report

1.መ ግ ቢ ያ

    የባሶ ሊበን ወረዳ በምሥ/ጐጃም ዞን በአማራ ክልል ከሚገኙ 169 ወረዳዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን በሰሜንና በምስራቅ አነደድ ወረዳ፣ በደቡብ ከኦሮሚያ ክልል፣  እና በምዕራብ  ጐዛምን ወረዳ ጋር ያዋሰናል፡፡አጠቃላይ የቆዳ ስፋቱም 1132.84 ካሬ ኪ/ሜትር እንደሚሆን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ወረዳው በ22 የገጠር ቀበሌዎች እና በ1 መሪ ማዘጋጃ በ2 ታዳጊ ከተማ ዉስጥ 4 ቀበሌዎች  በድምሩ በ26 ቀበሌ የተከፋፈለ ሲሆን የወረዳው ዋና ከተማ ከሆነችው ከየጁቤ ደ/ማርቆስ 27 ኪ/ሜ ከክልሉ ዋና ከተማ ባህር ዳር በ292 ኪ/ሜ እና ከአዲስ አበባ በ3ዐ7 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ለኢንቨስትመንትና ለኑሮ ተስማሚ የአየር ንብረት ያላትና በፈጣን ዕድገት ላይ የምትገኝ  ከተማ ናት፡፡

ወረዳው በአጠቃላይ ከባህር ወለል በላይ ከ8ዐዐ እስከ 2700 ሜትር ከፍታ ያለው የመሬት አቀማመጥ ሲኖረው የአየር ንብረቱም 46% ወይና ደጋ፣ 54% ቆላ ሲሆን በዓመት በአማካኝ ከ9ዐዐ እስከ 27ዐዐ ሚ.ሜ የዝናብ መጠን ያገኛል፡፡

በ2014 ዓ.ም የወረዳው ህዝብ ብዛት 173881 እንደሆነ የተገመተ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 82424/ ወንዶችና 91456(52.59%) ሴቶች ናቸው፡፡ በገጠር የሚኖሩ 75716/47.61%/ ወንዶችና 83782/52.38%/ ሴቶች በከተማ የሚኖሩ 6708/45.07%/ ወንዶችና 8174/54.92%/ ሴቶች ይሆናሉ ተብሎ ይገመታል፡፡

ባለፉት የስራቴጅክ አመታት እንደ ሀገር ብሎም እንደ ክልላችን ለተመዘገበው አጠቃላይ ፈጣን ልማትና መልካም አስተዳደር ግንባታ ወረዳችን የበኩሉን ድርሻ እንደተወጣ መገንዝብ የሚቻል ሲሆን በተለይም ካለን ምቹ አግሮ ኢኮሎጅ አንፃር በሰብል ምርትና ምርታማነት ልማት ዘርፍ ለአጠቃላይ ኢኮኖሚው እድገት የነበረን ድርሻ የላቀ ነበር፡፡ከዚህም በተጨማሪ በማስፈፀም አቅም ግንባታ ዙሪያ የልማት ኃይሎች በተቀናጀ መንገድ ለልማት እድገትና ለመልካም አስተዳደር ግንባታ አስተዋጽኦ ከማድረጋቸውና በከተማ ልማትና የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን ከማስፋፋትና ሥራ አጥነትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ተግባራትን ከማከናወን እንዲሁም በማህበራዊ ልማት ዘርፍ የትምህርትና ጤና የምዕተ አመቱን ግቦች ለማሳካት ሲደረግ የነበረው እንቅስቃሴና በመልካም አስተዳደርም ዘርፍ የዴሞክራሲ ተቋማትን ከማስፋት አንፃር የነበሩን አበረታች እንቅስቃሴዎች አሁን ለጀመርነው የዕድገትና የትራንስፎርሜን እቅድ መሳካት እንደ ትልቅ መሰረት ሊወሰዱ የሚገባቸው አበረታች ክንውኖቻችን ነበሩ፡፡

ይሁን እንጂ የወረዳችንን ልማት በማፋጠን ረገድ በነበረው እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጸዕኖ በማሳደር ረገድ የጐላ ድርሻ የነበራቸው የተፈጥሮ ሀብት መመናመን ፣የሥራ አጥ ቁጥር መበራከትና በየደረጃው የሚሰጠው ትምህርት ጥራት መጓደልና የመልካም አስተዳድር መጓደል የመሳሰሉት ጉዳዮች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው በሚቀጥሉት የስትራቴጅክ አመታት ከፍተኛ ርብርብ ሊደረግባቸው የሚገቡ አበይት ተግባራት ናቸው፡፡በመሆኑም ከባለፉት አመታት ያገኘናቸውን መልካም አፈፃፀሞችና ተሞክሮዎች አጥብቀን በመያዝና እንደ እርሾም በመጠቀም እንደ ወረዳ በየአስተዳደር እርከኖች በላቀ ሁኔታ በመፈፀም እንደ ሀገር፣ እንደ ክልል፣ ብሎም እንደ ወረዳ የሚጠበቀውን የኢኮኖሚ እድገት ትርጉም ባለው መልኩ ለማሳካት ይረዳ ዘንድ ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ እያሳሰብን የ2014 በጀት ዓመት 4ኛ ሩብ አመት እቅድ ክንውን አፈፃፀምን የሚያሳይ ሪፖርት ተዘጋጅቷል፡፡

2.ዓላማ

የዚህ ሪፖርት አላማ እንደ ወረዳ የሚጠበቀውን የኢኮኖሚ እድገት ትርጉም ባለው መልኩ ለማሳካት ይረዳ ዘንድ ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ እያሳሰብን የ2014 በጀት ዓመት እስከ 4ኛ ሩብ አመት መጨረሻ እቅድ ክንውን አፈፃፀምን የሚያሳይ ሪፖርት በበጀት አመቱ ከአቀዱት አመታዊ እቅድ አንፃር የዕቅድ ክንውናቸውን ለማመላከትና በአፈፃፀማቸው መሰረት በቀጣይ ሩብ አመት የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖራቸውና ከምዕራፍ ሁለት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አንፃር ያለውን አፈፃፀም ለማሳየት ጉልህ ሚና እንዲኖረው ለማስቻል ነዉ፡፡

3.የሪፖርት አሰራር ስልት

     ይህ ሪፖርት የተዘጋጀው ሴክተሮች አዘጋጅተው በሚልኩት ሪፖርት ላይ የተመሰረተ ሆኖ የልማት ዕቅድ ክትትልና ግምገማ ቡድን አጭርና ግላጭ በሆነ መንገድ በዘርፍ ለማስቀመጥ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፡፡ሪፖርቱም የ2014 የ4ኛው ሩብ አመት ዕቅድ ክንውን አፈፃፀምን በግልፅ ለማሳየት እንዲያስችል ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡

 

 

4.ዕቅድ ክንዉን አፈጻጸም በዘርፍ

4.1.ኢኮኖሚ ዘርፍ

1.ግብርና ልማት

    በክልላችንም ሆነ በወረዳችን ዋነኛ የልማት አጀንዳና ከድህነት በመቀነስ የህዝባችንን ኑሮ ለማሻሻል ዘመናዊ ቴክኒኦሎጅ የሚጠቀም፤በገበያ የሚመራ አርሶ አደር ለመፍጠር ሲሆን ይህን ትልቅ ራዕይ ለማሳካት በዋነኛ የኢኮኖሚ መስክ ግብርና ተደርጎ ርብርብ እየተደረገበት መሆኑ ይታወቃል፡፡በዚህም በተያዘዉ አቅጣጫ  መሰረት በወረዳችን አርሶ አደሩን በግብርና ኤክስቴንሽን በማደራጀት የአዳዲስ አሰራሮችን እና ቴክኒኦሎጅዎችን ከማስፋፋት ዕቅድ 11 ክንዉን 3187፤ጠቅላላ የሚካሄድ ሰርቶ ማሳያ ዕቅድ 370 ክንዉን 606፤በአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት 115 ክንዉን 121፤በአርሶ አደር ማሳ እቅድ 255 ክንዉን 485 መፈፀም ተችሏል፡፡በጠቅላላ ድግግሞሽ 114667 ጊዜ የአ/አደር በዓላት ቀን በማካሄድ 95096፡፡

የኮሞዲቲ ሰብሎችን  በተለይም የመስኖ ስንዴ ኩታገጠም ኮሞዲቲ ተሳታፊ ቀበሌ ዕቅድ 22 ክንዉን 14 ስራዉን ለማከናወን  የተደራጁ ክላስተሮች ብዛት ዕቅድ 16500ሄ/ር ክንዉን 40500 ሲሆን አፈፃፀሙ >100% መሆኑን ያሳያል፡፡ጠቅላላ ተሳታፊ ዕቅድ 1400 ክንዉን 3002 ማድረግ ተችሏል፡፡

ሰብል ልማትን በተመለከተ  ለማዘራት ፤የግብዓት አጠቃቀም እየተሻሸለ የአፈር ለምነት ማሻሻያ የተሰሩ ስራዎች በተለይ በግሪን ማኒዩር፤በቨርሚ ኮምፖሰት የአረምና የኩትኳቶ ስራዎች በወቅቱ መከናዎናቸዉ በጥንካሬ የታዩ ተግባራት ናቸዉ፡፡አ/አደሩ አባዉራ 22170 እማዉራ 3358 በልማት ቡድን 976 በ1ለ5 4379 በአባላት 26760 ለማደራጀት ታቅዶ በክንዉን ሁሉንም በመፈጸም 100% መፈፀም ተችሏል፡፡ከአረም መከላከል ተግባር አኳያ በዋና ዋና እና የተለመዱ የሰብል አይነቶች አረምን ለመከላከል የተዘራ በሄ/ር 46024 የታቀደ ሲሆን የተዘራ ክንዉን 46112 ሄ/ር መከላከል የተቻለዉ በ1ኛ ዙር 46112 ሄ/ር በ2ኛ ዙር 42547 ሄ/ር በ3ኛ ዙር 0 ሄ/ር ሰብል አረም መከላከል ተችሏል፡፡

በተለያዩ የሰብል አይነቶች 11110  ሄ/ር የሰብል ስብጠር ልማት ለማልማት በእቅድ ተይዞ ጠቅላላ የተዘራ ዋና ሰብል በሄ/ር 22092፣ጠቅላላ የተዘራ 2ኛ ሰብል በሄ/ር 0 ተሳታፊ ወንድ 21178 ሴት 508 ድምር 18086 የተለያዩ የሰብል አይነቶች ማለትም ለበቆሎና ባቄላ፣በቆሎና ቦለቄ፤ማሻላና ቦለቄ፣ማሽላና በማቀናጀት የተሰራ ነዉ፡፡ዩሪያ ሳይድ ድሬሲንግ በዕቅድ 41610 የተዘራ 43326 ዩሪያ የተደረገበት 38530 ሲሆን የተሳታፊ ብዛት፣ዩሪያ መጠን 42421 ተሳታፊ ወንድ 49375 ሴት 2706 ድምር 52081 ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ግብዓት አጠቃቀም፡- የኮትቻ አፈር ልማት በገብስ እና ቦለቄ ሰብል እቅድ 178 ሄ/ር በ5 ክላስተር 168 ሄ/ር በቢኤም 0 በባህላዊ መንገድ 168 በድምሩ 168 ሄ/ር መሬት ማንጣፈፍ ስራ መስራት ተችሏል፡፡የተሳተፈ 292 ለገብስ 118 ቦለቄ 47 በድምሩ 337 በባህላዊ ዘዴ ጥቁር አፈር ማንጣፈፍ ተችሏል፡፡

የህያዉ ማዳበሪያ ልማት ፡- ባቄላ፣አተርና ቦለቄ ሰብል በድምሩ 2850 ሄ/ር፣የተመለመለ ወንድ 412 ሴት 0 ድምር 412፣የተሰራጨ 412 ሳቸት፣ጥቅም ላይ የዋለ 412 የለማ መሬት በሄ/ር 103 ተሳታፊ ወንድ 412 ሴት 0 ድምር 412

በኖራ አጠቃቀም 14 ቀበሌዎች የተጠቀሙ ጠቅላላ የቀረበ ኖራ 2650 የተሰራጨ ኖራ 2650፤የተበተነ ኖራ መጠን በኩ/ል 2132  ይህም በመሬት ስፋት 106 ሄ/ር ማድረስ ተችሏል፡፡

 የተገዛ ግብጦ 48፤ የተሰራጨ ግብጦ 12፣የተዘራ የማሳ ስፋት በሄ/ር 40 ተሳታፊ ወንድ 127 ሴት 6 ድምር 133፣የተዘጋጀ ኮምፖስት እቅድ 37497 በሄ/ር  ተይዞ 13642 ሄ/ር  በተሳታፊ ወንድ 18437 ሴት 954 ድምር 19391ማድረስ ተችሏል፡፤የተስቦ ትል ወይም ቨርሚ ኮምፖስት ዝግጅት በተመለከተ በነባር 281 በአዲስ 111 በድምሩ 392 በቁጥር በማዘጋጀት 870 ኩ/ል ኮምፖስት በማምረት በ25ሄ/ር ላይ  500 ኩ/ል መበተን ተችሏል፡፡

የማዳበሪያ አጠቃቀም ያለበት ሁኔታ የተዘራ መሬት በሄ/ር 46612 ጥቅም ላይ የዋለ ማዳበሪያ መጠን ኤንፒስ 80572፣ዩሪያ 16244 ድምር 96086 ጥቅም ላይ መዋል ችሏል፡፡

  በ2013/14 የምርት ዘመን ቴክኖሎጂና የተሻሻለ አሰራርና አጠቃቀም 46162 ሄ/ር ሊዘራ የታቀደ ሲሆን ጠቅላላ የተዘራ 46112 ሄ/ር/99.8%/፣ለማዳበሪያና ለም/ዘር የተዘራ 12075.1 ሄ/ር /23.18%፣ለአካባቢ ዘርና ለማደበሪያ የተዘራ በሄ/ር 33739/60.9%/፣በኮምፖስትና በአካባቢ ዘር የተዘራ 250.94 ሄ/ር/3.9%/፣በአካባቢ ዘር ብቻ 19.534 ሄ/ር/13.71/፣በመስመር የተዘራ 34253/70.17%/ ተሳታፊ ወንድ 22222 ሴት 2300 ድምር 24522 ነዉ፡፡

 የ2013/2014 ምርት ዘመን ዘር ብዜት ስንዴ (ኦገልቾ) ፤ቦሩ፤ዱርሳ፤ሊሙ ዝርያ ሙከራ የታቀደ ምርጥ ዘሮች ናቸዉ፡፡ በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅትና በአማራ ምርጥ ዘር ድርጅት በ32 ክላስተር በ2350 አባላት 1143.5 ሄ/ር የማሳ ስፋት ላይ ተከናዉኗል፡፡ከመስኖ ጋር በተያያዘ በ2ኛ ዙር መስኖ የታረሰ መሬት በዕቅድ 730 ሄ/ር ሲሆን በክንዉን 78 ሄ/ር፤በ2ኛ ዙር መስኖ የተዘራ መሬት 103 ሄ/ር፤የዘራዉ በሰብል ዓይነት አዝርዕት 37.1 ሄ/ር፤ስንዴ 22 ሄ/ር፤በቆሎ 12.1 ሄ/ር፤አትክልት 280.65 ሄ/ር ይሸፍናል፡፡በዚህም 2920 አርሶ አደሮችን ለማሳተፍ ታቅዶ 2473 አርሶ አደሮችን ለማሳተፍ ተችሏል፡፡

ከመስኖ ልማት አኳያ የ1ኛ ዙር መስኖ በነባር 1523.4 ሄ/ር በአዲስ 267 ሄ/ር በድምሩ 1790.4 አዝርት 590 ሄ/ር፤አትክልት 399.4 ሄ/ር፤ስራስር 5.25 ሄ/ር፤ቀ/ቅመም 77.25 ሄ/ር፤ጥራጥሬ 153.5 ሄ/ር፤አንቂ ተክል 255 ሄ/ር፤ቋ/ተክል 310 ሄ/ር ማልማት ሲቻል በ2ኛ ዙር መስኖ 598 ሄ/ር በአዝርት ሲሸፍን ስንዴ 37.1 ሄ/ር፤አትክልት 410.15 ሄ/ር፤ቅመማቅመምና በርበሬ 72 ሄ/ር፤ስራስርና ድንች 70 ሄ/ር፤ጥራጥሬ ማሾ 8.75ሄ/ር፤ቋሚ ተክል ና ሸንኮራ አገዳ 598 ሄ/ር መሸፈን ተችሏል፡፡

ከተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ አኳያ 18.13 ሚሊዮን ችግኝ ለማፍላት ታቅዶ 16.33 ሚሊዮን ችግኝ በማፍላት፤938.505 ሄ/ር የደን ትከያ ቦታ ለመለየት ታቅዶ 816.81 ሄ/ር በመለየት 8.2 ሚለየን ገርጓድ በማዘጋጀት፤87.0 ሄ/ር መሬት ላይ ለመትከል ዝግጅት አልቋል፡፡

1969.24 ሄ/ር የማሳ ላይ እርከን ስራ፤1890.92 ሄ/ር የእርከን ጥገና፤የማሳ ላይ እርከን ደረጃ ማሳደግ  1765 ሄ/ር፤የሳር ሸንተር እርከን ስራ 164.3 ሄ/ር፤ጎርፍ መቀልበሻ ቦይ ስራ 57.4 ኪ/ሜ፤ወሃ ማፋሰሻ ቦይ ስራ 67.65 ኪ.ሜ፤የአገገሙ ተራራማ መሬቶችን ባለቤት መስጠት 75 ሄ/ር፤የተራቆቱ መሬቶችን መከለል 36 ሄ/ር፤የጋራ ላይ እርከን ስራ 2.75 ሄ/ር፤የጋራ ላይ እርከን ደረጃ ማሳደግ 33.1 ኪ.ሜ፤የቦረቦር ልማት 52  ሄ/ር፤የክትር ስራ 52 ሄ/ር፤ለመስራት 591838 በድግግሞሽ የተሳተፈ የሰዉ ሀይል ማከናወን ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ በ55 ነባር ተፋሰስ ፤በ22544 ሄ/ር መሬት ወደ ስራ ለማስገባት ታቅዶ 1618.22/7.1%/ ብቻ ማከናወን ተችሏል፡፡ለዚህም ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በወረዳ አመራር አለመደረጉ በመንስኤነት ተቀምጧል፡፡

2.የእንስሳት ሃብት ልማት

 ከድህነት ቅነሳ ፕሮግራም መካከል የእንስሳት ሀብት ምርታማነት ከፍ በማድረግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከተቀመጠዉ የፖሊሲ አቅጣጫ አንጻር፡-የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል በተመለከተ በተፈጥሮ ድራት የዳልጋ ከብት ማዳቀል እቅድ 760 ክንውን 564 አፈፃፀም 74.2% በተሻሻለ ዝርያ ላሞች/ጊደሮች ቁጥር ዕቅድ 266 ክንዉን 68 አፈፃፀም 25.56% ሲሆን የተወለደ እንስት 156 ተባዕት 151 በድምሩ 207 የማዋለድ ስራ ተሰርቷል፡፡በተሻሻለ በኮርማ ማዳቀል እቅድ 600 ክንውን 670 አፈፃፀም 101.5% ከዚህም ዉስጥ ተዳቅለዉ  የተወለደ ተባዕት 197 እንስት 104 በድምሩ 367 የማዋለድ ስራ ተሰርቷል፡፡ ከተሻሻለ የደሮ አቅርቦትና ስርጭ አኳያ በመደበኛ የ1 ቀን ጫጩት እቅድ 21107 ክንዉን 25395/100%/

ከእንስሳት ማድለብ አኳያ፡-የዳልጋ ከብት ማድለብ እቅድ 12861 ክንውን 13552 አፈፃፀም 100% የደረሰ ሲሆን በግና ፍየል  ማድለብ  እቅድ 55972 ክንውን 56573 አፈፃፀም 100% ከብት በግና ፍዬል የተሳተፉ ወንድ 3336 ሴት 26 ድምር 3362 ናቸው፡፡ 

  የንብ እርባታ ስራ ለማሳካት በመጀመሪያ ደረጃ በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ያሉትን የክህሎት ክፍተት  ለመሙላት የቀበሌ ሙያተኞችን በንብ ማዛወር  ስልጠና ተሰርቶ  ወደ ተግባር  ለመግባት ጥረት ተደርጓል፡፡ የተሰራ የሽግግር  ቀፎ እቅድ 437 ክንውን 398 አፈፃፀም 91.07%፣ወደ ዘመናዊ ቀፎ ንብ ማዛወር 407 የታቀደ ሲሆን እስከአሁን 210 የማዘወር ስራ፣ወደ ሽግግር እቅድ 239 ክንዉን 215 አፋጻጸም 93 በአጠቃላይ የተመረተ ማር ምርት ከሶስቱ የቀፎ አይነቶች እቅድ 83 ክንዉን 93.5 ቶን ሲሆን አፈጻጸም 112.10% በዚህም ተሳታፊ የሆኑ አ/አደሮች ብዘት 0 ሲሆኑ የተሰራጨ ዘመናዊ ቀፎ ብዛት 46 ነዉ፡፡ የሽ/ቀፍ መስራች 437 ታቅዶ 19 ሽ/ቀፎ በ0 አ/አደር ተሰርቷል፡፡በዚህም 0 ቶን ተመርቷል፡፡

 

ከመኖ ልማት አንፃር ፡-የግጦሽ መሬትን በመስኖ ልማት እቅድ 66.35 ክንዉን 37.5ሄ/ር አፈጻጸም 56.52 %፣የተመጣጠነ መኖ ስርጭት እቅድ 221.66 ክንዉን 128.5 ቶን አፈጻጸም 57.97%

   የክትባት አገልግሎት በተመለከተ፡-  አባ ሰንጋ  ክትባት  ዳልጋ  ከብት፣ በግና ፍየል ጋማ ከብት  በድምሩ እቅድ 404250 ክንውን 188114 /46.5%/ እንስሳት የክትባት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል፡፡ አባ ጉርባ/ዳልጋ ከብት/እቅድ 16551 ክንውን 6500/39.3%/፤ ጉሮርሳ ለዳልጋ ፤ከብት ፣ በግና ፍየል እቅድ 23531 ክንውን 11264 ፣ የበጎችና ፍየሎች  ፈንጣጣ  እቅድ 47477 ክንውን 26638፣አጉረብርብ /ዳልጋ ከብት/ እቅድ 50173 ክንውን 37666፣ የአፍሪካ  የጋማ ከብት  በሽታ  እቅድ  21384 ክንውን 9467/44.3%/፣ተላላፊ የደሮ በሽታዎች  ፈንገስ፣ጉምበሮ  ፈንጣጣ እና የደሮ  ታይፎይድ  እቅድ 136023 ክንውን 22700/216.7%/ እንስሳት የክትባት  አገልግሎት  እስከዚህ  ሩብ አመት  ማግኘት ችለዋል፡፡

የቅድመ መከላከል ህክምና ከውስጥ ጥገኛ የቁም እንስሳትን ለመከላከል በእቅድ 91658 ተይዞ 36258/39.5%/ እንስሳትን የቅድመ መከላከል ህክምና ስራ ማከናወን ተችሏል፡፡

 የህክምና አገልግሎት በእንስሳት  ዝርያ  ለውስጥ  ጥገኛ/ለታመሙ/ ዳልጋ  ከብት  በግና ፍየል  ጋማ ከብት  እና ሌሎች  በተመለከተ  እቅድ 21890 ክንውን 32663/149.2%/፣ ለውጭ ጥገኛ ዳልጋ ከብት በግና ፍየል ጋማ ከብት ሌሎች እቅድ 14593 ክንውን 8310/56.9%/፣የገንዲ ህክምና   ዳልጋ ከብት   በግና ፍየል ጋማ ከብት ሌሎች እቅድ 18125 ክንውን 5960፤ ልዩ ልዩ ህክምና እቅድ 21890 ክንውን 14252፣የኩልሸት አገልግሎት ለዳልጋ ከብት በግና ፍየል ጋማ ከብት እና ሌሎ እቅድ 3648 ክንውን 100/2.7% እንስሳት የማኮላሸት ስራ መፈፀም ተችሏ

 

  1. ንግድ ኢንዱስትሪ ገበያ ልማት

  ፍትሃዊ የንግድ ዉድድር እንዲሰፍን በማድረግ አምራቹን፣ሸማቹንና የንግድ ማህበረሰቡን ሊያረካ የሚችል የንግድ አሰራር ስርዓት መፍጠር የህብረተሰቡን ጤንነት ደህንነት ሊጎዱ የሚችሉ ከጥራት ደረጃቸዉ በታች የሆኑ ምርቶችና አገልግሎቶች በገበያ ላይ እንዳይዉሉ ጠንካራ ክትትልና ቁጥጥር ስራ በመስራት የተረጋጋ ገበያ ከመፍጠር አኳያ፡-    በተለያዩ ዘርፎች  ለንግድ ማህበረሰብ ፣ለባለሀብትና ለደንበኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠት በእንስሳት ተዋጸኦ እቅድ 1095 ክንዉን 1710/156%/፣በንግድ ውድድርና ሸማቾች እቅድ 1824 ክንዉን 3341/100%/፣በንግድ ምዝገባና ፍቃድ እቅድ 1205 ክንዉን 1205/100%/፣በሰብል ግብይት እቅድ 1591 ክንዉን 840/100%/ መስጠት ተችሏል፡፡

አዲስ ንግድና ምዝገባ አገልግሎት በዓመቱ 466 ለማከናወን ታቅዶ እስከዚህ ሩብ ዓመት 633 ማከናወን ሲቻል አፈፃፀሙ >100% ማድረስ ተችሏል የንግድ ምዝገባ እድሳት የአመቱ እቅድ 2845 ክንዉን 2280/80%/፣አዲስ የተሰጠ የንግድ ፍቃድ ዕቅድ 667 ክንዉን 694/100%/፣ የንግድ ምዝገባ ማሻሻያ መስጠት ዕቅድ 144 ተይዞ 56 መፈፀም ተችሏል በዚህም 38.8% ማከናወን ተችሏል፡፡

ከንግድ ውድድር ሸማቾች ጥበቃ አኳያ መሰረታዊ ምርቶች አቅርቦት ስርጭት ስኳር የዓመቱ እቅድ 1394 ኩ/ል ሲሆን ክንውኑ 1312 ኩ/ል በማሰራጨት አፈጻጸም 94.11%፤የዳቦ ዱቄት የዓመቱ እቅድ 233 ኩ/ል ክንውን 233 ኩ/ል 100%፤  የፓልም ዘይት በሊትር የዓመቱ እቅድ 270000 ሊትር ክንውን  61050 ሊ/ር 22.6%፤ ህጋዊ የመሸጫ ደረሰኝ ያላቸውና እንዲያዘጋጁ የተደረጉ ድርጅቶች ብዛት እቅድ 900 ክንውን 1580/>100%/፤

ከኢንስፔክሽንና ሪጉሌሽን አንጻር ለ3652 የንግድ ምዝገባና ፍቃድ እድሳት አሰጣጥ የውስጥ ኢንስፔክሽን ማካሄድ በዕቅድ ተይዞ 3894 />100%/፣ የውጭ ኢንስፔክሽን የድርጅት በር ከበር ማካሄድ 7920 ታቅዶ 11496/>100%)፣ የመለኪያ መሳሪያ ቬሪፊኬሽን እቅድ 3799 ክንውን 3544/100%/፣የመለኪያ መሳሪያ ኢንስክት ማድረግ እቅድ 13717 ክንዉን 13200/100%/ ማከናወን ተችሏል፡፡የዉጭና የዉስጥ ኢንፔክት በማድረግ የመጣ ለዉጥ/የተወሰደ እርምጃ ለ10 የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ለ993 እሽጋ የተደረገ፣ስረዛ የተደረገባቸው 8 በአጠቃለይ ለ191 ነጋዴዎች እርምጃ ተወሰወዷል፡፡

 ከቁም እንስሳት ተዋጽኦ ግብይት ኳያ በጉዞ የተሸኘ የቁም እንስሳት ብዛት ዳልጋ ከብት በግና ፍየል እቅድ 1416 ክንዉን 185/13%/ ለሀገር ውሥጥ የቀረበ ቆዳናሌጦ ብዛትየበግ/የፍየል ሌጦ ዕቅድ 1023 ክንውን 502/49%/ ለሀገር ውሥጥ የቀረበ የእንስሳት ተዋፅኦ ለገበያ የቀረበ ዶሮ 7400፤እንቁላል 35314፤ወተት በሊትር 648፤የማር ምርት ትስስር 420 ቶን ፣እንስሳት መኖ 10 ዕቅድ ተይዞ  እስከዚህ ሩብ ዓመት ክንዉን ዶሮ 9600/85.7%/፤ እንቁላል 29430/79.28%/ ፤ወተት በሊትር 540000/100%/ ፤የአይብ ትስስር 0/0%/ ቶን ፤የማር ትስስር 244/68.62%/ ቶን፡፡

 

  1. ስራና ስልጠና አንፃር

የስራ ፈላጊ ዜጎችን የክህሎትና የምርታማነት አቅማቸዉን እንዲያሻሽሉ በማድረግ ሰፊ የስራ እድል በመፍጠርና ገብያቸዉን በማሳደግ ድህነት በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስበትንና ኢንተርፕራይዞች የልማታዊ ባለሀብቶች መፍለቂያና የኢንዱስትሪ ልማት የሚሆኑበት አቅጣጫ በመከተል ሴቶችን፣ወጣቶችን፣አካልጉዳተኞችን፣ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተያዘዉ አቅጣጫ መሰረት፡-በበጀት አመቱ በወረዳዉ በከተማ የተመዘገቡ ስራ ፈላጊ እቅድ 2649 ክንዉን 1806/68.18%/፣በገጠር የተመዘገቡ ስራ ፈላጊ እቅድ 5370 ክንዉን 5226/97.3%/ ጠቅላላ የተመዘገበ ስራ ፈላጊ እቅድ 8019 ክንዉን 7032/87.6%/ ስራ ፈላጊ  የተመዘገበ መሆኑ፡፡በአንቀሳቃሽ በስራ ፈላጊዎችና ስራ ፈላጊ ወላጆች ዙሪያ የሚታዩ የአመለካከት የክህሎት ክፍተትን በመለየትና ስልጠና በመስጠት በዘርፋ ልማት ተሳታፊ ለማድረግ ለ8019 ስራ ፈላጊ፣ለ8019 ስራ ፈላጊ ወላጆች፣4010 ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ለ314 የዩኒቨርስቲ ምሩቃን፣909 ቴክኒክ ምሩቃን፣ለ7 አካል ጉዳተኞችና 20 ከስደት ተመላሽ በድምሩ 21298 የህ/ሰብ ክፍል ግንዛቤ ለመፍጠር ታቅዶ 7032/87.69%/ስራ ፈላጊ፣3962/85.22%/ስራ ፈላጊ ወላጆች፣1730/43.14%/ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ፣ለ0/0%/ የዩኒቨርስቲ ምሩቃን፣0/0%/ቴክኒክ ምሩቃን፣ለ0/0%/ አካል ጉዳተኛ የተፈጠረ;ከስደት ተመላሽ  ሲሆን በአጠቃላይ 6480/30.43%/ግንዛቤ የተሰጠ መሆኑ፡፡

 ገበያ ባላቸው ሙያዎች መደበኛ ባልሆኑ አጫጭር ስልጠና በኢንተርፕሪነርሽፕ በከተማ 2325 በገጠር 3670  በድምሩ 5995 ለመስጠት ታቅዶ በከተማ 2382/102.45%/ በገጠር 3412/92.97%/፣ ቴክኒካል ክህሎት በከተማ 850 ና በገጠር 1929 በድምር 2779 ለመስጠት በእቅድ ተይዞ 1183/139.18%/ ከተማና 1932/100.16%/ ገጠር ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

 የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር በዕድገት ተኮር ዘርፎች ክፍተትን መሰረት ያደረገ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት በመስጠት 80%  ብቁ እንዲሆኑ ማስቻልና 10 መሪ መዛኝ ማፍራት 4 ምዘና ማዕከል እንዲሆኑ ማድረግ የሚል ዕቅድ ታቅዶ ነባር በከተማና በገጠር 71 ኢ/ዝ 212 አንቀሰቃሽ በእቅድ ተይዞ 71/100%/ በኢ/ዝ፣257/121.23%/ አንቀሳቃሽ  እንዲሁም አዲስ በከተማና በገጠር ለ36 ኢ/ዝ ለ106 አንቀሳቃሽ በእቅድ ተይዞ ለ36/100%/ ኢ/ዝና 135/100%/ አንቀሳቃሽ፡፡

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢ/ዞች የፋይናንስ ችግር ለመቅረፍ በመደበኛ የብድር አቅርቦት ለ243 ኢ/ዞች ለ729 አንቀሳቃሾች ብር 18231041.40 ለማበደር በእቅድ ተይዞ ለ182/74.9%/ኢ/ዝ፣ለ525/72.02%/አንቀሳቃሽ 27782000/72.02%/ ተሰራጭቷል፡፡

 የቁጠባ እንቅስቃሴ በተመለከተ ለ243 ኢ/ዞች ለ729 ተጠቃሚዎች ብር 18231041.4 ቁጠባ ለማስቆጠብ ታቅዶ 252 ኢ/ዝ/>100%/818/100%/12939454/70.97%/ብር ፣ማከናወን ተችሏል፡፡ተዘዋዋሪ ብድር አመላለስ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በከተማና በገጠር ለ20904627 ብር ለ49 ኢ/ዝ፣216 አንቀሳቃሽ የተሰራጨ ሲሆን በከተማ 12475769 በገጠር 5355304 በድምሩ 17831073 ብር ተመላሽ መሆን ችሏል፡፡

   በአጠቃላይ በወረዳዉ በበጀት አመቱ በከተማ  አዲስ ኢ/ዝ በማቋቋም የተፈጠረ የስራ እድል እቅድ 4414 ክንዉን 1874/53%/፣ነባር በማጠናከር እቅድ 1047 ክንዉን 302/29.3%/፣በከተማ የመንግስት ፕሮጀክት እቅድ 1356 ክንዉን 7006/100%/ ፣የከተማ የመንግስት ሰራተኞች ቅጥር እቅድ 507 ክንዉን 35/6.9%/፣መፍጠር ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ በገጠርና ከተማ  ቋሚ ወንድ 1743 ሴት 633 ድምር 2376 የስራ እድል  ጊዚያዊ ወንድ 5952 ሴት 894 ድምር 6846 በአጠቃላይ ቋሚ ጊዜያዊ ወንድ 7695  ሴት 1527 ድምር 9222 የስራ እድል ተፈጥሯል፡፡

  1. ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ

የበጀትዝግጅትአስተዳደርና የመንግስታት ትብብር  አንፃር

  የወረዳዉን የ2014 በጀት አመት ክልል ባሳወቀዉ መሰረት ከመንግስት ግምጃ ቤት 275942435 ብር ሲሆን ከክልል ድጎማ 0 ብር፣ከወረዳ የሚሰበሰብ 80145056 ብር እንዲሁም የጤና ጣብያ የዉስጥ ገቢ 10643877 ብር ቴ/ሙያ ኮሌጅ ብር 0 ሲሆን አጠቃላይ 286586312 ብር የተመደበ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ ለደመወዝ 243508937 ብር ፣ለስራ ማስኬጃ 34543209 ብር እና ካፒታል 8648000 ብር እንዲሁም የዉስጥ ገቢ 10643877 ብር በተገቢዉ የበጀት መደልደያ ኮድ በመጠቀም መደልደል ተችሏል፡፡የጸደቀዉን በጀት በአይቤክስ በመመዝገብ ለእያንዳንዱ ተቋም መ/በማ/4 ለማዘጋጀት ለ40 በጀት ተጠቃሚ ተቋማት ማሰራጨት ተችሏል፡፡

    የ4ኛ ሩብ አመት የበጀት አፈጻጸም ስንመለከት የተስተካከለ ለደመወዝ ብር 243508937 ብር ስራ ላይ የዋለ 156496866.43 ብር ቀሪ 87012070.57 ብር አፈጻጸም 64.3% የተስተካከለ ስራ ማስኬጃ ብር 34543209 ብር ስራ ላይ የዋለ 16829076.52 ብር ቀሪ 17714132.48 ብር  አፈጻጸም 48.72% እና ለካፒታል ብር 8648000 ብር ስራ ላይ የዋለ 2309323.96 ብር /26.7%/ቀሪ 6338676.07

 ከፋይናንስ አኳያ፡- ጠቅላላ የተመደበ መደበኛ በጀት 276272134 እስካሁን የተለቀቀ የዉጭ መርጃ 206715083 እስከአሁን የተሰበሰበ 62406240.23 ከዚህ ዉስጥ ለ28 ሴክተር መ/ቤቶች ለ2624 ሰራተኞች የተስተካከለ ደመወዝ በጀት 241304891 ሲሆን ስራ ላይ የዋለ 237956437.64/98.61%/ ቀሪ 3348453.36 ብር ነዉ፡፡ በመደበኛ ስራ ማስኬጃ በተመለከተ በተመሳሳይ ለ28 ሴክተር መ/ቤቶች የተመደበ በጀት 25952113 ስራ ላይ የዋለ 23797517.05 /91.69%/ ቀሪ 2154595.95 ሲሆን ካፒታል የተመደበ 9015130 ስራ ላይ የዋለ 8902845.98/98.75/ ቀሪ 112284.02 ብር መሆኑን ያሳያል፡፡ ከክልል የፌደራል ክፍያዎች እስከአሁን የተለቀቀ የዉጪ መርጃ 27877982፣ ከክልልናተጠሪ የተመደበ ደመወዝ 24319441 ስራ ላይ የዋለ 24175614.04 ቀሪ 143826.96፣የተመደበ ስራ ማስኪያጅ 3604495 ስራ ላይ የዋለ 3604491.99 ቀሪ 3.01 ፣

የዉጭ መጋራት እስከዚህ ወር የተሰበሰበ 159394.19፣ቅድመ ግብር እስከዚህ ወር የተሰበሰበ 56947.47፣የጡረታ መዋጮ እስከዚህ ወር የተሰበሰበ 3167059.31 ብር፣የጡረታና ማህበራዊ ዋስትና የተላለፈ መጠን 3167059.31 ለማህበራዊ ጡረታ ዋስትና ተላልፏል፡፡

  ግዝ በድግግሞሽ 4 ጊዜ ግልጽ ጫራታ በማዉጣት ብር 1961547.99  በመደበኛ ግዥ መፈጸም ተችሏል፡፡በዉስን ጫራታ 18 ጊዜ በማዉጣት ብር 2292133.24 ብር ፣በቀጥታ ግዥ 13 ጊዜ የተደረገ ሲሆን ብር 1665891.13፤ከመደበኛ በጀት መፈጸም ተችሏል፣በፕሮፍርማ 4 ጊዜ በመደበኛ ጫራታ በማዉጣትም ብር 560570.38 ሲሆን/ 17 ጊዜ እርዳታ 854485.15  ብር ተችሏል፡፡በአጠቃላይ በበጀት አመቱ በግልጽ ጫራታ ፣በዉስን ጫራታ፣በፕሮ ፎርማ፣በቀጥታ ግኝ 56 ጊዜ ግዥ በመካሄድ ከመደበኛ በጀት 6480142.74 እና ከእርዳታ በጀት 854485.15  በድምሩ 7334627.89 ብር ግዥ ተችሏል፡፡

 በበጀት አመቱ 55 በተለያዩ ተቋማት ኦዲት ለማድረግ በእቅድ ተይዞ የተመረመሩ ተቋማት 60 አፈጻጸም /100%/ ት/ቤት 25 ፣ጤና ጣቢያ 3 ፣6 ግብርና /ኤፍቲሲ/ እና 1 እንስሳት ክሊኒክ፣ 1 ሚሊሻ ጦር መሳሪያ፣1 ጤና መድን፣1 አልማ ፣9 ኤፍቲሲ ቀበሌ አስተዳደር በድምሩ 60 ተቋማት ምርመራ ማድረግ ተችሏል፡፡የዘመኑ ግኝት 136055.26 የተመለሰ 48342.58 ከወጭ ቀሪ 87712.68 ቀሪ ነዉ፡፡ዉዝፍ የዞረ 1408316.98 የተመለሰ 870279.58 ከወጭ ቀሪ 538037.40 የዘመኑ+ ዉዝፍ ዞረ 1544372.24 ብር የተመለሰ 941262.36 ብር ከወጭ ቀሪ 603109.88 ብር በፍ/ቤት ክስ የተመሰረተበት  ለወረዳ 60858 ለዞን 263480.39  ዉሳኔ የሚሰጥበት በመመለስ ላይ ያለ በድርድር ብር 212801.21 እልባት ያላገኘ 61667.83 ነዉ፡፡

  1. ገቢዎች

የታክስ ከፋዩን ማህበረሰብ ስለግብር ትምህርት በመስጠት ለልማቱ ሊሆን የሚችል ኢኮኖሚዉ ያመጣዉን የግብር ገቢ ለመሰብሰብና ግብር ከፋዩ የግብር የመክፈል ሃላፊነቱን እንዲወጣ ለማስቻል የግብር ትምህርትና ኮምኒኬሽን ስራዎች በታቀደዉ መሰረት 14 መድረክ በማዘጋጀት ለወንድ 2944 ሴት 1297 ድምር 4241 ግንዛቤ ለመፍጠር በእቅድ ተይዞ 9 መድረክ በመፍጠር ለ2226 ግንዛቤ መስጠት ተችሏል፡፡ቤት ለቤት ትምህርት ስልጠና ለ ለወንድ 1238 ለ600 ለሴት ድምር 1838 ለሚሆኑ ግብር ከፋዩች ግንዛቤ ለመፍጠር በእቅድ ተይዞ ለወንድ 1176 ሴት 504 በድምሩ 1680/91.4%/ ግንዛቤ ተሰጥቷ፡፡

 በሚኒ ሜድያ የተሰጠ መረጃና ትምህርት በሚኒሜድያ ማስታዎቂያ ማስተላለፍ በዜና መግለጫ አዘጋጅቶ ለሚዲያ ማስተላለፍ በዕቅድ ተይዞ 1 ሰዓት ተይዞ 45 ደቂቃ ማስተላለፍ   ተችሏል፡፡በበራሪ ወረቀት ትምህርት ማስተላለፍ በ7 እትም 300 ቅጅ ለማስተላለፍ በዕቅድ ተይዞ በ5 እትም 186 ቅጅ ለማሰራጨት ተችሏል፡፡

   የደንበኛ አገልግሎት አሰጣጥ ፡-በተመለከተ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ቅሬታናይግባኝ አሰጣጥ  የቀረበ 32 አቤቱታዎች ቀርበዉ 32 ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ከግብር ጋር በተያያዘ 32 አቤቱታዎች ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ የቀረበ ሲሆን ለ30/93%/ አቤቱታ ቅሬታ በማጽናት በብር 459718 ሲሆን 2/6.4%/ አቤቱታ በመቀነስ  አቤቱታ ቅሬታዎችን በመጨመር የተወሰነላቸዉ ግብር ከፋይች ናቸዉ፡፡

በወረዳ ካሉት 1598 ግብር ከፋዩች ዉስጥ 30 ግብር ከፋዩች ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆኑ የብር መጠን 467748 ከዚህ ዉስጥ 0 ግብር ከፋይ  በመጨመር ብር ፣30 ግብር ከፋይ በማጽናት የተወሰነላቸዉ ሲሆን የብር መጠን 459718፣2 በመቀነስ የተወሰነላቸዉ  ብር መጠን 2030 ግብር ከፋይ ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ ግብር ታክስ በዛብኝ በማለት ለግብር ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ  የቀረቡ አቤቱታዎች በቁጥር 0 ሲሆኑ የብር መጠናቸዉ 0 ዉሳኔ የተሰጣቸዉ ግብር ከፋዩች የተቀነሰ/የጸና/ የብር መጠን በመጨመር 0 የብር መጠን 0 በማጽናት 0 የብር መጠን 0 በመቀነስ 0 የብር መጠን 0 ድምር 0 ብር፡፡   

ከገቢ አሰባሰብ አኳያ፡-በአዲሱ በጀት ዓመት በአዲስ ወደ ግብር መረቡ የገቡትን ነጋዴዎችና አከራይ ተብለው የተለዩትን በወቅቱ በመወሰን አሰራጭቶ ግብሩን ለመሰብሰብ የተቻለ ሲሆን በወረዳዉ ኢኮኖሚ በሚያመነጨዉ በብቃት ለመሰብሰብ ብር 69501175 ለመሰብሰብ በዕቅድ ተይዞ እስከዚህ ወር የተሰበሰበ 62406240.23 አፈጻጸም 89.8% ከተሰበሰበዉ ዉስጥ  ተጨማሪ እሴት ታክስ 707353 በእቅድ ተይዞ 127427/18%/፣ቲኦቲ ታክስ አሰባሰብ 6691609 በእቅድ ተይዞ 4390729.12/65.6%/፣ የኪራይ ገቢ 98800 በእቅድ ተይዞ 267681.95/271%/፣ሮያሊቲ ገቢ አሰባሰብ 150356 በእቅድ ተይዞ 1208469.33/>100%/፣የካፒታል ዋጋ እድገት ገቢ 452878 በእቅድ ተይዞ 222522.94/49.13%/፣የንግድ ትርፍ ገቢ አሰባሰብ 13490709 በእቅድ ተይዞ 8811216.72/65.3%/፣ሌሎች ገቢዎች 52026288 በእቅድ ተይዞ 48187865.13/92.62%/፣ወጭ መጋራት 301638.36 በእቅድ ተይዞ 278517.74/92.33%/ ፣ከሌሎች ድርጅቶች ተቀጣሪ የስራ ግብር 1101-2 እቅድ 4695928 ክንዉን 3191357.93 አፈጻጸም 68 %፣ቅድመ ግብር/ዊዝ ሆልድ ታክስ/ 31500 በእቅድ ተይዞ 6901.33/22%/፣ አሰባሰብ በዘርፍ ሲታይ በእርሻ ዘርፍ 5407158.38 በእቅድ ተይዞ 4320749.2337955.18/108.4%/፣በንግድ 13490709 በእቅድ ተይዞ 8811216.72/65.3/%/፣ሌሎች 52026288 በእቅድ ተይዞ 48187865.13/92.62%/ በድምሩ 69501175 በእቅድ ተይዞ 62406240.23/89.8%/ የተሰበሰበ ሲሆን በዋና ዋና የታክስ መደቦች  በቀጥታ ታክስ 56426696 በእቅድ ተይዞ 50523700.45/89.53%/፣ቀጥታ ያልሆኑ ገቢዎች 8601631 በእቅድ ተይዞ 5943115.2/69%/፣ታክስ ያልሆኑ ገቢዎች 4472848 በእቅድ ተይዞ 5939424.58/132.78%//በድምሩ 69501175 በእቅድ ተይዞ 62406420.23/89.8%/ መሰብሰብ ተችሏል፡፡

7.ህብረት ስራ ማህበራት ዘርፍ

   የህብረት ስራ ማህበራት 46 የግንዛቤ ፈጠራ መድረክ 6750 ተሳታፊዎች  ለመፍጠር በእቅድ ተይዞ   76 መድረክ፣2560/38%/ ተሳታፊዎች ግንዛቤ ፈጠራ ስራ ተስርቷል፡፡  በበጀት አመቱ ለ22 መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ለማጠናከር በእቅድ ተይዞ 15/68.2%/ ህ/ስ/ማህበር ማጠናከር የተቻለ ሲሆን የመሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራት ካፒታል ከነበረበት 2.6 ቢሊዮን ወደ 2.7 ቢሊዮን ለማድረስ በተያዘዉ ግብ መሰረት እንደ ወረዳ  በእቅድ ተይዞ 639963 ብር ጭማሪ ለማድረግ ታቅዶ 1490604.275 ብር  በማድረስ />100%/ ማድረስ ተችሏል፡፡በተጨማሪም በ5 ህ/ስ/ማ ፤12 አመራሮችን በመቀየር ለማጠናከር ተችሏል፡፡ከመ/ህ/ስ/ማ  ለ22 ትርፍ ክፍፍል ለማድረግ በእቅድ ተይዞ ለ8 ህ/ስ/ማ የተሰራ ሲሆን የተገኘ የተጣራ ትርፍ 1298730.284 ከዚህ ዉስጥ ለትርፍ ክፍፍል የዋለ ብር 553039.457 ዉሏል፡፡

   52 ጊዜ የገብያ መረጃ አገልግሎት ለመስጠት በእቅድ ተይዞ እስከዚህ ሩብ አመት 39/75%/ለመሰራት ተችሏል፡፡ከመሰረታዊ ህ/ስ/ማህበራት የተከሰተ ጉድለትን ከዘመኑ 392969.74 ከባለፉት ዓመታት 56251.61 በድምሩ 4499221.35 በድርድር ማስመለስ ሲቻል በፍ/ቤት ዉሳኔ የተመለሰ የለም፡፡በወረዳ ደረጃ ለ34 መ/ህ/ስ/ማህበር የኢንስፔክሽን አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ ለ13 መስጠት ተችሏል፡፤

  የኦዲት አገልግሎት በተመለከተ ለ10 ሁለገብ፤ለ12 የቁጣና ብድር፤ለ4 ሸማቾች በድምሩ ለ26 ማህበራት ለመስጠት ታቅዶ ለ17 ማህበራት/65.38%/ መስጠት ተችሏል፡፡በዚህም ጉድለት የታየባቸዉ ማህበራት ብዛት 9 ሲሆን፤ትርፍ ያገኙ ማህበራት ብዛት 14፤የተጣራ የትርፍ መጠን 2780244.10 ሲሆን 71506.36 ደግሞ ኪሳራ ታይቷል፡፡ለ26 መሰረታዊ ህ/ስ/ማህበራት የህግ ምክር አገልግሎት ለመስጠት እቅድ ተይዞ ለ1/0%

 8.አካባቢ ጥበቃና መሬት አስ/አጠቃቀም ዘርፍ አንፃር

ግብ1፡- በየደረጃው የመፈጸም አቅምን ለመገንባት ለባለሙዎች የአጭር ጊዜ ስልጠና መስጠት ለ54 ወንድ 53 ሴት በድምሩ ለ107 ስልጠና መስጠት ተችሏል ፡፡

ü ለቀበሌ ፤ለወረዳና ለዞን ባለሙዎች በሶፍትዌርና በካዳስተር በመሬትአስተዳደር ጽንስ ሃሳብና ተግባር ስልጠና በተቋማት በተደራጀ አግባብ መስጠት፤ለ46 ወንድ ለ39 ሴት በድምሩ 85

üለ87 ወንድ ለ56 ሴት ድምር 143 ለቀበሌ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኮሚቴ አባላት ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ ለ264 ወንድ ተሰጥቷል ፡፡

ግብ 2 የቀበሌ አመራሮችን የቀበሌና የን/ቀበሌ መሬት አስ/አጠ/ኮሚቴዎች የሚመለከታቸው የቀበሌ ባለሙያዎችና አርሶአደሮች የሚሳተፉበት በአጠቃላይ ስራወቻችን ላይ በቀበሌ ደረጃ ኮንፈረንሱን የሚካሄድ ቀበሌዎች ብዛት 22 ተሳታፊ ብዛት 13860 ወንድ 8426 ሴት 5434 እቅድ 10 መድረክ ወንድ 6093 ሴት 1670 በድምር 7763 ኮንፈረንስ ተካሄዷል ፡፡

ግብ 3 የ2ኛ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተርን የብድር ዋስትና በማድረግ ባለሙያዎች ብር የብድር ተጠያቂ ማድረግ

ü የባለይዞታ ቁጥር 45 ወንድ30 ሴት15 የሚበደሩት መጠን 359611 ታቅዶ 83 ባለይዞታ ወንድ 57 ሴት 26 ብር 1800000

ü ከግብይትውልምዝገባ የአገልግሎት ክፍያ መሰብሰብ ብር 1250 ታቅዶ 85800 ተሰብስቧል ፡፡

ግብ4፡- የሚቀርቡትን ሁሉንም የመሬት ግብቶች ማረጋገጥ፤ማጽደቅ፤በሠናላስመመዝገብ

ü  በ11 ናርሌስ ወረዳዎች የመሬት ልውውጥ ጸድቆ የተመዘገበላቸው ባለይዞታወች ብዛት 140 በእቅድ ተይዞ 13 መከናወኑ፣

üለ419 ስጦታ መርምሮ ማጽደቅና ደብተር መስጠት በእቅድ ተይዞ 144 መስጠት ተችሏል፡፡

ü ለ885 ያለኑዛዜ ውርስን መመዝገብና ለባለይዞታወች ደብተር መስጠት ታቅዶ ድምር 167 አፈጻጸም --

ü ለ140 የኪራይ ማጣራትና መመዝገብ ተይዞ 16 ለ311 ልማት ተነሺ ወቅታዊ ማድረግ በእቅድ ተይዞ 57 ፍርድ ቤት ውሳኔና ሌሎች ልዩ ልዩ 95 በእቅድ ተይዞ 232 መሰራቱ,

ግብ 5 በገጠር መሬት ያለውን ህገወጥ ተጠቃሚነትን ለመከላከል የመልካም አስተዳደር ችግሮች በ85% መቀነስ 

 üለ33 አላግባብ ይዞታወች ያጡ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍል መረጃ በማጣራት ይዞታቸው እንዲመለስላቸው ማድረግ

üለ2 ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት

üለ2 መጠቀም መብት የሌላቸው ግለሰቦች የያዙትን መሬት ማስመለስ

üለ810 ወንድ የተወረሩ መሬቶችን ማስመለስ

ü4250 ከመሬት ጋር ተያየዘው የሚነሱ አቤቱታና ቅሬታወች በቀበሌ ፤ በወረዳ ፤ዞንና ክልል መፍታት

üለ250 አዲስ መሬት ጠያቂዎችና ለስራ አጥ ወጣቶች ለቡድንም ይሁን ለተናጠል በቋሚነትና በጊዜአዊነት 65 ሄ/ር መሬት ለማቅረብ ታቅዶ ለ83 ተሰርቷል ፡፡

 በየደረጃዉ የመፈጸም አቅምን ለመገንባት ለ22 በላሙያዎችና ለ112 የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኮሚቴ አባላት የአጭር ጊዜ ስልጠናዎች በ1 መድረኮች ኮንፈረንስ በማካሄድ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ለማከናወን ታቅዶ ለ60 የቀበሌ መሬት አስተዳድር እና አጠቃቅም ኮሚቴ አባላት ስልጠና መስጠት ተችሏል፡፡ለ46 ወንድ ለ39 ሴት በድምሩ ለ85 ባለሙያዎች አጫጭር ስልጠና ለመስጠት ተችሏል፡፡

የመሬት ሀብት መረጃን ወደ ኮምፒዉተር ማስገባት፣ለ2 ቀበሌዎች ለ2748 ባለይዞታዎች 13738፤ማሳ ብዛት ና 12042 ማሳ ስፋት ለመፈጸም በእቅድ ተይዞ 2/100%/ቀበሌዎች የመሬት ሀብት መረጃን ወደ ኮምፒዉተር ማስገባት ፣ ለ2748/100% ባለይዞታዎች ፣13738 /100/ማሳ ብዛት፣የማሳ ስፋት በሄ/ር 325.34 መፈጸም መቻሉ፣

  ለ4 ቀበሌ የመሬት አጠቃቀም እቅድ ተዘጋጅቶ ርክክብ ባለይዞታዎች ለ4998 ፣ለ25711 ማሳ ብዛት ፣ለ12191.2877 ማሳ ስፋት በእቅድ ተይዞ ለ5 ቀበሌዎች ባለይዞታዎች 435፤ማሳ ብዛት 2303፤የማሳ ስፋት 426.1266 ለመፈጸም ተችሏል፡፡የመሬት አጠቃቀም እቅድ ተዘጋጅቶ ርክክብ ከተደረገላቸዉ ክትትልና ድጋፍ የተደረገላቸዉ ቀበሌዎች ብዛት 20፤ ባለይዞታዎች ለ17729 ፣ማሳ ብዛት 51840፣ለማሳ ስፋት 30733.0469 በእቅድ ተይዞ የቀበሌ 20፤ 8454 ባለይዞታዎች፣9423 ማሳ ብዛት፣ 3532.594 ሄ/ር የማሳ ስፋት ለመፈጸም ተችሏል፡፡

 በበጀት አመቱ የመሬት አጠቃቀም እቅድ ባልተዘጋጀባቸዉ ቀበሌዎች ነባሩ የመሬት  አጠቃቀም ያለጥናት እንዳይቀየር ቁጥጥር  የተደረገባቸዉ ቀበሌዎች እቅድ 2 ክንዉን 2፣ባለይዞታ ብዛት እቅድ 2748 ክንዉን 50፣ ማሳ ብዛት እቅድ 13738 ክንዉን 20 ፣ማሳ ስፋት ሄ/ር እቅድ 12042 ክንዉን 26.64 ማከናወን ተችሏል፡፡

  በበጀት አመቱ የመሬት አጠቃቀም እቅድ በተዘጋጀባቸዉ ቀበሌዎች  ቁጥጥር የተደረገባቸዉ ቀበሌዎች እቅድ 20 ክንዉን 19 ፣ባለይዞታ ብዛት እቅድ 2653 ክንዉን 2405፣ ማሳ ብዛት እቅድ 7763 ክንዉን 2599፣ማሳ ስፋት ሄ/ር እቅድ 4589 ክንዉን 1008 መፈጸም ተችሏል፡፡በገጠር መሬት በተለያዩ ምክንያት የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ሲለወጥ ወይም ሲታደስ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ሰነድ ማስተካከል የሚያስፈልጋቸዉን ለይቶ ወቅታዊ ለማድረግ ለ20 ቀበሌ፤ለ500 ባለይዞታ፤1986 የማሳ ብዛት፤375.25 ሄ/ር የማሳ ስፋት ለመስራ ታቅዶ በክንዉን ለ18 ቀበሌ፤ለ604 ባለይዞታዎች፤ለ1238 የማሳ ብዛት ለ488 ሄ/ር የማሳ ስፋት መስራት ተችሏል፡፡

ለህዝብ ጥቅም ሲባል መሬታቸዉን ለሚለቁ ባለይዞታዎች በህግ የተፈቀደዉን የካሳ መጠን በማስላት እንዲከፈሉ በማድረግና የልማት ተነሺዎችን መልሶ ለማቆቋም ተግባራትን ማከናወን ያስፈልጋል፡፡በዚህም መሰረት በበጀት ዓመቱ የሚለቁ ባለይዞታዎች ብዛት 391፤የሚለቀቀዉ የመሬት መጠን 97.82 ሄ/ር፤የሚገመት የካሳ መጠን 29.4 ሚሊየን ብር  በእቅድ ተይዞ እስከዚህ ወር የተነሱ 30 ባለይዞታ፣ የመሬት መጠን 8.2863 ሄ/ር ፣14519189.80 ብር የካሳ መጠን ለባለይዞታዎች በመለየት ካሳ መክፈል ተችሏል::

  1. ከባህልና ቱሪዝም ዘርፍ

   ባህል የማህበረሰብ ሀብት እንደመሆኑ የባህል ልማትና ሽግግር የህዝቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማረጋገጥ የክልሉ ህዝብ ከዘርፋ የሚያገኘዉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲያጠናክር ከምንጊዜዉም በበለጠ በመቀናጀት መስራት፣በእዉቀት ላይ የተመሰረተ ህብረተሰብ ለመፍጠር የሚደረገዉን ጥረት ለማገዝ የንባብ ባህልን የሚያዳብር ቤተ መጽሃፍትና ንባብ ቤቶችን የማስፋፋትና ለህዝብ ተደራሽ የማድረግ ተግባራትን ማከናወን ፤ክልሉ ያለዉን ተፈጥሮዊ፣ታሪካዊና ባህላዊ ሀብት በሚገባ በመለየት በማልማት እንዲሁም እምቅ የቱሪዝም ሀብታችን ለአለም ሀገራትና ለመላ ህዝባችን ማስተዋወቅ ክልላችን ከዘርፋ የሚያገኘዉን ገቢ ለማሳደግና የሚፈጠረዉን የስራ እድል ለማስፋት እንዲቻል ቀዳሚ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት በተያዘዉ አቅጣጫ መሰረት ፡- የወረዳዉን የባህልና የቋንቋዎች ልማትና አጠቃቀምን ማሳደግ በተቀመጠ ዓላማ የወረዳዉን ህዝብ ባህል ታሪክና ቋንቋ በማጥናት የሚተዋወቁበትንና የሚለሙበትን ሁኔታ መፍጠር በኩል የተሰበሰቡና የተደራጁ ልዩ ልዩ ስነ ቃሎች ብዛት በሰነድ ዕቅድ ..ክንዉን ..፤ የጥምቀት የመስቀል እና ሌሎች ክብረ በዓላት ባህላዊ አልባሳት በበዓሉ እንዲለበሱ በመድረኮች ግንዛቤ መፍጠር፤ ዕቅድ 1 ክንዉን 1 ፤የጎጂ አኗኗር ዘይቤዎች የጥናት ግኝትን ለማህበረሰቡ በመድረክ ማሳወቅ ዕቅድ 1 ክንዉን 1፤የእንግጫ ነቀላ እና ከስይ አጨዳ በአባላትን በዞን እና በወረዳ ደረጃ እንዲከበር ማድረግ እና በዓሉን ከትዉልድ ትዉልድ ለማስተላለፍ አልሞ መስራት በቁጥር 1 በማካሄድ 1 ጊዜ መስራት ፤ በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ዙሪያ መድረክ ማዘጋጀት  ዕቅድ..ክንዉን ..፤በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ዙሪያ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠር ከዚህ ዉስጥም 50% ሴቶች ያሳተፈ ለማድረግ ዕቅድ ወንድ 1500 ሴት 1500 ድምር 4000 ክንዉን ወንድ 1680 ሴት 1670 ድምር 4560 አፈፃፀም 100% ማድረስ ተችሏል፡፡ በወረዳዉ የኪነ-ጥበብና ስነ ጥበብ ፈጠራን ማጎልበትና ለህዝቡ የሚቀርብ ስራዎችን ማስፋፋት ለተጣለዉ ግብ መሰረት የስነ-ፅሁፍና የቅኔ ምሽቶችን ማካሄድ እቅድ 4 ክንዉን 6፤ለማካሄድ ወንድ 675 ሴት 675 ድምር 1350  በእቅድ ተይዞ ለወንድ 850 ሴት 779 ድምር 1629 ታዳሚዎችን ማሳተፍ ተችሏል፡፡

 የሀገር ውስጥ ቱሪስት ፍሰት በአምስቱ የቱሪስት ፍሰት ዘርፎች ማለትም በኮንፈረስ፤በእምነትና ክብረበዓላት፤በቢዝነስ፤በጤናናስፖርት በድምሩ 16239 ታቅዶ 22487 />100%/ማከናወን ተችሏል፡፡

 ከሀገር ውስጥ ቱሪስት ፍሰት የሚገኝ ገቢን ለማሳደግ በየዘርፉ ታቅዶ የተከናወነ ጠቅላላ የአገር ዉስጥ ቱሪስት ፍሰት ገቢ ዕቅድ 1242795 ታቅዶ 2934300/>100%/ተከናዉኗል፡፡

  1. ወጣቶችና ስፖርት ልማት አኳያ፡-

 የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራዎችን በማስፋፋት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ብቃት በመገንባት በተያዘዉ አገራዊ አቅጣጫ መሰረት ፡-የስፖርት ህዝባዊ አደረጃጀት አቅም መገንባት በተለያዩ የስፖርት መስኮች ክለቦችን ማጠናከርና አዲስ ማደራጀት  17 ክለቦችን ለማጠናከር በእቅድ ተይዞ 18 ፣1 አዲስ ክለቦችን ለማቋቋም ተይዞ …/0%/፣በወረዳ ደረጃ መመሪያን መሰረት በማድረግ የተደራጁ የስፖርት ፌዴሬሽን ማጠናከር ዕቅድ 11 ክንዉን 11 አፈጻጸም 100%፣በወረዳ ደረጃ የስፖርት ኮሚቴዎችን ማጠናከር ዕቅድ 26 ክንዉን 26 አፈጻጸም 100%፣የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራዎችን ማስፋፋት፡-በገጠር የተስፋፊ የማዝወተሪያ ስፍራዎች የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር እንዲኖራቸዉ እቅድ 3 ክንዉን... አፈጻጸም..%

 ሀብት በማሰባሰብ ተቋማዊ የፋይንንስ አቅምን ከማሳደግ አኳያ፡-ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ዕቅድ 51000 ክንዉን 480000 አፈፃፀም 94.1%፣የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ለልማታዊ ድርጅቶች ለባለሀብቶችና ለግለሰቦች በማቅረብ የተሰበሰበ ብር ዕቅድ 149978 ክንዉን .. አፍጻጸም ..%፤ከመንግስት ድጋፍ በደረጃዉ የተገኘ ገቢ ዕቅድ 639527 ክንዉን 150000 አፈጻጻም 23.4%፣በስፖርት ኢንቨስትመንት ባለሀብቶች እንዲሳተፋ ማድረግ፤በስፖርት ኢንቨስትመንት ዙሪያ ለ19 የህብረተሰብ ክፍሎች፣ለ19 አጋር አካላትና ባለሙያዎች ግንዛቤ ለመስጠት በእቅድ ተይዞ ለ12 ህብረተሰብ/..%/፣ለ12 አጋር አካላት/63.1%/መስጠት ተችሏል፡፡ለ2 ባለሀብት በስፖርት ኢንቨስትመንት እንዲሰማራ በእቅድ ተይዞ 1 ባለሀብት ተሰማርቷል፡፡

ግብ 1 ውጤታማ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን በመተግበር የኢኮኖሚ እድገት ሊያመጡ በሚችሉ ዘርፎች ላይ የኢቨስትመንት ፍሰቱን ማሳደግ ፡- 

የተከናወኑ ተግባራት

  • የማስተዋወቂያ መድረኮችን በማዘጋጀት በኩነቶች በመገኝት ኢንቨስትመንት ማስተዋወቅ የሚዘጋጅ ባለሃብት መደረክ ብዛት እቅድ 1 ክነውን 1 አፈጻጻም 100%፤ የሚዘጋጅ ፎርም ብዛት እቅድ 1 ክነውን 1 አፈጸጸም 100%፤የሚዘጋጅ ፕሮሸር ብዛት እቅድ 50 ክነውን 111 አፈጻጸም >100/ የሚሰረጭ ፕሮሸር ብዛት እቅድ 50 ክንውን111፣የሚዘጋጅ በራሪ ወረቀት ብዛት እቅድ 50ክንውን 60 አፈጸጸም 100%/ በራሪ ወረቀት ብዛት እቅድ 50 ክነውን 60 አፈጸጻም 100%
  • የተመለመሉና ፕሮፋይል የተዘጋጀላቸው ባለሃብቶች ብዛት እቅድ 15 ክነውን 14 አፈጸተም 93.3%፣ከተመለመሉት ውሰጥ ሳይት የጎበኙ ብዛት እቅድ 10 ክነውን 8 አፈጻጸም 80%
  • ለተለያዩ ማስተዋወቂያ መንገዶች ለተሰራ የማስተዋወቅ ስራ ፍቃድ ያወጡ ባለሃብቶች ብዛት እቅድ 11 ክነውን 13 አፈጻተም >100%፣ፍቃድ ባወጥ ባለሃብቶች የተመዘገበ ካፒታል እቅድ 0.042 ቢሊዮን ክንውን 0.528 አፈጻጸም 100%፣

ግብ2 ለኢንቨስትመንት ፐሮጀክት የሚውል 10ሄክታር መሬት ለማዘጋጀት እቅድ የተያዘ ሲሆን

  • ከኢንዱሰትሪ መንደር ፓርክ ውጭ ለሚቀርቡ ፕሮጀክቶች 3 ሄክታር መሬት ለማዘጋጀት እቅድ ተይዞ ክንውን 4.47 ሄ/ርአፈፃፀም>100% ማድረስ ተችሏል፡፡

ግብ 3 ፡-የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን በመገምገም፤ በመደገፍና በመከታተል በማምረት አገልግሎት በመስጠት ውጤታማና ዘላቂ እንዲሆኑ ማድረግ ፣

የተከናወኑ ተግባራት

  • የግብርና ፐሮጀክት ብዛት እቅድ 2 ክንውን 24 አፈጻጸም 100%
  • የአገልግሎት ሰጭ ፕሮጀክት እቅድ 6 ክንውን 7 አፈጻጸም 100%
  • ተገምግመው ያለፉ ኢንዱስትሪ ፕሮጀክት ብዛት እቅድ 7 ክነውን 7 አፈጻጸም 100%
  • የኢንተርፕርነርሽ ችግር የተለያባቸው እቅድ 11 ክንውን 11 አፈጻጸም 100%
  • ጥራትና ምርታማነት ችግር የተለየባቸው እቅድ 11 ክነውን 11 አፈጻጸም 100%
  • የቴክኖሎች አጠቃቀም ችግር የተለያቸው እቅድ 9 ክነውን 3 አፈጻጸም 33.3%
  • የሊዝ ፋይናንስ ችግር የተለያቸው ኢንዱስትሪዎች እቅድ 3 ክንውን 3 አፈጻጸም 100% ለመፈፀም ተችሏል፡፡

ግብ 4 ፡- ባህላዊ የማዕድን የማምረት ስራ ፍቃድ መስጠት

የተከናወኑ ተግባራት

  • በዚህ ሩብ አመት 4 የተሰጠ ሰሆን ተጠቃሚ ወይም አንቀሳቃሽ ብዛት 20
  • አመታዊ የማዕድን ገቢን በተመለከተ በዚህ ሩብ አመት የተሰበሰበ ገቢ 5184 እስከዚህ ሩብ አመት 7475
  • ከግብር የተሰበሰበ ገቢ በዚህ ሩብ አመት 6489 እሰከዚህ ሩብ አመት 26618
  • የተነሳ የማዕድን ምርት መጠን ከባህላዊ ማዕድን በዚህ ሩብ አመት 252 እስከዚህ ሩብ አመት 1390 ሜ.ኩ ደርሷል፡፡

4.2. መሰረተ ልማት

  1. መንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ

   በመንገድ ልማት ዘርፍ የወረዳዉን የገጠር መንገድ አዉታር ይዞታ በማሻሻልና ጥራቱን የጠበቀ የመንገድ አዉታር፣ የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽ በማድረግ የአጠቃላይ ልማትን ለማፋጠን በተቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት ፡- የመንገድ ተደራሽነት ለማሳደግ ከወረዳ 4885626.479 ብር ከህብረተሰቡ 4391730 ብር የተሰበሰበ ሲሆን የመንገድ ጥገና በማሽን 17.37 ኪ.ሜ፣በሰዉ 30.049 ኪ.ሜ አዲስ የመንገድ ግንባታ ስራ ማሽን የተጠረገ 19.5 ኪ.ሜ ፣የተጠረገበት ቀበሌ ደን፣ወንቱ እና ድንጓም ቀበሌ ማዕከል፣

በወረዳ መስመሮች በተዘረጉ መንገዶች የመንገድ ጥገና እና አዲስ መንገድ ግንባታ እቅድ 15 ኪ.ሜ  በማሽን ስራ ተይዞ 17.37 ኪ.ሜ በሰዉ ሀይል 35 ክንዉን በድምሩ 52 በኪ.ሜ ማከናወን ተችሏል፡፡

በወረዳችን ላይ ባሉ መስመሮች ላይ የተሸከርካሪና የአሽከርካሪን በመቆጣጠር 2 ትራፊክ 2 የመንገድ ደህንነትና ስምሪት ባለሙያዎች 570 መኪና የተከሰሰ ሲሆን 232850 ብር እንዲሁም በትራፊክ ፖሊሶች 446031 በድምሩ 678881 ብር ተሰብስቦ ለመንግስት ገቢ ተደርጓል፡፡

  1. 2. የውሃና ኢነርጅ ልማት ዘርፍ ፡-

    የወረዳዉ ህዝብ ጤናዉ ተጠብቆ በልማቱ የሚኖረዉን ተሳትፎ በማሳደግ የንጹሕ መጠጥ ዉሃ አቅርቦት ማሻሻልና ተጠቃሚ ለማደረግ በተቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት ፡- የሚገነቡ የውሃ ተቋማትን ህብረተሰቡ በባለቤትነት ስሜት  ለማስተዳደር ያስችል ዘንድ 150 አዲስ የውሃ ኮሚቴ ለማቋቋምና 420 ነባር የውሃ ኮሚቴ ለማጠናከር በእቅድ ተይዞ 160 አዲስና 425 ነባር የውሃ ኮሚቴ አባላት የማቋቋም ስራ ተሰርቷል፡፡ውሃ ጥገናን በተመለከተ ከህብረተሰቡ ጉልበት በገንዘብ 199500 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 304650 ሲሆን በቁሳቁስ 77169 ብር  የሚገመት ቁሳቁስ ከህብረተሰብ ለመሰብሰብ ታቅዶ 83125 ብር እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ 83125 ብር የሚገመት ቁሳቁስ ለማዉጣት ታቅዶ 108439 ብር በማዋጣት ብልሽት ያጋጠማቸውን 50 ቀላል ጥገና መከናወን ዕቅድ ተይዞ እስከዚህ ሩብ አመት 49 አፈጻጸም 99% የዉሃ ተቋማት ተጠግነዋል፡፡37 የተለያዩ የውሃ ተቋማት መካከለኛ ጥገና በእቅድ ተይዞ 59 ተቋማት ተጠግነዋል፤32 የተለያዩ የውሃ ተቋማት ከባድ ጥገና ለመሰራት ታቅዶ 73 እሰከዚህ ሩብ አመት ተቋማት ተጠግኗል፡፡ለዉሃ ተቋማት ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን ተጠግነዋል፡፡የወሃ ጥራት ጠብቆ ከመያዝ አኳያ የዉሃ ማከም ስራ ለ705 የዉሃ ተቋማትን ህክምና በመስጠት በሩብ አመት 1 ጊዜ ዉሃ ለማከም ታቅዶ ይህንን ለማሳካት 625 ተቋማት ለማከም ተችሏል፡፡

 ከመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሥራዎች አኳያ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ተቋማት ለመገንባት ከህብረተሰቡ በእቅድ ደረጃ በጉልበት 900000፣በቁሳቁስ 210000፣በጥሬ ገንዘብ ደግም 900000 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እስከአሁን 722000 በጉልበት እንዲሁም በቁሳቁስ በገንዘብ 308600 ብር በጥሬ ገንዘብ 454700 ብር በድምሩ 1485300 ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡በገጠር የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በመጀመሪያ ደረጃ የመጠጥ ውሃ መገኛ ለማጥናት በእቅድ 0 የገመድ ፓምፕ፣18 የእጅ ጉድጓድ ፣4 መ/ጥ/ጉ፤1 ምንጭ ና 5 ማኑዋል ድሪሊንግ እና 1 ጥልቅ ጉድጓድ በእቅድ ተይዞ አፈፃፀሙ 0 ገ/ፓምፕ፤ 18 እጅ ጉድጓድ፤3 ምንጭ፤ 2 ምንጭ ከመስመር ፣0 መ/ጥ/ጉ ፤ጥልቅ ጉድጓድ…፤ 1 ጥ/ጉ 2 ማኑዋል ድሪሊንግ  በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

 

የወረዳችን  ህዝብ ብዛት  173750 ውስጥ  የመጠጥ ውሃ  ተጠቃሚ  ህዘብ  87127 የወረዳ መጠጥ ዉሃ ሽፋን እስከበጀት አመቱ 50% በሚገነቡ የዉሃ ተቋማት ብቻ 4250 የወረዳ የመጠጥ ዉሃ ሽፋን በበጀት አመቱ በሚገነቡ የዉሃ ተቋማት በእቅድ ተይዞ ክንዉን 5790 አፈጻጸም>100% መሆኑን ያሳያል፡፡

  ገጠር ህዝብ ብዛት 158996 የገጠር  መጠጥ  ውሃ   ተጠቃሚ  ህዝብ  ብዛት  እስከ  በጀት  አመቱ   86690 ህዝብ  ሲኖር  ተጠቃሚ  የሆነ አፈፃፀም  75.5% ፣  የገጠር  መጠጥ  ውሃ  ሸፋን   72%  ለማድርስ ታቅዶ  አፈፃፀም   54.5 % ፣የገጠር  መጠጥ  ውሃ  ተጠቃሚ  ህዝብ  ብዛት  በጀት  አመቱ  ብቻ  እቅድ  4250  ተጠቃሚ  ህዘብ  5358  አፈፃፀም  >100%፣መሆኑን ያሳያል፡፡

የከተማ ህዝብ ብዛት 14885 የከተማ መጠጥ ዉሃ ተጠቃሚ ህዝብ ብዛት በቁጥር በበጀት ዓመቱ 432 ፤የከተማ መጠጥ ዉ ሽፋን 100% ለማድረስ ታቅዶ አፈፃፀም 100% ማድረስ ተችሏል፡፡ 

 የኢነርጅ ምንጮችና ቴክኖሎጅ ህብረተሰቡ እንዲላመዳቸውና ተጠቃሚ እንዲሆንባቸው ከማስቻል አኳያ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያየ የህዝብ መሰባሰቢያ ቦታዎች በመገኘት በተግባር ቴክኖሎጅዎችን ለማስተዋወቅ በአመት በእቅድ ደረጃ ለ1000 ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች እውቅና ለመፍጠር ታቅዶ ለ2400 የህብረተሰብ ክፍሎችን የኢነርጅ ምንጮች ቴክኖሎጅዎችን  በተግባር የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል፡፡ ለእነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ቴክኖሎጂ የማስተዋወቅ ስራ በመሰራቱ 3000 የተሸሻሉ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎች፣250 የኤሌክትሪክ ምድጃዎችን፤2500 ሶላር ሆም ሲስተም ስርጭት፣100 ባዮ ጋዝ ቴክኖሎጂ ለማድረግ በእቅድ ተይዞ 3168 የተሸሻሉ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎች፣683 ኤሌክትሪክ ምድጃ፣2780 ሶላር ማሾ፣75 ባዮ ጋዝ ቴክኖሎጂ  ምርት  ግንባታ ለህብረተሰቡ ለማሰራጨት ተችሏል፡፡

  1. መሪ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ዘርፍ

      የከተሞችን መሬት በቁጠባ መጠቀምን የሚያጠናክር በቂ የካሳና የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ በማድረግ የልማቱ የሚዉል መሬት በበቂ መጠን በቀጣይነት የማቅረብና በከተሞች የሚስተዋለዉን የቤት ፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣም ለማስወገድ የተጀመረዉን የቤት ልማት ፕሮግራም ለማስቀጠልና የመሰረተ ልማት ከማስፋፋት አኳያ በተያዘዉ አቅጣጫ መሰረት፡-

በከተማችን በሚከናወኑና ህብረተሰቡ ሊሳተፍባቸው በሚገቡ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሰረተ-ልማት ስራዎች የህብረተሰቡን ተሳትፎ ድርሻ 50% ለማድረስ ከዚህም 20% በገንዘብ፣ 15% በጉልበትና 15% በቁሳቁስ እንዲሆን በማድረግ በልማቱ ተሳታፊነቱን እና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ ታቅዶ በልማት ስራዎች ላይ ወንድ 739 ሴት 207 በድምሩ 946 ህብረተሰብ የተሳተፈ ሲሆን የጥሬ ገንዘብ መዋጮ ብር 823600 በጉልበት ብር 70950 በቁሳቁስ ብር 23650 በድምሩ ብር 918200 መዋጮ የተደረገ ሲሆን የህብረተሰብ ተሳትፎን 100% ማድረስ ተችሏል፡፡

  በሪፖርት ዘመኑ የፋይናንስ አቅርቦት ስትራቴጂ ሰነድ እና የአደረጃጀትና የአሠራር ሥርዓት በመተግበር በየጁቤ ከተማ 58764028 ሚሊዮን ብር ገቢ እንዲሰበስቡ በማድረግ የከተማችን የመሰብሰብና የመጠቀም አቅም 100% ለማድረስ ታቅዶ የፋይናንስ አቅርቦት ስትራቴጂ ሰነዱና የአደረጃጀትና የአሠራር ሥርዓቱ ለመዘርጋትና ወደ ትግበራ ለመግባት ነባራዊ ሁኔታውን መሰረት በማድረግ ከማዘጋጃ ቤት 537951 ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል፡፡ ከተሰበሰበው ገቢም 34643821.95 ብር መጠቀም ተችሏል፡፡ አፈጻጸሙም 98.9% ማድረስ ተችሏል፡፡

 በከተማ ፕላን ክልል ዉስጥ የሚገኘዉን በማንም ያልተያዘና በክፍትነት የሚገኝ  21.06 ሄ/ር በጊዚያዊነት የተላለፈ 0 ሄ/ር  መሬት በመቁጠር ለመመዝገብ ታቅዶ በክፍተት የሚገኝ 0 ሄ/ር እና በጊዜያዊነት የተላለፈ 0 ሄ/ር መሬት መቁጠርና መመዝገብ ተችሏል፡፡ በበጀት አመቱ 11.7047 ሄ/ር መሬት በጫራታና 0 ሄ/ር መሬት በምደባ በድምሩ 11.7047 ሄ/ር መሬት መሰረተ ልማት ተሟልቶላቸዉ እንዲዘጋጅ ለማድረግ ታቅዶ 0.8917 ሄ/ር መሬት በጫራታ እና 10.813 ሄ/ር መሬት በምደባ በድምሩ 11.7047 ሄ/ር መሬት የተዘጋጀ ሲሆን አፈጻጸሙ 0% ነዉ፡፡

  በከተማችን ለምቶ ወደ መሬት መረጃ ባንክ ከገባዉ መሬት ዉስጥ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚዉል 0 ሄ/ር መሬት በምደባ እንዲተላለፍ ለማድረግ ታቅዶ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚዉል 0 ሄ/ር ቦታ በምደባ ለተጠቃሚዎች የተላለፈ ሲሆን አፈጻጸሙ 0 ነዉ፡፡በበጀት ዓመቱ ውስጥ መስፈርቱን አሟልተው ለተገኙ 0 የመኖርያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት ቦታ ለመስጠት በእቅድ ተይዞ ለ0 የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት 0 ሄ/ር መሬት በመስጠት ወንድ 0 ሴት 0 በድምሩ 0 የቤት ህብረት ስራ ማህበራት አባላትን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

  በየጁቤ ከተማ በሊዝ እና ኪራይ ለተጠቃሚዎች ከተላለፋ ይዞታዎች ከሊዝ ቦታዎች 32 ሚሊዩን እንዲሁም ከኪራይ ይዞታዎች 0.270528 ሚሊዩን ብር በድምሩ 32.27 ሚሊዩን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ በ1 ከተማ ከሊዝ ቅድመ ክፍያ  1111552.7 ብር፣ከዓመታዊ የሊዝ ክፍያ 786828.97 ብር ከአመታዊ የቦታ ኪራይ 133269.73 በአጠቃላይ 2.031 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡ከስመ ንብረት ዝዉውር ጋር በተያያዘ  በበጀት አመቱ ዉስጥ  ከቀረቡ 1344 ጉዳዩች ዉስጥ 1275(94.87%)አገልግሎት ፈላጊዎች አገልግሎት አግኝተዋል፡፡

  በፕላን ለተመላከቱ 33 የአረንጓዴ ቦታዎች በመለየት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲሰራላቸው ለማድረግ ታቅዶ ለ18 ቦታዎች ካርታ የተሰራላቸዉ ሲሆን 15 ደግሞ ያልተሰራላቸዉ ናቸዉ፡፡0.95 ሄ/ር ነባር የለሙ አረንጓዴ ቦታዎችን ለመንከባከብ ታቅዶ 0.95 ሄ/ር እንክብካቤ ተደርጎላቸዋል፡፡ እንዲሁም በከተሞች ለ 5 ነባር ፓርኮች እንከብካቤ ለማድረግ ታቅዶ ለ5 ፓርኮች እንክብካቤ ተደርጓል፡፡የተቀናጀ ደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ስርዓት በመዘርጋት 1 ከተማ የተመደበላቸዉን የፕላን ምደብ ቦታ መሰረት 2564 ሜ.ኩ ደረቅ ቆሻሻ እንዲያስወግዱ ለማድረግ ታቅዶ 2500.65 ሜ.ኩ ደረቅ ቆሻሻ የተወገደ ሲሆን አፈጻጸሙ 99% ነዉ፡፡

በህንፃ አዋጁ ተግባራዊ በሚደረግባቸዉ ከተሞች ለሚገነቡ ለ120 ግንባታዎች የፕላን ስምምነት ለመስጠት ታቅዶ 114 />95%/ የፕላን ስምምነት ለመስጠት ተችሏል፡፡በተጨማሪም ለ250 የግንባታዎች የዲዛይን ምርመራ ለማድረግ ታቅዶ 468 በመፈፀም >100% ፣250 የግንባታ ፍቃድ ለመስጠት ታቅዶ 163 /95%/ማከናወን ተችሏል፡፡የማይቀሳቀስ ን/ም/ወረቀት/ቋ/ካርታ መስራት በ 12 ወር የታቀደ ለመኖሪያ 350 ለንግድ 30 መ/ቤቶች 3 ለኢንዱስትሪ 2 እና ለከተማ ግብርና  ድምር 391 ታቅዶ ለመኖሪያ 396  ለንግድ 29 ለመ/ቤት 2 ለኢንዱስትሪ 2 ለከተማ ግብርና -- ሌሎች  ተከናውኗል፤ድምር 429/>100%/ ተከናውኗል ፡፡

4.3 የከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽን

የከተሞች መሰረተ ልማትና የእሰዳደር ወጪአቸዉን የገቢ አሰባሰብ አቅማቸዉን በማሳደግ እንዲሸፍኑ ለማድረግ በተያዘዉ አቅጣጫ መሰረት የኮርክ ታዳጊ ከተማ ገቢ ዕቅድ 4059560 የተሰበሰበ 1304956.67 አፈፃፀም 32% ፤የላምገጅ ታዳጊ ከተማ በዕቅድ 2068280 ታቅዶ 976296 በመሰብሰብ አፈፃፀሙ 47% መሰብሰብ ሲቻል ሁለቱም ከተሞች በመንግስት 500000 ለእያንዳንዳቸዉ የተደጎሙ ናቸዉ፡፡

ከወጪ አኳያ ለደመወዝ ኮርክ 536840፤ለስራ ማስኬጃ 358301፤ለካፒታል 270029.4 በድምሩ 1165170.4 የላምገጅ ታዳጊ ከተማ ለደሞዝ 331979፤ለስራ ማስኬጃ 84720.54፤ለካፒታል 389775.2 በድምሩ 806474.79 መሆኑን ያሳያል፡፡

4.3 ከማህበራዊ ዘርፍ

  1. ትምህርት አንፃር

በተደራጀ የትምህርት ሰራዊት በሁሉም ደረጃዎች የትምህርት ተደራሽነትን፣ጥራትንና ፍትሃዊነትን በማረጋገጥ የትምህርት ለሁሉምና ዘላቂ የልማት ግቦችን ማሳካት በሚል በተያዘዉ አቅጣጫ መሰረት፡-

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትን ለማሳደግ የጥራት ማስጠበቂያ ፓኬጅ ተነድፎለት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ከትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ አንጻር የትምህርት አመራር እና አደረጃጀት ንዑስ ፕሮግራም አተገባበር በተመለከተ የመምህራን፤የር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ዝዉዉርና  ምደባ ተጠናቆ ወደ ስራ በማስገባት የትምህርት ዘመኑን ትምህርት ማስጀመርና ማስቀጠል ተችሏል፡፡ከዚህ ባሻገር የት/ቤት ማሻሻያ ዕቅድ ማዘጋጅት በተመለከተ ስትራቴጅክ ዕቅድ ያዘጋጁ እና ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጁ ት/ቤቶች ቁጥር ዕቅድ 67 ሲሆን 67 ት/ቤቶች ማዘጋጀታቸዉን ያሳያል፡፡

የትምህርት ተሳትፎ ማሳደግ በተመለከተ በትምህርት ዘመኑ ለመማር የተመዘገቡ ወንድ 1ኛ ደረጃ ተማሪዎች እቅድ ወንድ 17183 ሴት 16990 ድምር 34173 በእቅድ ተይዞ በአመቱ መጀመሪያ የተመዘገቡ ወንድ 12884 ሴት 12804 ድምር 25688 መመዝገብ ተችሏል፡፡ ከዚህም ዉስጥ የ1ኛ ክፍል ጥቅል ቅበላ እቅድ ወንድ 2447 ሴት 2980 ድምር 5428 ተይዞ ወንድ 2283 ሴት 2065 ድምር 4348 በመመዝገብ የእቅዱን 80.1% መፈጸም ተችሏል፡፡

በንጥር ቅበላ እቅድ ወንድ 2447 ሴት 2980 ድምር 5428 ተይዞ ወንድ 1818 ሴት 1673 ድምር 3491 በመመዝገብ የእቅዱን 64.3% መፈጸም ተችሏል፡፡

 ይህም ከባለፈዉ ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 13% በመቀነስ ያሳያል፡፡ ስለሆነም የ7 አመት ህጻናት 36% በላይ ያልገቡ መሆኑን ያሳያል፡፡ ከሁለተኛ  ደረጃ ትምህርት አኳያ ወንድ 2955 ሴት 3215 ድምር 6170 ለመመዝገብ ታቅዶ ወንድ 2320 ሴት 2577 ድምር 4797 በመመዝገብ 77.4% ማከናወን ተችሏል፡፡

በትምህርት ዘመኑ ከትምህርት ገበታቸዉ በመቅረት ወይም በማቋረጥ የተማሪዎች መቀነስ አፈፃፀም ከኛ-6ኛ ክፍል ወንድ 186 ሴት 131 ድምር 317 ከ7ኛ-8ኛ ክፍል ወንድ 75 ሴት 73 ድምር 148 እንዲሁም በሁለተኛ ደረጃ ወንድ 181 ሴት 103 ድምር 284 ትምህርታቸዉን አቋርጠዋል፡፡

የትምህርትን ጥራት እና ተደራሽነት ለማሳደግ ከ1-6ኛ ወደ 1-8ኛ ክፍል ደረጃቸዉን ያሳደጉ ት/ቤቶች ዕቅድ 1 ክንዉን 1 ነዉ፡፡የሳተላይት ት/ቤቶች ዕቅድ 0 ሲሆን ክንዉን 0 ማድረግ ተችሏል፡፡ በአጠቃላይ የሙሉ ሳይክል ት/ቤቶች ያገኙ ቀበሌዎች ዕቅድ 26 ሲሆን ክንዉን 26 ማድረስ ተችሏል፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች አዲስ ግንባታ ፤ደረጃ ማሳደግ ፤ማስፋፋት ፤ጥገና ፤መልሶ መተካት በተመለከተ የነባር ት/ቤቶችን ደረጃ ለማሳደግ የተገነቡ ተጨማሪ ክፍሎች ዕቅድ 1 ክንዉን 1፤መጨናነቅ በመፈጠሩ በተጨማሪ የተገነቡ ክፍሎች ዕቅድ 0 ክንዉን 0 አፈፃፀሙ 0% ማድረስ ተችሏል፡፡በመልሶ መተካት የተገነቡ የመማሪያ ክፍሎች ዕቅድ 0 ክንዉን 0 አፈፃፀም 0% መፈፀም ተችሏል፡፡

 ከዚህ ባሻገር የአዲስ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የድጋፍ ሰጪ አገልግሎት ክፍሎች ግንባታዎች አፈፃፀም በተመለከተ አዲስ የተገነቡ የመፀዳጃ ቤት ግንባታ ዕቅድ 6 ክንዉን 20፤ አዲስ የተገነቡ አስተዳደር ክፍሎች ዕቀድ 5 ክንዉን 8፤አዲስ የተገነቡ ቤተ መፃህፍት ዕቅድ 4 ክዉን 1፤አዲስ የተገነቡ ቤተ ሙካ ዕቅድ 3 ክዉን 1፤አዲስ የተገነቡ የመምህራን መጠለያ ክፍል ዕቅድ 8 ክንዉን 35፤አዲስ አጥር ያጠሩ ት/ቤቶች ዕቅድ 10 ክንዉን 14 ማድረስ ተችሏል፡፡ከዚህ ባሻገር የተጠገኑ የመማሪያ ክፍሎች ዕቅድ 32 ክንዉን 40፤የተጠገኑ የመጸዳጃ እቅድ 1፤  የተጠገኑ የመምህራን መጠለያ ክፍል ዕቅድ 28 ክንዉን 38 እና የአጥር ጥገና ያደረጉ ት/ቤቶች ዕቅድ 12 ክንዉን 12 መሆኑን ያሳያል፡፡

የ1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የቁሳቁስ አቅርቦት በተመለከተ 15 አዲስ የቀረበ የጥቁር ሰሌዳ፣40 የተጠገነ ጥቁር ሰሌዳ፤ 50 አዲስ ኮምባይንድ ዴስክ ማቅረብና ፣ 145 የተጠገኑ ኮሞባይንድ ዴስክ ፣15 አዲስ የተገዙ ሬዲዩኖች፣550 አዲስ የተገዙ ማጣቀሻ መፃኅፍት፤አዲስ የተገዙ ሳይንስኪት ብዛት 25 ለተማሪዎች ጠቀሜታ ማዋል ተችሏል፡፡

በተመሳሳይ ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች 0 አዲስ የቀረበ ጥቁር ሰሌዳ፣1 የተጠገኑ ጥቁር ሰሌዳ፣0 ኮምባይንድ ዴስክ ፣640 አዲስ የተገዙ የማጠቀሻ መጽሃፍ ፣0 የተጠገኑ ኮምባይንድ ዴስክ ፣4 ት/ቤቶች ኬሚካል ማቅረብ ተችሏል፡፡

 የመጀመሪያ ደረጃ 1-6 ት/ቤቶች የተማሪዉ መፃህፍት አቅርበትን በተመለከተ አማርኛ  መጽሃፍት 23856 ሲሆን የተማሪዉ ቁጥር ደግሞ 20930 ይህም የዕቅዱን >100% ይሸፍናል፡፡እንግሊዝኛ መጽሃፍ 25188 የተማሪዉ ቁጥር 20930 />100%/ ተማሪ ይሽፍናል፡፡ሂሳብ መጽሃፍት 20731 ሲሆን የተማሪዉ ቁጥር ደግሞ 20930 ይህም የዕቅዱን >100% ይሸፍናል፡፡አካባቢ ሳይንስ መጽሃፍት 13329 ሲሆን የተማሪዉ ቁጥር ደግሞ 17043 ይህም የዕቅዱን 78.2% ይሸፍናል፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ 7-8 ት/ቤቶች የተማሪዉ መፃህፍት አቅርበትን በተመለከተ አማርኛ  መጽሃፍት 4755 ሲሆን የተማሪዉ ቁጥር ደግሞ 4758 ይህም የዕቅዱን 100%  ይሸፍናል፡፡እንግሊዝኛ መጽሃፍ 5442 የተማሪዉ ቁጥር 4758 />100%/ ይሽፍናል፡፡

ሂሳብ መጽሃፍት 5012 ሲሆን የተማሪዉ ቁጥር ደግሞ 4758 ይህም የዕቅዱን 94.9%  ይሸፍናል፡፡ ሰማጎ መጽሃፍት 3112 ሲሆን የተማሪዉ ቁጥር ደግሞ 20930 ይህም የዕቅዱን 14.86% ማድረስ ይሸፍናል፡፡ሳይንስ መጽሃፍት 4628 ሲሆን የተማሪዉ ቁጥር ደግሞ 6366 ይህም የዕቅዱን 72.7%ማድረስ ይሸፍናል፡፡

የመጀመሪየ ደረጃ (ከ1-6) ፤የመምህራን ብዛት 576 ፤የመካከለኛ ደረጃ 7-8 486 ማድረስ ተችሏል፡፡የመጀመሪያ ደረጃ 1-8 ኛ መምህራን 1062 ማሟላት ተችሏል፡፡የአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ መምህራን  298 ማሟላት ተችሏል፡፡

የትምህርት ጥራት ለማምጣት የ1ኛ ደረጃ የሴክሽን ተማሪ ጥምርታ 1ለ45፤የተማሪ መምህር ጥምርታ 1ለ38 በማድረስ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት የሴክሽን ተማሪ ጥምርታ 1ለ50 እና የተማሪ ሴክሽን ጥምርታ 1ለ50 በማድረስ እንዲሁም በሁሉም የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ትምህርቱን ተጨባጭ ለማድረግ በቤተሙከራ የታገዘ ትምህርት እየተሰጠ ይገኛል፡፡በዚህም መሰረት በሶስቱም የሳይንስ ትምህርቶች የተሟላ ቤተሙከራ ኖሯቸዉ ትምህርቱን በተግባር ለማስተማር የሞከሩ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብዛት 4 ናቸዉ፡፡

 

  1. ሲቪል ሰርቪስ የሰዉ ሀይል አንፃር

    የተገልጋዩች እርካታ ማሳደግ አንጻር ከተሰሩ ስራዎች በተለያዩ ጊዜ በተሰጡ አገልግሎቶች በተሰሩ ስራዎች የቀረቡ ቅሬታዎችን እና የተፈቱበት አግባብ ዉስጥ የቀረቡ ቅሬታዎች ብዛት ወንድ 4 ሴት 1 ድምር 5 ከዚህም ዉስጥ በዉሳኔ የተፈቱ ወንድ 4 ሴት 1 ድምር 5 ፣ለአስተዳደር ፍ/ቤት ይግባኝ የጠየቁ ወንድ 2 ሴት 1 በድምር 3 ይግባኝ ተጠይቋል በአስተ/ፍ/ቤት የጸና ወንድ 2 ሴት 1 ድምር 2 ፡፡                                  የስራ አፈጻጸም ምዘና ስርዓት ፡- በወረዳችን  ከ1/05/2013 እስከ 30/04/2014 ዓ.ም ዉጤት ሊሞላላቸዉ የሚገቡ ሰራተኞች ወንድ 347 ሴት 335 ድምር 682 ከዚህም ዉስጥ ዉጤት የተሞላላቸዉ ወንድ 321 ሴት 316 ድምር 637 ፣ያልተሞላላቸዉ ወንድ 26 ሴት 19 ድምር 45 ያልተሞላላቸዉ ሰራተኞች ምክንያት  ወደ መከላከያ የሄደ፣በእስር ላይ፣ከሌላ ወረዳ የመጡ፣በወሊድ ፣በአመራር ቸልተኝነት ፣ትምህርት ላይ ያሉና የለቀቁ ናቸዉ፡፡

በወረዳችን   ከ1/5/2014 እስከ 30/10/2014 ዓ.ም እቅድ ሊያዝላቸዉ የሚገቡ ሰራተኞች ወንድ 513 ሴት 490 ድምር 1003 ከዚህም ዉስጥ እቅድ የተያዘላቸዉ ወንድ 504 ሴት 483 ድምር 987 ፣ያልተያዘላቸዉ ወንድ 9 ሴት 7 ድምር 16 ያልተያዘላቸዉ ሰራተኞች ምክንያት በወሊድ ፣በአመራር ቸልተኝነት ፣ትምህርት ላይ ያሉና የለቀቁ ናቸዉ፡፡

  መረጃ አያያዝ  በተመለከተ፡- የሰው ሃይል መረጃዎችን በፕሮፋይል ፣በቋሚ መዝገብ ፣በሶፍት ኮፒ በአግባቡ ተደራጅተው ተይዘዋል፡፡ በትምህርት ደረጃ  ሲገልፅ ሁለተኛ ድግሪ ወንድ 28 ሴት 5 ድምር 33፣ የመጀመሪያ ድግሪ ወንድ 562 ሴት 285 ድምር 847፣ ከፍተኛ ድፕሎማ  ወንድ 179 ሴት 240 ድምር 419 ፣ድፕሎማና አቻ ወንድ 685 ሴት 596 ድምር 1281 ፣ ሰርተፍኬት ወንድ 20 ሴት 66 ድምር 86 ፤12ኛ ክፍልና አቻ የት/ዝግጅት ያላቸው ወንድ 41 ሴት 27 ድምር 68፤ ከ12ኛ ክፍል በታች ወንድ 33 ሴት 29 ድምር 62  ዲቪኤም ወንድ 7 ሴት 3 ድምር 10 ፤በአጠቃላይ ወንድ 1555 ሴት 1251 ድምር 2806 ሰራተኞችን መረጃ አደራጅቶ መያዝ ተችሏል፡፡

 በበጀት አመቱ በተቋሙ በመደበኛ ተግባራት ከተከናወኑ ተግባራ የተፈጸሙ ስምሪቶች ቅጥር ወንድ 3 ሴት 7 ድምር 10፣ደረጃ እድገት/ኬርየር/ ወንድ 57 ሴት 82 ድምር 139፣ምደባ ወንድ 6 ሴት 3 ድምር 9፣ዝዉዉር(የዉስጥ ሴት 1 ድምር 1፣የዉጭ ወንድ 1 ሴት 2 ድምር 3፣የእርስ በርስ ወንድ 1 ሴት 3 ድምር 4) ድምር ወንድ 2 ሴት 6 ድምር 8  ፣የአጭር ጊዜ ስልጠና  ለ..ወጣት፣ለረጅም ጊዜ ስልጠና ለ 3 ወንድ ለ4 ሴት በድምሩ ለ7 ወጣቶች ፣ቋሚ ቅጥር ለ4 ወንድ ለ12 ሴት በድምሩ 16 ወጣቶች ከዚህም ዉስጥ 0 አካል ጉዳተኛ ፣ደረጃ እድገት በኬርየር 139፣ስንብት በፍላጎት 25፣ስንብት በዲሲፒሊን 1፣ምደባ በመደበኛ 9 በጠቅላላ 92 ወንድ 113 ሴት በድምሩ 205 መከናወን ተችሏል፡፡

3.ጤና ጥበቃ

    መከላከልን መሰረት ያደረገ የጤና ፖሊሲ ተቀርጾ ሁሉም እርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡ከጤና አኳያ በወረዳው ውስጥ በወረዳ ባሉ ጤና ጣቢያዎችና ጤና ኬላዎች ያሉ የተለያየ ባለሙያዎች 159 ፣53 የገጠር ጤና ኤክስቴንሽን፤9 የከተማ ጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኛ ፤104 አስተዳደር ሰራተኛ በድምሩ 320 ባለሙያዎች ይገኛሉ፡፡

 ከእናቶችና ወጣቶች ጤና አገልግሎት፡-የቤተሰብ እቅድ አጠቃቀም በበጀት አመቱ ለ35176 ሴቶች ዉስጥ 35176 እናቶች እስከዚህ ወር የቤተሰብ እቅድ ተጠቃሚ ለመስጠት በእቅድ ተይዞ ለ19338 የተሰጠ ሲሆን አፈጻጸም 54.9% መሆኑን ያሰያል፡፡ለ5860 እናቶችን በጤና ተቋም የቅድመ ወሊድ፤የወሊድና የድህረ ወሊድ ክትትል እንዲያደርጉ  ዕቅድ ተይዞ በክንዉን 5250 አፈፃፀም 89.5%፤2332 አፈፃፀም 39.79%፤እና 2931 አፈፃፀም 50% በቅደም ተከተል መሆኑን ያሳያል፡፡1717 ኤች፤አይ፤ቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ  ምርመራ ለማድረግ ታቀዶ ለ159 አገልግሎት በመስጠት የዕቅዱን 9.3% አገልግሎት መስጠት የተቻለ ሲሆን ከተመረመሩት ዉስጥ 3 እናት ቫይረሱ በደሟ የተገኘ ሲሆን ተገቢዉን ክትትል እየተደረገላቸዉ ይገኛል፡፡

 ህጻናት ጤና አገልግሎት፡-በወረዳ ዉስጥ የቲቢ መከላከያ ክትባት ማግኘት ያለባቸዉ 5860 ህጻናት ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ 3523(60.1%) ህጻናት እስከዚህ ወር ተጠቃሚ ማድራግ ተችሏል፡፡ለ4056 ህጻናት የጸረ-8 ክትባት ለመጀመሪያ ለ3ተኛ ጊዜ፣የኩፍኝ ክትባትና ሁሉም አይነት ክትባት እንዲይገኙ ታቅዶ 3848(98%)ለመጀመሪያ ጊዜ፣3586(87%) ለ3ተኛ ጊዜ፣3435(472%)ኩፍኝ ክትባትና 3331(72%) ሁሉም አይነት ክትባት ህጻናትን እንደቅደም ተከተላቸዉ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ለ373 ህጻናት የከፋ ምግብ እጥረት ህክምና ለመስጠት ታቅዶ 218 ህጻናት 110.5% ብቻ ተጠቃሚ ሆነዋል

 

 በመኖሪያ ቤት ደረጃ የሃይጅን ፖኬጅ አፈጻጸም፡-የተሸሻሻለ መጸዳጃ ቤት የአዲስ የመጸዳጃ ቤት ግንባታ እቅድ በወረዳ ደረጃ  23763 እስከዚህ ሩብ አመት አዲስ ክንዉን 6400 አፈጻጸም 26.9%፣ጠቅላላ መጸዳጃ ቤት ድምር የተለሞዶና የተሻሻለ ጥቅል እቅድ 26682 ክንዉን 21392 አፈጻጸም 80.2% ማድረስ ተችሏል፡፡

በተቋም ደረጃ ደረጃ የፋሲሊቲ ግንባታ፡-በጤና ጣቢያ ደረጃ የመጸዳጃ ቤት ግንባታ 5 በጤና ጣቢያ በእቅድ ተይዞ ክንዉን 5 አፈጻጸም 100%፣በመጸዳጃ ቤት ግንባታ በጤና ኬላ  በዕቅድ 20 ተይዞ ክንዉን 20 አፈጻጸም 100% ማድረስ ተችሏል፡፡

ከአይነ ምድር የጸዳ ቀበሌ፡-በአንደኛ ደረጃ ከአይነምድር የጸዳ ቀበሌ በአመቱ ዕቅድ 26 ክንዉን 0 አፈጻጸም 0፤

ጤና መድን፡-ከሚጠበቁት 41246 አባወራዎች ዉስጥ 17217/42%/ አባል ሆነዉ ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡5665 አዲስ የጤና መድን አባላት ለማፍራት ታቅዶ ክንዉን 151 አባላት ማፍራት ችለናል፡፡ በጤና መድን 47417 ከፋይ አባላትና 2842 የድሃ ድሃ አባላት የህክምና አገልግሎት አግኝተዋል፡፡ ለዚህም አገልግሎት 2287075 ብር ለደንበኞች አገልግሎት ክፍያ ዉሏል፡፡

   ኤች አይቪ ኤዲስና ተላላፊ በሽታዎች፡-በፈቃደኝነትላይ የተመሰረተ የኤች አይ ቪ ምርመራ ለ2926 በፍቃደኝነት ራሳቸዉን ለማወቅ ለፈለጉ እና እንዲሁም በባለሙያ ምክር አነሳሽነት ለ9977 ሰዎች ለመስጠት ታቅዶ ለ883 (88%) በፈቃደኝነት ራሳቸዉን ለማወቅ ለፈለጉ እና ለ4148 (42%) በባለሙያ ምክር አነሳሽነት ስዎችን መስጠት ችለናል፡፡

  በበጀት አመቱ በወረዳዉ ባሉ 5 ጤና ጣቢያ በቲቢና በስጋ ደዌ ከ173882 ህብረተሰብ 243 ሊገኝ ይችላል ተብሎ ተይዞ 23 በበሽታ ተጠቂ የሆኑ ተገኝተዋል፡፡የወባ በሽታና የህብረተሰብ ጤና አዳጋዎች መከላከልና መቆጣጠር፡-በወረዳ ደረጃ ጠቅላላ ተመላላሽ ታካሚዎች 347764 ሲሆኑ ለ104329 የወባ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍል፤ለ7929 የወባ ላቦራቶሪ ምርመራ እንዲያደርጉ እቅድ ተይዞ ለ19366 መርመራ መደረግ ተችሏል፡፡

4.4.መልካም አስተዳደር

  1. ወረዳ ምክርት ቤት

በወረዳ ደረጃ ጉባኤ በማካሄድ የእቅድ ኦረንቴሽን ለመሥጠት ለ42 ወንድ ፤ለ42 ሴት በድምሩ ለ84 የም/ቤት አባላት ፤ለ47 ወንድ ለ1 ሴት በድምሩ ለ48 የቀበሌ አፈጉባኤዎች፣ ለ6 ወንድ ለ9 ሴት በድም ለ15 የወረዳ ቋሚ ኮሚቴዎች፤ለ144 ወንድ ለ72 ሴት በድምሩ ለ216 የቀበሌ ቋሚ ኮሚቴዎች  እና ለ3 ወንድ ለ3 ሴት በድምሩ 6 ባለሙያዎች ኦረቴሽን ለመስጠት እቅድ ተይዞ ለ… ወንድ ፤ለ…. ሴት በድምሩ ለ…/..%/ የወረዳ ም/ቤት አባላት ፤ለ36 ወንድ ለ1 ሴት በድምሩ ለ37/77%/ የቀበሌ አፈጉባኤዎች ፣ለ6 ወንድ ለ9 ሴት በድምሩ ለ15/100%/ የወረዳ ቋሚ ኮሚቴዎች፤ለ48 ወንድ ለ24 ሴት በድምሩ ለ72/100%/ የቀበሌ ቋሚ ኮሚቴዎች ሰብሳቢዎች እና ለ3 ወንድ ለ3 ሴት በድምሩ 6 ባለሙያዎች የእቅድ ኦረንቴሸን ተሰጥቷል፡፡

 ለ1 ጊዜ አስቸኳይ ጉባኤ ያካሄደ የወረዳ ም/ቤቶች በጉባኤ መገኘት  ያለባቸዉ ወንድ 50 ሴት 50 ድምር 100 የተገኘ ወንድ 30 ሴት 35 ድምር 65፣ሀገር የለቀቁ ወንድ 13 ሴት 13 ድምር 26 ፤መሞት የተለዩ ወንድ 6 ሴት 2 በድምሩ 8፤በራሳቸዉ ፈቃድ የለቀቁ ወንድ 1 ሴት 2 በድምሩ 3 በጠቅላላ ወደ ጉባኤ መምጣት የማይችሉ ወንድ 20 ሴት 15 ድምር 35 መሆናቸዉ ተረጋግጧል፡፡

ሲቪክ ማህበራት ለ4 ወንድ ለ1 ሴት በድምሩ 5 እቅድ ተይዞ ወንድ 4 ሴት 1 ድምር 5/100%/ ሲሆን ም/ቤቱ የተወያየባቸዉ አጀንዳዎች የተመረጡ ሴ/ር ሪፖርቶችን ማዳመጥ፣የኦዲት ሪፖርት ማዳመጥ የሚሉት ናቸዉ፡፡

 የቀበሌ ምክር ቤት ዝርዝር አፈጻጸም፡-የቀበሌ ም/ቤት የሚያካሂዱ  24 ቀበሌዎች  እስከዚህ ሩብ አመት 8 ጊዜ ያካሄዱ 6 ቀበሌዎች ፣7 ጊዜ ያካሄዱ 7 ቀበሌዎች፣ 6 ጊዜ ያካሄዱ 5 ቀበሌዎች፣5 ጊዜ ያካሄዱ 4 ቀበሌዎች  ሲሆን በጉባኤዉ መገኘት የነበረበት ወንድ 3529 ሴት 3471 ድምር 7000 ሲሆን በጉባኤዉ የተገኙ ወንድ 2452 ሴት 1745 ድምር 4197 አገር የለቀቀ ወንድ 235 ሴት 17 ድምር 252 በሞት የተለዩ ወንድ 220 ሴት 53 ድምር 273 ናቸዉ፡፡

  1. አስተዳደር ዘርፍ አንፃር

   ከአይሲቲ የስራ ሂደት ፡-በአይሲቲ ዘርፍ በተለያዩ ስልጠና የተሰጠ ቅድመ ስራ ላይ ስልጠና ወ 0 ሴ በድምሩ ፣አድቫንስ ስልጠና ወ.. ሴ.. በድምሩ …፣ ወ 0 ሴ 0 በድምሩ 0 ኢንተርፕርናር ወ 0 ሴ  0 ድምር 0 ግንዛቤ ማስጨበጫ በድምሩ  ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ለ ወንድ ለ ሴት በድምሩ የመ/ሰራተኛ፣ለ.. አርሶ አደርና ለ.. መምህር መሰረታዊ በድምሩ 0 የኮምፒውተር ስልጠና መስጠት፣ ተችሏል፡፡

የኢንተርኔት ተጠቃሚ የሆኑ ሴክተሮች 19 ሲሆኑ 1 በወረዳ ኔት 18 በፐብሊክ መስመር ኢንተርኔት ተጠቃሚ ናቸዉ፡፡

ብሮድ ባንድ ኢንተርኔት ለሚጠቀሙ ሴክተሮች የዝርጋታ ድጋፍ ማድረግ በዕቅድ 12 ተይዞ በክዉን 10 መፈፀም ተችሏል፡፡

በሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚገኙ የእይሲቲ መሳሪያዎች ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤ብልሽት ሲያጋጥም ጥገና ማድረግ ዕቅድ 360 ክንዉን 294 አፈፃፀም 98% ማድረግ፡፡በተፈቀዱ የአይሲቲ ዘርፎች የብቃት ማረጋገጫ ፤ፈቃድ፤ ዕድሳት መስጠት ዕቅድ 14 ክንዉን 8 አፈፃፀም 57% መፈፀም ተችሏል፡፡

በፕላዝማ መጠቀም የነበረባቸዉ ት/ቤቶች ብዛት 4 ሲሆን 2 እየተጠቀሙ ይገኛል፡፡በገጠር ሁለገብ የመረጃ ማዕከላት አጠቃላይ መረጃ ለመስራት የተደራጁ ማዕከላ ብዛ 1 በቀበሌ ደረጃ የአባላት ብዛት ወ 10 ሴ 2 ድ 12 ያከናወኑት ተግባር 2 ቀበሌ የደም ናሙና ሰርተዋል፡፡

   ከአገልግሎት አሰጣጥ አኳያ፡-የአገልግሎትአሰጣጥ ስታንድርድ 36 የፑል ጽ/ቤቶች ተግባራዊ እንዲያደርጉ እቅድ ተይዞ 0/0%/ ለመፈጸም ተችሏል፡፡ድጋፍና ክትትል የሚደረግላቸዉ የወረዳ አስተዳደር ፑል ጽ/ቤቶች 9 ዕቅድ ተይዞ 0/0%/ ክትትልና ድጋፍ
9፡፡ከሰራተኞችና ከደንበኞች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ተቀብሎ በመርመር ፍትሃዊ ዉሳኔ ለመስጠት 10 ዕቅድ ተይዞ በሩብ አመቱ 8 ,የአወንታዉና አሉታዊ አስተያየቶች በመመዝገብና በማሰባሰብ ለሚመለከተዉ አካላት ማሳወቅ በአዉንታ 12 በአሉታ 12 በድምሩ 24 በእቅድ ተይዞ 10 በአወንታ 6 በአሉታ በድምሩ 16 ቅሬታዎችን መመዝገብ ተችሏል፡፡

በወሳኝ ኩነት ምዝገባ በኩል መረጃ መመዝገብ ፡-   5769 ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ ለመፍጠር እቅድ ተይዞ 5769 ግንዛቤ መስጠት ተችሏል፡፡በተያያዘ የልደት መረጃ ለመመዝገብ ዕቅድ 4269 ክንውን 4269/100%/፤የተመዘገበ ሞት ዕቅድ 932 ክንዉን 932/100%/፤የተመዘገበ ጋብቻ ዕቅድ 676 ክንዉን 676/99%/፤ ፍች በዕቅድ 74 ክንዉን 19/25%/፤በድምሩ 5951 ወሳኝ ኩነቶችን ለመመዝገብ ታቅዶ 5896 በመመዝገብ 99% ማከከናወን ተችሏል፡፡

የጋብቻ የምስክር ወረቀት ለመስጠት  ዕቅድ 29 ክንውን 0 /የልደት የምስክር ወረቀት መስጠት ዕቅድ 764 ክንውን 0፣ የተሰጠ የሞት የምስክር ወረቀት ዕቅድ 168 ክንውን 0  የምስክር ወረቀት መስጠት ተችሏል፡፡

3 .ከጸጥታ ዘርፍ አንጻር

የማስፈጸም አቅምን ለማሳደግ ግጭትና የግጭት መንስኤ የሆኑ ጉዳዩች አስቀድሞ መከላከል፣የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራ ማጠናከር የህብረተሰቡ ሰላምና ደህንነት መጠበቅ አቅጣጫ በተያዘዉ መሰረት፡-በበጀት አመቱ እስከዚህ ሩብ አመት በፀጥታ ማስከበር ላይ የተሰማራውን አባልና አመራር የመፈፀም አቅም ለማጎልበት አዲስ የፖሊስ አባላት ምልመላና ስልጠና የአዲስ የሚኒሻ አባላት ምልመላ እቅድ 300 ክንዉን 202 መመልመል እንዲሁም ወንድ 1642 ሴት 12 ድምር 1654 የነባር ሚኒሻና የብሄራዊ ተጠባባቂ ሀይል ማጠናከሪያ ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ ወንድ 1213 ሴት 5 ድምር 1218 ማጠናከሪያ ስልጠና በመስጠት ማብቃት ተችሏል፡፡

ከግጭት መከላከል አፈታት ተግባራት በተመለከተ ፡-ወር በገባ በ19 ወረዳችን ከሚያዋስኑ ወረዳዎች ማለትም አነደድ፣ ደ/ማ ከተማ ወረዳ፣ጎዛምን ወረዳ ጋር በተለይ ከአነደድ ወረዳ ግጭቶችን ለመፍታትና ለመከላከልና ለመፍታት እንዲሁም ተዘዋዋሪ ወንጀሎችን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል የጋራ አቅድ በማዉጣት ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

በዚህ ሩብ አመት በወረዳ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች የተደቀነብን የህልዉና አደጋ አደጋ ለመመከት ከመንግስት ሰራተኛዉ፤ከወጣቱና ከማህበረሰቡ ምን ይጠበቃል በሚል ርዕስ  በ ኮንፈረንስ ተካሂዷል የተሳታፊ ብዛት ወንድ 76000 ሴት 22000 ድምር 78200 ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡የሀይማኖቶች ፎረም እቅድ 0 ክንውን 0 የተቋቋመ ሲሆን በቅድመ ማስጠንቀቂያ የተከሰቱ ግጭቶች በእምነት 9፤ በተፈጥሮ ሃብት 0፤መልካም አስተዳድር 0 በድምሩ 9 ናቸዉ፡፡ የተከሰተና የተፈቱ ግጭቶች በተመለከተ 9 በእምነት፣0 በተፈጥሮ ሀብት በድምሩ 9 ግጭቶች የተከሰቱ ተፈተዋል፡፡

የሰላም ክበባት ማጠናከር በተመለከተ በየት/ቤቶች የሰላም ክበባት ለ56  ክበባት ለማቋቋም እቅድ ተይዞ እስከ አሁን ድረስ 28 ክበባት ተቋቁመዋል፡፡ በወረዳ ደረጃ የሰላም ም/ቤት ለማጠናከር 1 ዕቅድ ተይዞ 1 በቀበሌ ደረጃ 26 እቅድ ተይዞ 0 ማጠነከር ተችሏል፡፡

 በቀበሌዎች በሰላም ኮሚቴ የታቀፉ የአመራር አባላት ብዛት በዕቅድ ደረጃ ወንድ 276 ሴት 46 ድምር 364 ተይዞ እሰከዚህ ሩብ ዓመት ወንድ 132 ሴት 22 ድምር 190 በመፈፀም 70% ማከናወን ተችሏል፡፡

በኮሚኒቲፖሊስንግ ወ 36652 ሴ 26470 ድ 63122 ለሚሆኑ ህዝብ የት/ት ማስጨበጫ ግንዛቤ ተሰጥቷል፡፡በኮሚኒቲፖሊስግ ቀበሌዎችን ለማቀፍ ለ26 እቅድ ተይዞ ለ17 ማዕቀፍ የተቻለ ሲሆን አፈፃፀም 65.38% የተከናወነ ሲሆን በዚህ ሩብ አመት በኮሚኒቲ ፖሊሲንግ ቀበሌዎች አፈፃፀም ደረጃ ከፍተኛ 0 ፣ መካከለኛ 17፤ዝቅተኛ 0 ቀበሌዎች ተገኝቷል፡፡

  በአስተዳድር እርከኑ የተቋቋሙ ኮሚኒቲ ፖሊሲግ አማካሪ ም/ቤቶች የግጭት አስወጋጅ ኮሚቴ ወደ ስራ እንዲገቡ አድርጓል፣ በስነ ምግባር ችግር ያለባቸው ግለሰቦች የምክር አገልግሎት ተሰጥዋል፡፡የፀጥተውን ሁኔታ በመገምገም የመፍትሄ አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል፡፡ ኮሚኒቲፖሊስግ 22 ቀበሌዎች መኖሪያ ቤት ተሟልቶላቸዋል 4 ቀበሌዎች በክራይ እየተገለገሉ ይገኛሉ፡፡ በየጎጡ ግጭት መፍቻ ማዕከል ስገነባሉ፤በቀበሌአቸዉ ያለዉን ጥበቃ በየጊዜዉ ይፈትሻሉ፤ጎጦችን ተከፋፍሎ በመያዝ ግንዛቤ ይፈጥራሉ፤በአጠቃላይ የፀጥታዉን ሁኔታ በመገምገም የመፍትሄ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

   የተፈፀመ አጠቃላይ ወንጀል በገጠር 85 በከተማ 47 በድምሩ 132 ሲሆን ከዚህ ውስጥ የተፈጸመ ዋና ዋና ወንጀሎች በገጠር 63 በከተማ 19 ድምር 82 ናቸው፡፡ የወንጀል  የህዝብ ጥምርታ ከ1000 ስዎች ውስጥ ከአጠቃላይ ወንጀል በገጠር 0.53፣በከተማ 3.15 ፣በድምሩ 3.68 ወንጀል ተፈፅሟል፡፡ በአጠቃላይ ወንጀል ውስጥ በዋና ዋና ወንጀል በገጠር 0.39 በከተማ 1.27 ድምር 1.66 ወንጀል ተፈፅሟል፡፡በዋናነት ሰዉ መግደል 39፤የሴቶችን በማስገደድ የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ 4፤የሀሰት ብር ዝዉዉር 2፤ ለመግደል ሙከራ 13 እና ድብደባና አካል ማጉደል 13 የተፈፀሙ ሲሆን በአጠቃላይ 62 በገጠር 19 በከተማ  በድምሩ 81 ወንጀሎች ተፈጽመዋል፡፡

  አጠቃላይ በመሰረተ ልማት ተቋማት ላይ ህብረተሰቡ የራሱ አድርጎ እንዲጠብቃቸው ክትትል እንዲያደርግባቸው የግንዘቤ ት/ት ተሰጥቷል፡፡ የወንጀል ምርመራ አቅምና ጥራት የቀረበ ክስ 150 ሲሆን ተጣርቶ የተላከ 150 የምርመራ አቅም በእቅድ 96% ክንውን 100% የምርመራጥራት ዕቅድ 98% ክንዉን 100%ነዉ፡፡የግል አቤቱታ የማጣራት አቅምና ጥራት 0 የቀረበ ክስ ከዚህ ውስጥ 0 ተጣርቶ የተላከ የምርመራ አቅም እቅድ በ0%  ክንውን 0% መከናወን ተችሏል፡፡እንዲሁም የመንግስት ክስ የማጣራት አቅምና ጥራት 150 የቀረበ ክስ ከዚህ ውስጥ 150 ተጣርቶ የተላከ  ሲሆን የምርመራ አቅም በእቅድ 98% ክንውን 100% ተከናውኗል፡፡የተከሳሽ ምስክር አቀራርብ በተመለከተ የተከሳሽ እቅድ 315 ክንውን 300 አፈፃፀም 98% እንዲሁም ምስክር እቅድ 380 ክንውን 300 አፈፃፀም 94% ተከናውኗል፡፡

የመንገድ ትራፊክ ድህነት ት/ት ለ11004 ወንድ  ለ76714 ሴት በድምሩ ለ87718 የህብረተሰብ ክፍል የግንዘቤ ማስጨበጫ ት/ት ለመስጠት ታቅዶ እስከዚህ ሩብ አመት ለ14400 ወንድ  ለ31138 ሴት በድምሩ ለ45538 ለህብረተሰብ ክፍል በድግግሞሽ ግንዛቤ ለመስጠት ተችሏል፡፡የተሰጡ የት/ት ርዕሶች እዲሁም ያመጠው ለውጥ ስንመለከት ለውጥ የግራ መስመር አጠቃቅም በገጠርና በከተማ ያለበት ደረጃ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ እርምጃዎች ስለትራፊክ ትርጉም፣የትራፊክ አዳጋ አስከፊነት፣የተሳፋሪ መብቶችና ግድታዎች ፣ የአሽከርካሪ መብትና ግዴታ ፣ የእግረኛ  ግራ መስመር አጠቃቅም በሚሉ ርእሶች ላይ  ት/ት ተሰጧል፡፡የትራፊክ ደንብ መተላለፍ በተመለከተ እስከዚህ ሩብ አመት 1531 ተሸከርካሪዎች ደንብ የተላለፉ ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ 1531 ላይ እርምጃ ተወስዶ ይኸውም ብር 418180 እንዲከፍሉ ተደርጓል፡፡

  በ2014 የበጀት ዓመት የሚሊሻና ብ/ተ/ሀ/ አባላት አደረጃጀት በአዲስ የተደራጀ ሲሆን 4 ሻለቃ፣14 ሻንበል፣60 የመቶ ፣188 ጓድ አደረጃጀት ያለ ሲሆን የግልና መንግስት ታጣቂዎች አደረጃጀት ሻለቃ 2፣ሻንበል 13፣መቶ 27፣ጓድ 109 በማድረግ የተደራጀ ሲሆን ወደስራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡በአዲስ የተደራጀ የጥበቃ ቡድን 3450 ሲሆን 15700 በማደራጀት ወደ ስራ በማስገባት  የአካባቢዉና ኬላዎችን ማስጠበቅ ተችሏል፡፡

 በግድያ ወንጀል ከተጠረጠሩ 42 ተጠርጣሪዎች ዉስጥ 37 ተጠርጣሪዎችን ለህግ ማቅረብ ተችሏል በተጨማሪም በበጀት አመቱ 74 የተለያዩ የቤት እንስሳት 3 መሳሪያ፣13 ሽጉጥ፣0 ቦንብ፣1984 ጥይት፤4000 ብር የሀሰተኛ ብር፤ በመያዝ ተችሏል፡፡

በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ ለህልዉና ዘመቻ ዘምተዉ11 ለተሰዉ ጓዶች ለቤተሰባቸዉ 200ካ.ሜ እና 5000ሺ ብር ለእያንዳንዳቸዉ፤ቆስለዉ ለተመለሱ 40 ጓዶች 5000 ሺ ብር እና የእዉቅና ሰርተፊኬት፤በመስጠት እዉቅና ለመስጠት ተችሏል፡፡

  1. 4. ከፍትህ ዘርፍ አንፃር

   ከባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራና ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠርና የተደራጀ የህዝብ ተሳትፎን በፍትህ ስርዓቱ ዉስጥ በማረጋገጥ በወረዳዉ ዉስጥ ኪራይ ሰብሳቢነትን በጽናት መታገል፣መልካም አስተዳደር በማረጋገጥ ንጹሃንን መጠበቅ በሚል በተያዘዉ መሰረት፡-    በወንጀል ጉዳይ እስከዚህ ሩብ አመት 119 መዝገቦች የቀርቡ ሲሆን 119 መዝገቦች ላይ ዉሳኔ በመሰጠቱ አፈፃፀሙ 100% መሆኑን ያሳያል፡፡ቀዳሚ ምርመራን በተመለከተ በዕቅድ የቀረቡትን 27 መዝገቦች ቀርበዉ ተሰርተዋል፡፡የመዘግብት መንጠባጠብ 4.5% ለመቀነስ ዕቅድ ቢያዝም 14 መዝገብ የተቋረጠ መዝገብ በመኖሩ 18.18% ሆኖ ስለሚታይ በቀጣይ የማቋረጥ ምጣኔ መቀነስ አለበት፡፡

የዋስትና አስተያየት በተመለከተ አጠቃላይ በጽ/ቤቱ የቀረቡ ዋስትናዎች 280 መዛግብት ሲሆኑ ሁሉም ዋስትናወች ዉስጥ 254 የተፈቀደ፤23 በዓቃቢ ህግም በፍ/ቤትም የተከለከሉ ሲሆኑ 03 በኮማንድ ፖስቱ የተከለከሉ ናቸዉ፡፡

የእጅ ከፈንጅ ወንጀልን በተመለከተ 08 መዛግብት ቀርበዉ 03 መዝገቦች ወደ መደበኛ ክስ ተመስርቷል፡፡05 መዝገቦች በፍ/ቤት ክስ ተመስርቶ በእጅ ከፈንጅ ዉሳኔ አግኝተዋል፡፡ሰብዓዊ መብት ማስከበርን በተመለከተ የማረሚያ ቤት ጉብኝት በዕቅድ የተያዘ 264 ጊዜ መጎብኘት ሲሆን 149 ጊዜ ብቻ መጎብኘት ተችሏል፡፡የጣቢያ ጉብኝት 198 ለማድረግ ታቅዶ 116 ጊዜ ማድረግ 59% ማድረግ ተችሏል፡፡

በፍታብሔር ጉዳይ፡-ቅድመ መከላከልን አኳያ፤የህግ ምክር አገልግሎት 05 ለመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ለግለሰቦች የህግ ምክር መስጠት ተችሏል፡፡

45 መዝገቦች  የገንዘብ ምርመራ መጠናቸው 30146345 ብር፣ረቂቅ  ረቂቅ ውል ቀርቦ 40 የገንዘብ ምርመራ መጠናቸው 29478365 ብር ለህግና ለሞራል ተቃራኒ አለመሆናቸዉ ተረጋግጦ ተመርምሯል፡፡ነገር ግን 05 መዝገቦች የገንዘብ መጠናቸዉ 685979.97 ከተመረመሩት ሰነዶች የስራ ሂደት ላይ ሳየፀድቁ የቀሩ ናቸዉ፡፡

 ድህረ መከላከልን በተመለከተ በመንግስት ጉዳይ በዐ/ህግ  የተከናወኑ ከባለፈው የዞረ የለም፤በከሳሽነት አዲስ  የቀረበ 09 መዝገብ የገንዘብ መጠናቸው 190666.5 ብር፣03 መዝገቦች የገ/መጠናቸዉ 42000 ብር የያዙ የማየት ስልጣን ላለዉ አካል ሲላኩ፤03 መዝገብ የገንዘብ መጠኑ 39166.5 ብር የያዘ በፍ/ቤት ክስ ሳይመሰረት በድርድር ተዘግቷል፡፡   በተከሳሽነት አዲስ የቀረበ መዝገብ 11 የያዘው የብር ግምት 376694.46 ብር ቀርበዉ ፤41.0608 መድ መሬት እና 350 ካ/ሜ የከተማ ቦታ የያዙ ቀርበዉ 01 መዝገብ የገንዘብ መጠኑ 62613.8 ብር ክስ አያስመሰርትም ዉሳኔ ሲሰጥበት ቀሪ 10 መዝገብ የገ/መጠኑ 314080.66፤41.0608 ገመድ መሬት እና 350 ካ/ሜ የከተማ ቦታ የያዙ

በፍ/ቤት ክስ ተመስርቷል፡፡ በይግባኝ ባይነት የቀረበ መዝገብ 01 3 ገመድ መሬት የያዘ ቀርቦ የማየት ስልጣን ላለዉ አካል ተላልፏል፡፡ በይግባኝ መልስ ሰጪነት የቀረበ መዝገብ 05 የገንዘብ መጠናቸዉ 149642 ብር እና 16.14 ገመድ መሬት የያዙ ቀርበዉ የማየት ስልጣን ላለዉ አካል ተላልፈዋል፡፡

 በድምሩ 25 መዝገብ 714536 ብር፣60.2032 ገመድ መሬት እና 350 ካ/ሜ የከተማ ቦታ የያዙ ቀርበዉ የዐ/ህግ በመንግስት ጉዳይ የማጥራት ምጣኔ ዕቅድ 100% ነዉ፡፡

    በነፃ የህግ ድጋፍ በዐ/ህግ የተከናወኑ ከባለፈው የዞረ የለም፣አዲስ የቀረቡ በከሳሽነት 48 መዝገብ ግምቱ 1714582.5 ብርና 26.0476 ገመድ መሬት፤ሞግዚት ይሾምልኝና የያዙ ቀርበዉ 02 መዝገብ 01 ገመድ መሬት እና ሀብት ንብረትን የያዘ ክስ አይቀርብም ዉሳኔ ተሰጠ፡፡32 መዝገብ የገ/መጠናቸዉ 240632 ብር እና 1 ገመድ መሬት እና የያዘ የማየት ስልጣን ላለዉ አካል የተላከ ሲሆን ቀሪ 13 መዝገብ የገንዘብ መጠናቸዉ 918950.5 ብር፤24.476 ገመድ መሬት እና ሞግዚት ይሾምና ይዉረድ የያዘ በፍ/ቤት ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

በተከሳሽነት ካለፈዉ የዞረ የለም አዲስ የቀረበ 04 የገንዘብ መጠኑ 600000 መዝገብ 30 ኪ.ሜ የከተማ ቦታ የያዘ በፍ/ቤት ክስ ተመስርቷል፡፡

በይግባኝ ባይነት አዲስ የቀረበ  መዝገብ የለም፡፡በይግባኝ መልስ ሰጭነት አዲስ የቀረበ 01 መዝገብ ፣በአጠቃላይ 02 መዝገብ የገ/መጠናቸዉ 3000 ብር፤1 ገመድ መሬት የከተማ ቦታ የያዙ ቀርበዉ ሁሉም ዉሳኔ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

   በመንግስት ጉዳይ ፍ/ቤት የቀረቡ መዝገቦች ውጤት ሲታይ በከሳሽነት ከባለፈው  አመት የዞረ 05 የገ/መጠን 462058 ብር እና 17.05 ገመድ መሬት ፤አዲስ የቀረበ መዝገብ 01 ፤ መዝገብ የገንዘብ መጠናቸዉ 27500 ብር በድምሩ  06 መዝገቦች የገንዘብ መጠናቸዉ 489558 ብር እና 17.05 ገመድ መሬት የያዙ በአሸናፊነት ሲወሰን፤01 መዝገብ የገንዘብ መጠኑ 270000 ብር እና 1 ገመድ መሬት የያዙ ስልጣን ላለዉ አካል  ሲላኩ ቀሪ 03 መዝገቦች ገ/መጠናቸዉ 224080.66 ብር እና 35.762 ገመድ መሬት በፍ/ቤት ቀጠሮ ላይ ናቸዉ፡፡

በመንግስት ጉዳይ ጥቅል የማሸነፍ ምጣኔ በዕቅድ 87.5% ሲሆን አፈፃፀሙ 68.05% ነዉ፡፡

 በነጻ የህግ ድጋፍፍ/ቤት የቀረቡ መዝገቦች ዉጤት በከሳሽነት ከባለፈው የተላለፈ 02 መዝገብ 183223 ብር እና 3 ገመድ መሬት እንዲሁም በአዲስ የቀረበ 13 መዝገብ  918950.5 ብር ፤27.0476 ገመድ መሬት፤ሞግዚት ይዉረድልኝ ይሾምልኝ እና ልጅ ይመልስልኝ 05 መዝገብ ግምቱ 17812.5 ብር፤11.2408 ገመድ መሬት እንዲሁም እንዲሁም ሞግዚት ይዉረድልኝና ይሾምልኝ የያዙ በአሸናፊነት የተወሰነ፤01 መዝገብ የገ/መጠን 183223 ብር ዉስጥ 144166 ብር የያዘ ከክስ በኋላ በድርድር ሲጠናቀቅ፤ቀሪ 08 መዝገቦች 878338 ብር እና 13.782 ገመድ መሬት እና ልጅ ይመለስልኝ የያዙ በፍ/ቤት በቀጠሮ ላይ ናቸዉ፡፡

የሰነዶች፣የጠበቆች ምዝገባ እና ማረጋገጫ የስራን ክፍልን በተመለከተ ከፍታብሄር የስራ ሂደት ጋር የሚሰራ ሲሆን ውክልና መስጠት 746 ፣ ውክልና መሻር 22፣ትምህርት ስልጠና 16፤ የስራ ቅጥር 07፣የኪራይ ውል 28፣ቃለማህላ 249 ፣ ቅጅ ማመሳከር 06፤ከጋብቻ በፊትና በኋላ ንብረታቸዉን አስመልክቶ የሚያደርጓቸዉ ዉሎች 0፤ ልዩ ልዩ 0 በድምሩ 1165 ሰነዶች ተረጋግጦ የተመዘገበ ሲሆን በዚህ አገልግሎት ከቴምብር እና የአገልግሎት ክፍያ 758248.45 ብር ገቢ ተደርጓል፡፡

  1. ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች

የአየር ሰዓት መግዛት የወረዳዉን ኢኮኖሚያዊ፤ማህበራዊ እና ባህላዊ ሁነቶችን እና እንቅስቃሴዎችን በመዘገብና በማቅረብ የወረዳዉን መልካም ገፅታ በመገንባት የህብረተሰቡ ጥያቄዎች በአየር ላይ በማዋል ምላሽ እና እዉቅና እንዲያገኙ ለማድረግ በብሮድ ካስት ሜድያ 306 ዜና ለማስተላለፍ ታቅዶ ማለትም በአብመድ ዜና በሬድዮ 135፤ በቴሌቪዥን 74፤ በፋና ዜና በሬድዮ  35፤ በኢቢሲ ዜና በቴሌቪዥን 35፤በአካባቢ ማህበረሰብ ሬድዮ 44 በድምሩ 323 ዜናዎች በማስተላለፍ >100% ማድረግ ተችላል፡፡

በወሳኝ ጉዳዮች ላይ የክልሉን መንግስትን አቋም የሚያንፀባርቁ ጽሁፎችን በማዘጋጀትና በሚዲያዎች በማቅረብ ግንዛቤ ለመፍጠር እና የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማሳደግ 12 እቅድ ተይዞ 11 በመፈጸም 91.6% በላይ አፈፃፀም ተፈፅሟል፡፡

ነባር ሚኒሚዲያ ማጠናከር እቅድ 25 ክንዉን 108፣ ነባር ማስታወቂያ ሰሌዳ  ማጠናከር እቅድ 18 ክንዉን 18፣ነባር የመረጃ ማዕከላት ዕቅድ 13 ክንዉን 14 በማከናወን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ልማታዊ አስተሳሰብን ለማጎልበት በተመረቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ  የአቋም መግለጫ ዕቅድ 6 ክንዉን 8፤የፕሬስ ኮንፈረንስ ዕቅድ 6 ክንዉን 12፤ተሞክሮ ቅመራ ዕቅድ 2 ክንዉን 4፤ተሞክሮ ማስፋት ዕቅድ 2 ክንዉን 4፤ቋሚ ኤግዚቪሽን ዕቅድ 6 ክንዉን 12፤የሚዲያ ጥቆማ ዕቅድ 6 ክንዉን 9፤ለዉሳኔ ሰጪ አካላት የሚቀርቡ ሳምንታዊ መረጃ ዕቅድ 24 ክንዉን 48 መስራት ተችሏል፡፡

6.ቅሬታ ማስተናገጃ ጉዳዮች

ቅሬታ ማስተናገጃ ስርዓቱን ለማስፈፀም በሚያግዝ መንገድ ክፍተቶችን የለየ ለተለያዩ አካላት ስልጠና ለመስጠት 600 በዕቅድ ተይዞ ለቀበሌ ስራ አስኪያጅ እና ለቀበሌ አመቻች በድምሩ 1876 ለማሰልጠን ተችሏል፡፡ከህብረተሰቡ ለሚቀርቡ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ዉሳኔ አሰጣጥን ለማሸሻል የተሰሩ ስራዎች አንፃር 123 ዉስጥ 123 ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ተችሏል፡፡በመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አቤቱታ የቀረበባቸዉ በከተማ አገልግሎት አሰጣጥ 3፤ከሰዉ ሀይል አገልግሎት አሠጣጥ አንፃር 1፡እና ከአስተዳደራዊ አገልግሎት አንፃር13  መሆኑን ያሳያል፡፡

ቅሬታ የቀረበባቸዉ አገልግሎት ሰጪ መስሪያ ቤቶች ከገጠር መሬት አስተዳደር 12 ጉዳዮ፤የከተማ ቦታና አገልግሎት 4 ጉዳዮች፤ከአመራር አገልግሎት ጋር በተገናኘ 14፤ከፍትህና ፍ/ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተየያዘ 1፤ከፖሊስና ሚኒሻ አገልግሎት 3 ጉዳዮች፤ከሲቪል ሰርቪስና የሰዉ ሃይል 7 ቅሬታዎች ቀርበዉ በማጣራት ምላሽ ለመስጠት ተችሏል፡፡

  1. ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች
    • ከሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ

 የሴቶችን ሁለንተናዊ ብቃት በመገንባት በፖለቲካ፣በኢኮኖሚና በማህበራዊ መስኮች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በወረዳ ልማት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የራሳቸዉን ሚና እንዲያበረክቱ ማስቻል እንዲሁም የህጻናትን መብትና ደህንነት በማክበርና በማረጋገጥ ህጻናት በማህበራዊና መልካም አስተዳደር መስኮች እኩል ተሳታፊነታቸዉና ፍትሃዊ ተጠቃሚነታቸዉን ማሳደግ በሚል ትኩረት መስክ ለማሳካት፡-

በጥቃቅንና አነስተኛ መስኮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ግንዛቤ የተፈጠረላቸው ሴቶች /አዋቂና ወጣት/ በቁጥር 594 ታቅዶ እስከዚህ ሩብ አመት ለ2082 አፈፃፀም 100% ግንዛቤ ለመፍጠር ተችሏል፡፡

በጎጂ ልማዳዊ ድረጊቶችና የሃይል ጥቃት ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር ለ26000 የህብረተሰብ ክፍል ለመፍጠር ታቅዶ 13807 ማህበረሰብ ግንዛቤ መፍጠር 53.1% መፈፀም ተችሏል፡፡በልጅነት ጋብቻ ነፃ የሆኑ ቀበሌዎች 5 ክንዉን 12 ፤በእንጥል ማስቆረጥ ነፃ የሆኑ ቀበሌዎች በዕቅድ 13 ክንዉን 3፤በሴትልጅ ግርዛት ነፃ ቀበሌዎች በዕቅድ 5 ክንዉን ..በያዝነዉ ሩብ ዓመት ማከናዎን ተችሏል፡፡

የጡት የማህፀን ካንሰር እና የማህፀን መዉጣት ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ለሴቶች ግንዛቤ መፍጠር በዕቅድ 0 ተይዞ በክንዉን 0 አፈጻፀም --% መሆኑን ያሳያል፡፡

በኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት ለመከላከልና ስነ ተዋልዶ ዙሪያ ጤና አገልግሎት ግንዛቤ ያገኙት በዕቅድ 32290 ክንዉን 9560 በመፈፀም 39.4% መፈጸም ተችሏል፡፡ ምርመራ በማድረግ ሲታይ በዕቅድ 1076 ተይዞ ምርመራ ያደረጉ 2 በማድረስ 0.4% ማከናወን ተችሏል፡፡   

 በክትትልና ድጋፍ የተደረገላቸዉ በገቢ ማስገኛ ስራዎች የተሰማሩ የገጠር ሴቶች በቁጥር /አዋቂና ወጣት /ሴቶች ዕቅድ 1482 ክንዉን 2082 />100%/ ክትትል ተደርጓል፡፡በቁጠባ አገልግሎትና ብድር አመላስ ዙሪያ ግንዛቤ የተፈጠረላቸዉ ሴቶች /እማወራና ባለትዳር/ለ19374 በእቅድ ተይዞ እስከዚህ ወር የተከናወነ 2018/55.1%/ተከናዉፈኗል፡፡

ህፃናትን በፎስተር ኬር የአደራ ቤተሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ 4 ህፃናትን ለማሳደግ

ዕቅድ ተይዞ 2 ህፃናትን በማስረከብ 50% መፈፀም ተችሏል፡፡በማህበረሰብ ድጋ ክብካቤና ጥምረት ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር የጥምረት አዲስ አባል የሆኑ የህ/ብ ብዛት በዕቅድ 440 ተይዞ 4445 በመፈፀም >100% መፈፀም ተችሏል፡፡በዚህም 890 ህፃናን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ 74 ህፃናት ብቻ ታግዘዋል፡፡ ስለሆነም ተገቢዉ ልየታ ተደርጎ መረዳትና መደገፍ የሚገባቸዉ መፈፀም ይኖርበታል፡፡

    በህጻናት በህገ ወጥ ዝዉዉር ፣ጉልበት ብዝበዛና በማህበራዊ ጠንቅ ተጋላጭነት ዙሪያ ግንዛቤ የተፈጠረላቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች ቁጥር በአመት ለ7320 ግንዛቤ ለመስጠት ታቅዶ1830/25%/ ነዉ፡፡ በወጣጦች የህይወት ክህሎት ዙሪያ ግንዛቤ ያገኙ በዕቅድ 4854 ክንዉን 728/14.9%/፤በወጣቶች አቻ ለአቻ ግንዛቤ ያገኙ 5006 በዕቅድ ተይዞ ክንዉን 751፤በማህበራዊ ተጋላጭነት ዙሪያ በዕቅድ 7320 በክንዉን 548 ግንዛቤ ለመፍጠር ተችሏል፡፡

5.2 ከወጣቶች አኳያ

የወጣት ማዕከላት ለወጣቶች የስነ ተዋልዶ ጤናና ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከል አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ፣ታቅዶ በተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ተጠቃሚ የሆኑ ጣቶች ለ343 ወ 172 ሴ 171 ታቅዶ ለ306 ወ 113 ሴ 193 አፈፃፀም 89%

በአሉታዊ መጤ ልማዶች እና አደንዛዥ እፆች ዙሪያ ለወጣቶች  ለሃይማኖት መሪዎች፣ ለተቋም አመራሮች እና የግብረ-ሃይልአባላትግንዛቤ ለመፍጠርለ11200 ወ 5600 ሴ 5600 በእቅድ ተይዞ ለ4581 ወ 2713 ሴ 1668 ወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫትምህርት መስጠት ተችሏል፡፡ለወጣቶች ለ 11200 ወ 5600 ሴ5600 ታቅዶለ4581 ወ 2913 ሴ 1668  መፈፀም ተቸሏል፡፡የጠባቂነት አመለካከታቸው እንዲለወጥና የስራ ባህል እንዲያዳብሩ ለማስቻል ለ 7722 ወ 3861 ሴ 3861 ወጣቶች ግንዛቤ ለመፍጠር ታቅዶለ4939 ወ 3417 ሴ 1564 ወጣቶች 63%

በመልካም አስተዳደርና በጸረ ኪራይ ሰብሳቢነት ግንዛቤ የተፈጠረላቸው ወጣቶች በሩብ አመት ወ 731… ሴ730 … ድ1461 … እቅድተይዞ ወ 316… ሴ94 … ድ410 … የተከናወነ ሲሆን እስከ ዚህ ወር/ሩብ ዓመት/ ወ 943 ሴ 161 ድ 1104 ተከናውኗል፡፡ይህም የእቅዱን 19% መፈጸም ተችሏል፡፡

የወጣተች የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማሰማራት በዕቅድ 34758 ታቅዶ በክንዉን 29506 በማሳተፍ የዕቀዱን 84.8% መፈፀም ተችሏል፡፡

በብድር አጠቃቅምና አመላልስ 8189 ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር ታቅዶ 1228 በወጣቶች ግንዛቤ ለመፍጠር ተችሏል፡፡

የወጣቶችን ማህበራዊ ጠንቅ ተጋላጭነት ከመቀነስ አኳያ በማህበራዊ ጠንቅ ተጋላጭነት ዙሪያ በድምር 7320 ወጣቶች ግንዛቤ ለመፍጠር ታቅዶ በድምር 1830/13%/

ወጣቶች ቅሬታ ይዘው የሚመጡ ወጣት ደንበኞች ቁጥር በ50%መቀነስ በዚህ ሩብ አመት  ወ 5 ሴ 4ድ 9 እቅድተይዞ ወ 2 ሴ13  ድ 15 የተከናወነ ሲሆንእስከዚህ ወር/ሩብ ዓመት/ ወ 2 ሴ 13 ድ 15 ተከናውኗል፡፡ይህም የእቅዳቸንን 39%መፈጸም ተችሏል፡፡

  • ካል ጉዳተኛ፣

በወረዳችን ዉስጥ ካሉ ማህበረሰብ መካከል ለ125 ወንድና ለ70 ሴት በድምሩ ለ195 አካል ጉዳተኛ ድጋፍ ለማድረግ በእቅድ ተይዞ ለ16 ወንድ ለ32 ሴት በድምር 48/8.15%/ የበግና ፍየል ፣የአልባሳትና የህክምና አገልግሎት ድጋፍ ተደርጓል፡፡

5.4.ስነ ህዝብ፡-

  በ1985 ዓ.ም በወጣዉ የስነ-ህዝብ ፖሊሲ መሰረት በማድረግ የስነ ህዝብ ተግባራትን ከወረዳ እስከ ቀበሌ ለሚቋቋሙ ስትሪንግ ኮሚቴና የቴክኒክ ኮሚቴ አማካኝነት በማቀድ፣በመከታተል፣በመገምገም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ማህበራዊ ደህንነቱን ፣ሰብአዊ መብቱን የተከበረና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸዉ የተጠበቀለት ማህበረሰብ መፍጠር እንዲያስፈልግ ተቀምጧል፡፡በተለይም አምራች ሀይሉ ከህጻናት ጥገኝነትና ከእርጅና ጥገኝነት የበለጠ እንዲሆን በማድረግ ከኢኮኖሚ ጋር የተመጣጠነ ህብረተሰብ ማፍራት ተገቢ ነዉ፡፡በዚህም መሰረት በወረዳችን ያሉ ሴ/ርና መ/ቤቶች ከዕቅዳቸዉ ጋር በማካተት መፈጸም እንደሚገባ ታምኖበት በዕቅድ ተካቶ ለመስራት ሙከራዎች አሉ፡፡ስለሆነም ስነ ህዝብ ጉዳይ በእቅዳቸዉ አካተዉ ያቀዱ መ/ቤቶች ብዛት 12 ናቸዉ፡፡

የስነ ህዝብ ም/ቤት ያቋቋሙ ቀበሌዎች ብዛት 12 ሲሆኑ የስነ ህዝብ የቴክኒክ ኮሚቴ ያቋቋሙ ቀበሌዎች ብዛት 12 ናቸዉ፡፡የስነ ህዝብ ዕቅድ ያቀዱ ቀበሌዎች ብዛት  5 ናቸዉ፡፡በወረዳችን ካሉ 66 ት/ቤቶች ዉስጥ በት/ቤቶች የስነ ህዝብ ክበብ ያቋቋሙ ት/ቤት ብዛት 0/0%/ ናቸዉ፡፡በበጀት አመቱ ስነ ህዝብን በእቅድ አቅደዉ መላክ ከለባቸዉ 37 ሴክተሮች 13 ሴክተሮች አቅደዉ የላኩ ናቸዉ፡፡

5.5. ካፒታል ፕሮጀክት አኳያ፡-

    የ2012 በጀት የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እና በ2013 በ2014 የቀጠሉ

  1. በወርደው አስተዳድር  ጽ/ቤት G+3 ህንፃ በመንግስት በጀት በተቋራጭ ዘውዱ ዮሀኒስ ጠቅላላ ስራ  ተቋራጭ ብር 9.056.452.7/  ዘጠኝ ሚሊየን ሃምሳ ስድስት ሽህ አራት መቶ ሃምሳ ሁለት ብር ከ71/100  ውልየገባ ቢሆንም በውሉ  በላይ የተጓተተና ስራዉ የተቋረጠ መሆኑ፣

6.የህብረተሰብ ተሳትፎ

    በወረዳችን ያሉትን የዉሃ ተቋማት ጥገና ስራየህብረተሰብ ተሳትፎ የህብረተሰብ ክፍል በጥገና ስራ ላይ የተሳተፈ ሲሆን የህብረተሰብ ተሳትፎ በጉልበት 199500 ታቅዶ በገንዘብ በድምሩ 128750 ብር የሚገመት የጉልበት አስተዋጽኦ በህብረተሰቡ ተሸፍኗል፡፡50000 የሚገመት ቁሳቁስ ከህብረተሰቡ ለመሰብሰብ ታቅዶ 35169 ብር የሚገመት ቁሳቁስ ከህብረተሰብ ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡83125 ብር ለጥገና የሚዉል የገንዘብ መዋጮ ለመሰብስብ ታቅዶ 21479 ብር ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡የንጹህ መጠጥ ተቋማት መገንባት ከህብረተሰቡ በእቅድ ደረጃ በጉልበት 900000 በቁሳቁስ 210000 በጥሬ ገንዘብ 900000 ለመሰብሰብ በእቅድ ተይዞ 210000 ጉልበት በገንዘብ፣108300 ቁሳቁስ በገንዘብ ና በጥሬ ገንዘብ 197400 ብር መሰብሰቡ፣

   በተፈጥሮ ሰዉ ሰራሽ ቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ሙዝየም ግንባታ በገንዘብ፣በጉልበት በቁሳቅስ የህብረተሰብ ተሳትፎ ዕቅድ ከህብረተሰብ የተገኘ የገንዘብ መጠን 35200 ክንዉን 800000 አፈጻጸም >100፣ጉልበት ተሳትፎ እቅድ 52800 ክንዉን 108550 አፈጻጸም >100፣ቁሳቁስ ተሳትፎ በገንዘብ ሲተመን እቅድ 10350 ክንዉን 139500 አፈጻጸም >100%፣

7.የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎን

7.1. ጠንካራ ጐን፣

  • በአዲሱ በጀት ዓመት በአዲስ ወደ ግብረ መረቡ የገቡትን ነጋዴዎችና አከራይ ተብለው የተለዩትን በወቅቱ በመወሰን አሰራጭቶ ግብሩን ለመሰብሰብ የተቻለ ሲሆን በወረዳዉ ኢኮኖሚ በሚያመነጨዉ በብቃት ለመሰብሰብ ብር 69501175 ለመሰብሰብ በዕቅድ ተይዞ እስከዚህ ወር የተሰበሰበ 62406240 አፈጻጸም 89%
  • የንግድ ምዝገባ ምትክ፣የንግድ ፍቃድ እድሳት፣አዲስ የንግድ ፍቃድ፣የንግድ ምዝገባ ማሻሻያ የተሰራ ስራ የተሻለ መሆኑ፣
  • በትምህርት ዘመኑ ለ34173 የ1ኛ ደረጃ ተማሪዎች ለመማር ለመመዝገብ ለማቀድ ተይዞ በአመቱ መጀመሪያ ለ25688 አፈጻጸሙም 75.17 መመዝገብ መቻሉ፣
  • የኢነርጂ ምንጮችና ቴክኖሎጂ ህ/ሰቡ እንዲላመዷቸዉ ተጠቃሚ እንዲሆኑባቸዉ ከመቻል የተሰራ ስራ የተሻለ መሆኑ፣
  • ከህብረተሰቡ የዉሃ ተቋማትን ለመጠገን የተሰበሰበ ብር አፈጻጸም የተሻለ መሆኑ፣
  • በወረዳችን ላይ ባሉ መስመሮች ላይ የተሸከርካሪና የአሽከርካሪን በመቆጣጠር 2 ትራፊክ 2 የመንገድ ደህንነትና ስምሪት ባለሙያዎች 1531 መኪና የተከሰሰ ሲሆን 1418180 ብር ተሰብስቦ 1418180 ብር ለመንግስት ገቢ ተደርጓል፡፡
  • በበጀት አመቱ በወንጀል ጉዳይ እስከዚህሩብ አመት 119 መዝገቦች የቀረበ ሲሆን ከዚህም ዉስጥ አቃቢ ህግ 119 መዝገቦች ላይ ዉሳኔ መሰጠቱ፣
  • ገብያ ባለቸዉ ሙያዎች መደበኛ ባልሆኑ አጫጭር ስልጠና በከተማና በገጠር በቴክኒካል ክህሎት አፈጻጸም የተሻለ፣
  • በወረዳ መስመሮች በተዘጉ መንገዶች የመንገድ ጥገና በማሽን ስራ በኪ.ሜ እቅድ ክንዉን አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆኑ፣
  • በከተማና ገጠር የተፈጠረ የስራ እድል አፈጻጸም የተሸሻለ መሆኑ፣
  • ደካማ ጐን

   የተወሠኑ ሴክተሮች  ሪፖርቱን በወቅቱ ሰርቶ አለመላክና እንደተቋም የተገመገመ ሪፖርት አለማድረግ ታይቷል፤ይህ እንዳለ ሆኖ በኢኮኖሚ፤ በማህበራዊና በመልካም አስተዳደር ዘርፍ ሲታይ እንደ መነሻ፡-

  1. መሰረታዊ ምርቶች አቅርቦት ስርጭት ፣ዘይትና የዳቦ ዱቄት አቅርቦት አቅድ አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆኑ፣
  2. የተፈፀመ አጠቃላይ ወንጀል በገጠር 85 በከተማ 47 በድምሩ 132 ሲሆን ከዚህ ውስጥ የተፈጸመ ዋና ዋና ወንጀሎች በገጠር 63 በከተማ 19 ድምር 82 ናቸው፡፡
  3. የዉሃ ተቋማትን ለማስገንባት የህብረተሰብ ተሳትፎ አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆኑ፣

8.ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎች

8.1. ያጋጠሙ ችግሮች

  • የአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ለስራ መሰናክል መሆኑ፣
  • የተቋሙን ተልዕኮ ሊያሳይ በሚችል መልኩ የአጠቃላይ ዓላማ ማስቀመጥና የተቀመጠዉን ዓላማ ሊሣኩ የሚችሉ ግቦችና ተግባርት ከዕቅድ ጋር እየተነፃፀረ መቅረብ ሲገባዉ እንደዘገባ የተግባራት አፈጻፀም ብቻ መሰራቱ በብዙ ተቋማት መታየቱ
  • የተወሰኑ ሴክተር መ/ቤቶች የማህበረሰብ አቀፍ አሳታፊ አቅድ መሰረት ያደረገ ሪፖርት አለመስራት
  • ሴክተሮች ሪፖርቱን ወቅቱን ጠብቆ ለሚመለከተዉ አካል ጥራቱን በጠበቀ መልኩ መስራትና መላክ አለመቻል ፡፡
  • ሴክተሮች የሪፖርት ጥራት ለምሳሌ የዕቅድ አለመታቀድ፤የተደጋገመ ሪፖርት መሰራቱ፡
  • አንዳንድ ተቋማት ሪፖርት ዉጤት አመላከች በሆነ መንገድ ሪፖርቱን አለማዘጋጀት፣
  • አንዳንድ ተቋማት ሪፖርት ፈጽሞ አለመላክ ለምሳሌ ጤና ጽ/ቤት፣እንስሳት ጽ/ቤት፣ፖሊስ ጽ/ቤት

8.2. የተወሰዱ መፍትሄዎች

  • ተቋማት አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ስራዎችን ለመስራት ተችሏል፡፡
  • ሴክተሮች ሪፖርት በወቅቱ እንዲላኩ በደብዳቤ ገልጽን የላክንና በስልክ ደዉለን የጠየቅን መሆኑ በዚህ መሰረት የተወሰኑ ሴክተሮች የላኩ መሆኑ ፤ነገር ግን ችግሩ አሁንም አሳሳቢ መሆኑ
  • የሪፖርት ጥራት ከሴክተሮች ባለሙያ ጋር በስልክ በመነጋገር የሪፖርቱን ጥራት ባስጠበቀ መልኩ ለመስራት ተችሏል፡፡
  • ከሚመለከታቸዉ ጋር በመነጋገር የሚያጋጥሙን ችግሮችን መፍታት

     9.ማጠቃለያ

      በተለያዩ የሰብል አይነቶች 11110  ሄ/ር የሰብል ስብጠር ልማት ለማልማት በእቅድ ተይዞ ጠቅላላ የተዘራ ዋና ሰብል በሄ/ር 22092፣ጠቅላላ የተዘራ 2ኛ ሰብል በሄ/ር 0 ተሳታፊ ወንድ 21178 ሴት 508 ድምር 18086 የተለያዩ የሰብል አይነቶች ማለትም ለበቆሎና ባቄላ፣በቆሎና ቦለቄ፤ማሻላና ቦለቄ፣ማሽላና በማቀናጀት የተሰራ ነዉ፡፡ዩሪያ ሳይድ ድሬሲንግ በዕቅድ 41610 የተዘራ 43326 ዩሪያ የተደረገበት 38530 ሲሆን የተሳታፊ ብዛት፣ዩሪያ መጠን 42421 ተሳታፊ ወንድ 49375 ሴት 2706 ድምር 52081 ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ትምህርት ዘርፍ የትምህርትን ጥራት እና ተደራሽነት ለማሳደግ የሳተላይት ት/ቤቶች ዕቅድ 67 ሲሆን ክንዉን 67 ማድረግ ተችሏል፡፡ በአጠቃላይ የሙሉ ሳይክል ት/ቤቶች ያገኙ ቀበሌዎች ዕቅድ 25 ሲሆን ክንዉን 25 ማድረስ ተችሏል፡፡ጠቅላላ በ67 ት/ት ቤቶች በአጠቃላይ በበጀት አመቱ መጀመሪያ ወደ ትምህርት ገበታ መግባት በ1-6  ክፍል  ከነበረባቸዉ ወንድ 10653 ሴት 10146 ድምር 20930 የተመዘገበ ሲሆን በመማር ላይ ያለ ወንድ 10467 ሴት 10146 ድምር 20613 አፈጻጸም 98.5%፣7-8ኛ ለመማር የተመዘገቡ ወንድ 2320 ሴት 2577 ድምር 4897 በሩብ ዓመቱ መጨረሻ በመማር ላይ ያሉ 2135 ሴት 2474 ድምር 4613 አፈፃፀም 94.2%፤በኦ ክፍል በዓመቱ መጀመሪያ የተመዘገቡ ወንድ 1984 ሴት 1918 ድምር 3902 ሲሆን በሩብ ዓመቱ መጨረሻ በመማር ላይ ያሉ ወንድ 1984 ሴት 1918 ድምር 3902 አፈፃፀሙ 100%፤የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት 9-12 በዓመቱ መጀመሪያ የተመዘገቡ ወንድ 2320 ሴት 2577 ድምር 4897 ሲሆን በሩብ ዓመቱ መጨረሻ በመማር ላይ ያሉ ወንድ 2139 ሴት 2474 ድምር 4613 አፈፃፀም 94.2%ነዉ፡፡በአጠቃላይ በገጠርና ከተማ  ቋሚ ወንድ 1743 ሴት 633 ድምር 2376 የስራ እድል  ጊዚያዊ ወንድ 5952 ሴት 894 ድምር 6846 በአጠቃላይ ቋሚ ጊዜያዊ ወንድ 7695  ሴት 1527 ድምር 9222 የስራ እድል ተፈጥሯል፡፡መሰረታዊ ምርቶች አቅርቦት ስርጭት ስኳር የዓመቱ እቅድ 1394 ኩ/ል ሲሆን ክንውኑ 1312 ኩ/ል በማሰራጨት አፈጻጸም 94.11%፤የዳቦ ዱቄት የዓመቱ እቅድ 233 ኩ/ል ክንውን 233 ኩ/ል 100%፤  የፓልም ዘይት በሊትር የዓመቱ እቅድ 270000 ሊትር ክንውን 61050 ሊ/ር 22.6%፤  ከገቢ አሰባሰብአኳያ፡- በአዲሱ በጀት ዓመት በአዲስ ወደ ግብረ መረቡ የገቡትን ነጋዴዎችና አከራይ ተብለው የተለዩትን በወቅቱ በመወሰን አሰራጭቶ ግብሩን ለመሰብሰብ የተቻለ ሲሆን በወረዳዉ ኢኮኖሚ በሚያመነጨዉ በብቃት ለመሰብሰብ ብር 69501175 ለመሰብሰብ በዕቅድ ተይዞ እስከዚህ ወር የተሰበሰበ 62406240.23 አፈጻጸም 65.6%፡፡