የባሶሊበን ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት

ግብርና በወረዳው ኢኮኖሚ የመሪነቱን ደረጃ እንደያዘ የሚገኝ ሴክተር ነው፡፡

ሴክተሩ ለምግብ፤ ለአገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃና የውጭ ምንዛሬ

ምንጭ ሲሆን ወረዳው ሰፊ ከመሆኑና የተለያየ ስነ-ምህዳር ባለቤት ከመሆኑ

አንፃር  ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚውሉ እና ለውጭ አገር ገበያ የሚሆኑ

የተለያዩ የግብርና ምርቶችን በብዛት ለማምረት ያስችላል፡፡ የግብርናው

ክፍለ ኢኮኖሚ አጠቃላይ ኢኮኖሚውን ለማንቀሳቀስ የሚያስችል ሀብት

መፍጠር የሚቻልበት ከመሆኑ አንፃር እስካሁን ድረስ ትኩረት የተሰጠው

 ሴክተር ነው።

ወረዳው በርካታ የእህልና ጥራጥሬ እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬ

 ቢያመርትም በደረጃ ሲታይ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ጤፍ፣ ባቄላና አተር

በቅደም ተከተል የሚያበቅልና በአሁኑ ወቅት ከጊዜ ጊዜ እየጨመሩ

 የመጡትን ሰሊጥና የፍራፍሬ ምርቶች ባለቤትም ነው፡፡ በተለይ

 የዳቦ ስንዴና ከቅባት እህሎች ከፍተኛ ተፈላጊነት ያለውን ሰሊጥ

 ከመደበኛ እርሻ ባሻገርም ባለሃብቶች ቦታ በመረከብ የኢንቨስትመንት

 ሥራ በመጀመራቸው ለገበያ የሚፈለጉ ምርቶችን የመከተል ሥራ

በገበሬውም ተቀባይነት እንዲያገኝ የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን

 ያመላክታል፡፡ሰብል ልማት ወረዳው ከሚያካሄደው የእርሻ ስራ ውስጥ

ዋነኛውናትልቅ ድርሻ ያለው ክፍል ነው። በዚህም መሰረት ወረዳው የተለያዩ

ዓመታዊ ሰብሎችን (የብርዕ እና የአገዳ እህል፤ ጥራጥሬ፤ የቅባት እህሎች፤

 እንዲሁም የስራስር ተክሎች) እና  ቋሚ ሰብሎችን ስነ-ምህዳርን መሰረት

በማድረግ ያመርታል፡፡ የመኸር እርሻን በሚመለከት በወረዳው በ2011/12 ዓ.ም

 ስፋቱ 46418.5 ሄ/ር ማሳ ታርሶ 1498777.9 ኩ/ል ምርት ተሰብስቧል፡፡

መስኖ ልማትን በሚመለከት በ2012 በመስኖ 1314 ሄ/ር መሬት ለምቶ የነበር

ሲሆን የተገኘው ምርት ደግሞ ወደ 134602.24 ኩንታል ሆኗል፡፡ ይህ ውጤት

ውኃን የልማት ማዕከል አድርጎ በተካሄደ የተቀናጀ ጥረት ቢሆንም ከአምናው

ተመሳሳይ የምርት ዘመን ጋር ሲነጻጸር የምርት መቀነስ ይታይበታል፡፡ አሁንም

ወረዳው ካለው የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር ውሃ ሀብት አኳያ መጠቀምና

ማልማት የሚቻለውን ያህል ለምቷል ማለት አይቻልም። ስለሆነም ከውሃ

ሃብታችን  የሚገኘውንጥቅም ለማጎልበት  ገና ብዙ መስራትን ይጠይቃል።

 የኤክስቴንሽን አገልግሎቱም የቴክኖሎጂ ሽግግር በማምጣት የአርሶ አደሩን ገቢ

በከፍተኛ ደረጃ ሊያሻሽልና

በአጠቃላይም ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት ለማምጣት አስተዋጽኦ እንዲያበረክት

ሆኖ መቀጠል ይገባዋል።