

9786

70588

77641

148230

74999

83017

158016

2007

4665

5680

10345

71878

79052

150920

76532

84733

161265

2008

4932

6013

10945

73165

80478

153643

78097

86491

164588

2009

5195

6333

11528

73908

81273

155181

79103

87606

166709

2010

5484

6686

12170

74544

81975

156519

80028

88661

168689

2011

5767

7027

12793

74182

81595

155777

79949

88622

168571

2012

6075

7403

13478

74721

82188

156909

80795

89592

170387

2013

6380

7774

14154

75268

82792

158060

81648

90566

172214

 

 

 

 


            የወረዳችን ልዩ ልዩ የስነህዝብ ረጃዎች

ዓ.ም

 

 

የወረዳው የቆዳ ስፋት በካሬ ኪ.ሜ

የህዝብ ጥግግት/በ ካ.ኪ.ሜ

የምርት መጠን በኩንታል

የምግብ አቅርቦት ኩ/ሰው

የንጹኅ መጠጥ ውሃ ሽፋን %

የውልደት መጠን በ1000ኛ

የቤተሰብ እቅድአገልግሎት ተጠቃሚዎች በ%

የጥገኝነት ምጣኔ በመቶኛ

የልጅነት ጥገኝነት

የእርጅና ጥገኝነት

ድምር ጥገኝነት

2000

1132.84

135.18

1063341.77

6.94

41.9

110

48

90.59

5.77

96.36

2000/1

1132.84

138.82

1239352.5

7.88

 

109

70

90.56

5.77

96.33

2001/2

1132.84

127.43

1442665.98

9.99

50.2

109

85.1

 

 

 

2002/3

1132.84

130.35

1764218

12.28

57.7

109.07

110.1

83.88

5.79

89.67

2003/4

1132.84

132.5

1831620.76

12.20

62.8

111.91

90.2

83.81

5.78

89.59

2004/5

1132.84

134.70

1372446

11.12

70

97.23

107.5

83.74

5.78

89.52

2005/6

1132.84

139.49

2273569

14.09

81.5

118.32

83.3

77.52

9.51

87.03

2006/7

1132.84

141.68

3846065.5

23.3

93.1

137.1

88.04

77.05

7.22

84.27

2007/8

1132.84

145.2

3207122

19.48

67.48

136.04

92.5

74.81

5.96

80.77

2008/9

1132.84

147.16

3322692

19.93

74.8

136.3

94.45

74.68

5.94

80.63

2008/10

1132.84

148.9

2518630.75

14.9

93.8

139

116

74.54

5.93

80.47

20010/11

1132.84

148.8

2909739

17.26

84.8

116.9

49.56

74.37

5.93

80.30

2011/12

1132.84

150.41

1523671 አመት አልተጠናቀቀም

8.94

96.14

83.01

49.65

74.22

5.92

80.14

2012/13

113284

151

 

 

 

 

93 %

 74.08

5.9

79.98

 

 

   የ2013  ዓ/ም  የባሶሊበን   ወረዳ  ህዝብ   ብዛት   ማሣያ   ቅጽ

ተቁ

የቀበሌ ሥም

    የህዝብ ብዛት   በጾታ

 

       

ወንድ

ሴት

ድምር

ምርመራ

       

1

  የጁቤ

5891

7178

13069

 

       

2

 ልምጭም

4831

5033

9864

 

       

3

የለመለም

3272

3348

6620

 

       

4

የገላው

1920

2133

4053

 

       

5

ምችግ

2424

2654

5078

 

       

6

ደንደገብ

3680

4073

7753

 

       

7

አ/አምባ

2601

2888

5489

 

       

8

የዱግ

3328

3732

7060

 

       

9

እነተመን

3247

3686

6933

 

       

10

ዶገም

4569

4790

9359

 

       

11

ደን

3274

3588

6862

 

       

12

የላምገጅ

4105

4890

8995

 

       

13

ኮርክ

5773

6730

12503

 

       

14

ጉንድልሚት

1736

1826

3562

 

       

15

ድንጓም

3592

3884

7476

 

       

16

የንስቻ

2375

2710

5085

 

       

17

አንጅም

3245

3594

6839

 

       

18

ጭድማርያም

3307

3728

7035

 

       

19

ደጃት

3634

3962

7596

 

       

20

ጐበጥማ

1478

1649

3127

 

       

21

ዘንቦል

4043

4522

8565

 

       

22

ቤተ-ንጉሥ

4154

4452

8606

 

       

23

ኮሜ -ዘሜ

5169

5516

10685

 

       

 

  ድምር

81648

90566

172214

 

       
                   

 

 

 

 

 

 

 

 

                      2013  ዓ/ም     የባሶሊበን  ወረዳ   ህዝብ  ብዛት  በ  5  ዓመት  የዕድሜ  ክፍፍል

ዕድሜ

                ከተማ

         ገጠር

           ጠቅላላ ድምር

ወንድ

ሴት

ድምር

ወንድ

ሴት

ድምር

ወንድ

ሴት

ድምር

 0-4

1179

448

1627

9042

9841

18883

10221

10289

20510

   5-9

521

542

1063

11696

12088

23784

12217

12630

24847

10-14

689

604

1293

11827

12407

24234

12516

13011

25527

15-19

1168

2387

3555

9276

11236

20512

10444

13623

24067

20-24

615

812

1427

6275

6818

13093

6890

7630

14520

25-29

187

1168

1355

5487

6637

12124

5674

7805

13479

30-34

625

250

875

4144

4896

9040

4769

5146

9915

35-39

615

521

1136

4118

4889

9007

4733

5410

10143

40-44

271

365

636

2778

2574

5352

3049

2939

5988

45-49

167

167

334

2483

2321

4804

2650

2488

5138

50-54

94

83

177

1771

2554

4325

1865

2637

4502

55-59

83

177

260

2149

2490

4639

2232

2667

4899

60-64

83

0

83

1550

1395

2945

1633

1395

3028

65-69

0

167

167

956

935

1891

956

1102

2058

70-74

0

0

0

740

743

1483

740

743

1483

75-79

0

83

83

548

394

942

548

477

1025

80+

83

0

83

428

574

1002

511

574

1085

ድምር

6380

7774

14154

75268

82792

158060

81648

90566

172214

           

 

     

 

 

          

 

 

 

 

እድሜ

                    ከተማ

                   ገጠር

                  ድምር

 
 

 

0

348

159

507

1370

1816

3186

1718

1975

3693

 

1

169

89

258

1647

1380

3027

1816

1469

3285

 

2

358

89

447

1614

1852

3466

1972

1941

3913

 

3

79

0

79

2004

2694

4698

2083

2694

4777

 

4

169

89

258

2341

2027

4368

2510

2116

4626

 

5

79

79

158

2317

2011

4328

2396

2090

4486

 

6

169

0

169

2037

2485

4522

2206

2485

4691

 

7

0

89

89

2414

2845

5259

2414

2934

5348

 

8

169

347

516

2823

2190

5013

2992

2537

5529

 

9

79

0

79

2019

2470

4489

2098

2470

4568

 

10

159

159

318

2906

2599

5505

3065

2758

5823

 

11

89

169

258

1909

1807

3716

1998

1976

3974

 

12

0

169

169

2731

3060

5791

2731

3229

5960

 

13

80

79

159

1937

2332

4269

2017

2411

4428

 

14

328

0

328

2258

2519

4777

2586

2519

5105

 

15

338

328

666

2045

2624

4669

2383

2952

5335

 

16

79

586

665

2254

2264

4518

2333

2850

5183

 

17

258

506

764

1485

1773

3258

1743

2279

4022

 

18

169

586

755

2623

3007

5630

2792

3593

6385

 

19

268

268

536

802

1485

2287

1070

1753

2823

 

ድምር

3387

3791

7178

41536

45240

86776

44923

49031

93954

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

       የሥነ -ህዝብና ልማት ትስስር

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

                ዋቢዎች/references/

  • የገኢል ሚኒስቴር ዓመታዊ የስነ ህዝብ መፅሄት፣ ቅፅ 16 ቁጥር 1፣ ሀምሌ 2005 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ
  • የምስራቅ ጎጃም ዞን ስነ ህዝብና ልማት መፅሄት፣ ቅፅ 5 ቁጥር 1 ግንቦት 2007 ዓ.ም፣ ደብረ ማርቆስ
  • amharabofed.gov.et
  • የባሶ ሊበን ወረዳ ገኢል ፅ/ቤት የስነ ህዝብ ማኑዋል፣ ህዳር 2007 ዓ.ም፣
  • የጎጆየ ሚስጥር የግጥም መድብል 2005 ዓ.ም
  • የአብክመ ባህልና ቱሪዝም አመታዊ መጽሔት 1998
  • ባሶ ሊበን ወረዳ 2012 ወረዳ ሪፖርት፣
  • አባ ኮስትር በአበራ ጀምበሬ